የዳኞችና የፌዴሬሽን አመራሮች ስብሰባ በኮማንድ ፖስቱ ተከለከለ:: እሁድ በጁፒተር ሆቴል ሊካሄድ የታሰበው ይኸው ስብሰባ የፍቃድ ጥያቄ ቢቀርብም በኮማንድ ፖስቱ መከልከሉ ታውቋል። ከፌዴሬሽኑ ውስጥ አዋቂ በተገኘ መረጃ ፕሬዝዳንቱ ከመከላከያ ሚኒስቴር ወይም ከፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ጋር ተነጋግረው ፍቃድ እንዲገኝ ለማድረግ እየጣሩ መሆናቸው ታውቋል። ምናልባት የአቶ ጁነዲን ጥረት ተሳክቶ ውይይቱ የሚካሄድ ከሆነ ለመገናኛ ብዙሃኑ ዝግ መሆኑ ታውቋል::
↧