Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all 419 articles
Browse latest View live

ባሕር ዳር ላይ በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን 2ለ1 አሸንፋለች

$
0
0

ጨዋታውን አስመልክቶ አሰልጣኙ፣ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሙሉ የጨዋታ ብልጫ እና የኳስ ቁጥጥር ከጥሩ የግብ ሙከራዎች ጋር በማሸነፋችን ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። ዋልያዎቹ ጨዋታውን ማሸነፋቸው በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለመሳተፍ መልካም ጅምር መሆኑን እና ከምድቡ ከባድ ከተባለው ቡድን ሙሉ ሦስት ነጥብ መውሰዳቸው ለቀጣይ ጨዋታ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን ነው ኢንስትራክተር አብርሃም የተናገሩት። የዛሬው ውጤት ለቀጣይ ጨዋታዎች በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲዘጋጁ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አሰልጣኙ ገልጸዋል። ተጨዋቾች በሜዳ ውስጥ የነበራቸው እንቅስቃሴ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት መሆኑን በመጥቀስም አስጣኙ ምሥጋና አቅርበዋል። ከብሔራዊ ቡድኑ ጀርባ ሆነው በጥሩ ሥነ ምግባር ሲደግፉ የነበሩትን የባሕር

The post ባሕር ዳር ላይ በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን 2ለ1 አሸንፋለች appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.


ለአበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር ሊካሄድ ነው

$
0
0

ለጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በጃፖን ካሳማ ከተማ ከነገ በስቲያ የግማሽ ማራቶን ውድድር ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ ላይ ለመካፈልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ልኡካን ቡድን በስፍራው መገኘታቸውን ፌዴሬሽኑ በድረገጹ አስነብቧል፡፡ የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እና የሻምበል አበበ ቢቂላን ልጅ አቶ የትናየት አበበን ያካተተው ልኡክም በቶኪዮ ኦሊምፒክና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ማካሄዱ ታውቋል። በብርሃን ፈይሳ ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ድረ ገጽ (ኢ.ፕ.ድ)

The post ለአበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር ሊካሄድ ነው appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ዓመታዊ የእግር ኳስ ደረጃ ከዓለም 146ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች

$
0
0

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ዓመታዊ የሀገራት እግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ በወንዶች ከዓለም በነበረችበት 146ኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡ ቤልጂየም ፈረንሳይና ብራዚል ከ1ኛ-3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ከዓለም 20ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሴኔጋል በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች፡፡ ቱኒዚያና ከዓለም (27ኛ) ከአፍሪካ 2ኛ፤ ናይጄሪያ ከዓለም 31ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ ሶማሊያ፤ ሲሽልስና ኤርትራ የመጨረሻውን ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሀገራት ናቸው፡፡ በሴቶች ኢትዮጵያ ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 109ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ አሜሪካ ጀርመንና ኔዘርላንድ ከዓለም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሀገራት ናቸው፡፡ ምንጭ፡- ፊፋ

The post ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ዓመታዊ የእግር ኳስ ደረጃ ከዓለም 146ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ

$
0
0

በለንደን ከተማ በተካሄደው የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን፤ ቀነኒሳ በቀለ ክብረ-ወሰን በመስበር አሸንፏል። የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በዚህ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። 1:00:22 በሆነ ሰዓት የገባው ቀነኒሳ፤ በእንግሊዛዊው ሯጭ ሞ ፋራህ የተያዘውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ከቀነኒሳ ጋር ይፋጠጣል ተብሎ የተጠበቀው ሞ ፋራህ ከጥቂት ቀናት በፊት በህመም ምክንያት እንዳይማሰተፍ አሳውቆ ነበር። © The Vitality Big Half የቢቢሲ አማርኛ

The post ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

ሮምን የወረረው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ወታደር አበበ ቢቂላ

$
0
0

አበበ ቢቂላ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም በቀድሞው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ አካባቢ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ባሕልና ልማድ በእረኝነትና በትምሕርት ተሰማርቶ በ12 ዓመቱ የቄስ ትምህርቱን አጠናቀቀ። አበበ ገና በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥር የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ ሠራዊት በወታደርነት ይቀጠርና በገና ጨዋታ እና በስፖርት እየዳበረ ቆየ። ክቡር ዘበኛ ሠራዊት ውስጥ ሲገባም፤ ከስፖርት ጋር ይበልጥ ተቀራረበ እንጂ አልተራራቀም። ከውትድርና አገልግሎት ጎን ለጎን፤ በሠራዊቱ የስፖርት እንቅስቃሴ በተለይም በአትሌቲክስና በገና ጨዋታ ጎልቶ ለመታየት ጊዜ አልፈጀበትም። በኅዳር ወር 1948 ዓ.ም በአስራ ስድስተኛው የሜልቦርን ኦሊምፒክ ላይ የተሳተፈውን የኢትዮጵያን ቡድን

The post ሮምን የወረረው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ወታደር አበበ ቢቂላ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

ሪያል ማድሪድ 34ኛ የላ ሊጋ ዋንጫውን አሸነፈ

$
0
0

ትናንት ምሽት በተደረጉ የ37ኛ ሳምንት የላ ሊጋ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ቪላሪያልን አስተናግዶ 2 ለ 1 በማሸነፍ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው 34ኛ የላሊጋ ዋንጫውን አሸንፏል፡፡ በምሸቱ በተከናወነው ጨዋታ ለሪያል ማድሪድ ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ካሪም ቤንዜማ ነው ያስቆጠረው፡፡ ከተከታዩ ባርሴሎና በሰባት ነጥብ ልዩነት የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ያረጋገጠው ማድሪድ ከሶስት አመታት በኋላ የላ ሊጋ ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡ ባለፉት ሶስት አመታት የላሊጋው የበላይ የነበረው ባርሴሎና በምሽቱ ጨዋታ በሜዳው በኦሳሱና ሁለት ለአንድ ተሸንፏል፡፡ ከድሉ በኋላ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን በሰጠው አስተያየት ከሶስት ዓመታት በኋላ ከማድሪድ ጋር ላ ሊጋን ማሸነፉ ከሻምፒዮንስ ሊግ ድል በላይ እንዳስደሰተው ገልጿል፡፡ ” ይህ ድል ከምንም በላይ ነው ያለው አሰልጣኝ ዚዳን ዋንጫውን

The post ሪያል ማድሪድ 34ኛ የላ ሊጋ ዋንጫውን አሸነፈ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

የስፖርት አጫጭር የውጭ ወሬዎች  (ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)

$
0
0

(ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ) (ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህብራዊ ሃያሲ)   ✅ ዊልያን ከኢንተርሚያሚ ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ ዊልያን የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለሦስት አመት ለክለቡ እንዲፈርም ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደርጓል። Daily Telegraph እንደገለፀው ዊልያን በሜጀር ሊግ ሶከር ተሳታፊ የሆነው የኢንተር ሚያሚ ክለብ ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በአውሮፓ ለመቆየት ፍላጎት ስላለው ነው ተብሏል። የ31 አመቱ ብራዚላዊ ተጨዋች ፤በቸልሲ ቤት ያለው ውል ከዚህ የውድድር አመት ፍፃሜ በኋላ ያበቃል።ዊልያን ከውድድሩ ፍፃሜ በኋላ ወደ አርሴናል ወይንም ወደ ቶትንሀም ይዛወራል ተብሎ ይጠበቃል። የእንግሊዙ ሌጀንድ ዴቪድ ቤከም ክለብ እንደሆነ የሚነገርለት ኢንተር ሚያሚ ዊልያንን ለማስፈረም ከፍተኛ ወጪ ለማውጣት ከወዲሁ ተዘጋጅቶ ነበረው። ✅ ፓሪስ ሴንት ዠርመን ራሽፎርድ ላይ ትኩረት አድርጓል የፓሪስ

The post የስፖርት አጫጭር የውጭ ወሬዎች  (ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ) appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

የለንደን ማራቶን በቀነኒሳ እና በኪፕቾጌ መካከል ሊካሄድ ነው

$
0
0

ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የለንደን ማራቶን በቀነኒሳ በቀለ እና በኬኒያዊው ኤሊውድ ኪፕቾጌ መካከል ጥቅምት 4 (እ.አ.አ) ይደረጋል። በዚህም ሁለቱ አትሌቶች የዓለም የማራቶን ክብረወሰንን ለማሻሻል የሚያደርጉት አልህ አስጨራሽ ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡ ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ እኤአ 2018 በርሊን ላይ (2:01:39 )በማስመዝገብ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስምግቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ በርሊን ማራቶን ላይ ( 2:01:41) በመግባት የኪፕቾጌን ክብረወሰን ለሁለት ሰከንድ ሳያሻሽል በመቅረቱ ሁለትኛው ፈጣኑ የማራቶን ሰዓት ባለቤት ነው፡፡ የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን 1፡00፡22 በማጠናቀቅ ቀደም ብሎ በሞ ፋራህ ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረ ወሰን ማሻሻሉ ይታወሳል። በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆነው 313 ሺህ ዶላር ለሽልማት መዘጋጀቱ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል። የለንደን

The post የለንደን ማራቶን በቀነኒሳ እና በኪፕቾጌ መካከል ሊካሄድ ነው appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.


ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ

$
0
0

የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ ብራሰልስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ13 ዓመታት በሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን አሻሻለ፡፡ በትውልድ ሶማሊያዊው የሆነው ሞ ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው በኃይሌን ተመዝግቦ የነበረውን 21 ነጥብ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው፡፡ የ37 ዓመቱ ሞ ፋራህ የውድድሩን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጠው አስተያየት የዓለም ክብ ረወሰን መስበር ከባድ መሆኑን አንስቶ ትናንት የተወዳደረበትም ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር መቆየቱን አንስቷል፡፡ ፋራህ ከማራቶን ከተመለሰ በኋላ ያስመዘገበው በመሆኑ በውጤቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ሞ ፋራህ ክብረ ወሰን በያዘበት በዚህ ውድድር ተወዳዳሪዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚያስመዘግቡት ርቀት ነው የሚያዘው፡፡ በሴቶች ኔዘርላንዳዊቷ ሲፈን ሐሰንም በተመሳሳይ

The post ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

በለንደኑ ማራቶን ያልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ ሹራ ቂጣታ አሸናፊ ሆኗል

$
0
0

በለንደኑ ማራቶን ሰፊ ግምት የተሰጠው ቀነኒሳ በቀለ በጤና እክል ከውድድሩ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደማይሳተፍ መታወቁ መነጋገሪያ የመሆኑን ያህል ኢትዮጵያ ተስፋ እንደሌላት የተቆጠረውን የለወጠው አዲሱ የማራቶን ጀግና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል። በዘንድሮው የለንደን 40ኛ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ጎርፍ መሆናቸውን ዳግም አስመስከረዋል። ኬንያዊው ብቻ ሁለተኛ ሲወጣ እስከ ስድስተኛ ያለውን ኢትዮጵያውያን አሸንፈዋል። በውጤቱም 1ኛ የወጣው ሹራ ቂጣታ ኢትዮጵያ 2:05.41 ሲያስመዘግብ ሁለተኛው ኬንያዊ ኪፕቹምባ 2:05.42 ሰዓት ገብቶዋል። ከሶስተኛ እድል ስድስተኛ ኢትዮጵያውያን ተቆጣጥረውታል። 3. ሲሳይ ለማ ኢትዮጵያ 2:05.45፣ 4. ሞስነት ገረመው ኢትዮጵያ 2:06.04፣ 5. ሙሌ ዋሲሁን ኢትዮጵያ 2:06.08፣ 6. ታምራት ቶላ ኢትዮጵያ 2:06.41:: የአትሌቲክስ መንደር እንዲህ በርከት ያሉ ጀግኖችን አፍርቶ ተስፋን አለምልሟል።

The post በለንደኑ ማራቶን ያልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ ሹራ ቂጣታ አሸናፊ ሆኗል appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች እንኳን ደስ አለን አጨራረሷን ተመልከት 🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጵያ አሸንፋለች Posted by Shems Alnur on Wednesday, October 7, 2020 ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች እንኳን ደስ አለን አጨራረሷን ተመልከት

The post ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች appeared first on ዘ-ሐበሻ: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ስኬታማ ጊዜ ካሳለፉ የውጭ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን በ23 ግቦች ካጠናቀቀ በኃላ ውስብስብ በሆኑ አወዛጋቢ ጉዳዮች ታክለውበት ወደ ግብፁ ኢስማኤል ቢያመራም እምብዛም የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡ ዳግም ከተመለሰ በኋላ የቀድሞው ክለቡን በስፋት ይቀላቀላል ቢባልም በርካታ ክለቦች እሱን ፈላጊ በመሆናቸው ወደ ጅማ የመዘዋወሩን ጉዳይ አጠራጣሪ  አድርጎት ቢቆይም በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል ሲል ኢትዮሶከር ዘግቧል:: በሌላ ስፖርት ዜና በ2010 በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ከተሾሙ በኋላ በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫው ውጤታማ የውድድር ጊዜ የነበራቸው እና በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ ውድድር ውጤት የራቃቸው አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ ዛሬ ከወላይታ ድቻ ጋር

The post ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

እንግሊዝ በርኒንግሃም ውስጥ በተደረገው ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ:: በሌላ በኩል አትሌት አልማዝ ሳሙኤል በ3,000 ሜትር ተወዳድራ በጥሩ ሰዓት አንደኛ በመውጣቷ የ2019 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ለመሆን በቃች:: – ዛሬ በመቀሌ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ባህርዳር ከነማን 1ለ0 አሸንፏል::  

The post ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ፡፡ የኡጋንዳው ካዎዎ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ተጨዋቹ ከአዲሱ ክለቡ ሽሬ ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል ተፈራርሟል፡፡ የውሉ መጠን በምስጢር እንዲያዝ የተወሰነ ቢሆንም ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ለፊርማ ከ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደተከፈለው ዘግቧል፡፡ ተጨዋቹ ከደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ ክለብ በመጀመሪያ ወደኢትዮጵያ የመጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመፈረም ነበር፡፡ በመቀጠል ከፋሲል ከነማ ጋር የሁለት አመት ውል ፈፅሞ ወደጎንደር ሊያመራ ችሏል፡፡   ተጨዋቹ ከፋሲል ከነማ ክለብ ጋር ያለው ውል ያልተጠናቀቀና አምስት ወር የሚቀረው ቢሆንም ለክለቡ ቤተሰባዊ ምክንያት አቅርቦ በስምምነት ስምምነቱ መቀደዱ ይታወቃል፡፡ 

The post ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

በ2011 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ክለባችሁ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በፋሲለደስ ስታዲየም ከወልዋሎ አ/ዩ ክለብ ጋር በነበረበት የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ ፡- 1. ከውድድሩ 4 ቀን ቀደም ብሎ የክለቡ አመራሮች ወደ እንግዳው ክለብ አመራሮች ስልክ በመደወል የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የማረፊያ ሆቴል ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ስለመሆኑ፡- 2. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም የእንግዳው ክለብ አባላት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ቁጥሩ በርካታ የሆነ የስፖርት ቤተሰብ አቀባበል አድርጎ ከፍተኛ አውቶቢስ በመመደብ ከአውሮፕላን ማረፈያው እስከ ሆቴል ድረስ በተመልካቾች ታጅቦ የተጓዘ ስለመሆኑ፡- 3. የቡድን አባላት ያረፉበት ሆቴል አካባቢ

The post የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.


ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እስከሚያገኝ ከፕሪምየር ሊጉ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ  ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡ ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡ አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣

The post ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እስከሚያገኝ ከፕሪምየር ሊጉ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሞሮኮ እግር ኳስ ፕሬዝዳንትን ከሠሠ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሦስተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ፋውዚ ሌክጃ፤ በፊፋ እውቅና የተሠጠውን በዓምላክ ተሰማ (ዳኛ) ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በሳለፍነው ሳምንት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን በግብፁ ዛማሌክ እና በሞሮኮው ቤርካኔ የእግር ኳስ ክለብ መካከል በተደረገው የፍፃሜ ዋንጫ ላይ በአምላክ ተሰማ የመሐል ዳኛ ሆነው በመሩበት ጨዋታ የግብፁ ዛማሌክ አሸናፊ ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም፣ በሜዳሊያ ሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ ግን የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የትውልድ አካባቢቸውን የሚወክልላቸው እና የሚደግፉት ቤርካኔ መሸነፉን ተከትሎ የበአምላክን ጭንቅላት ጉልበት በተሞላበት ሁኔታ እንደመቷቸው እና በኋላም በፀጥታ ኃይሎች አማካይነት ዳኛው እንደተረፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ጥቂት ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ዳኞች

The post የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሞሮኮ እግር ኳስ ፕሬዝዳንትን ከሠሠ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ዳሬ ሰላም ገብቷል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

ቡድኑ ዳሬ ሰላም ሲደርስ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ እና ሌሎች አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም አዛምን 1ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ነሃሴ 18 የመልሱ ጨዋታ ዳሬ ሰላም ላይ ከአዛም ጋር የሚያደርገው ፋሲል ከነማ ለጨዋታው በአዲስ አበባና ባህርዳር ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይ ቡድኑ ባህርዳር ላይ ያደረገውን ጨዋታ አሸናፊ ያደረገውን ግብ ያስቆጠረው በዛብህ መለዮ በመልሱ በጉዳት ምክንያት ጨዋታ አይሰለፍም፡፡ በሌላ በኩል በባለፈው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ የወጣው ግብ ጠባቂው ሚካኤል ሳማኪ ከጉዳቱ በማገገሙ ተሰላፊ ይሆናል ተብሏል፡፡ @AmharaSport

The post ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ዳሬ ሰላም ገብቷል appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ድባብ –ዋልያዎቹ ከሌሴቶ ያደርጉት ጨዋታ -ታርቆ ክንዴ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

“90 ደቂቃ ያለእረፍት ከጎናችን በመሆን ያበረታንን ደጋፊ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ “በቴክኒካል አቅሙ ከፍ ያለ እና ጥሩ ቡድን የገነባውን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ፡፡” አሰልጣኝ ታቦ ሴኔንግ ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የሌሴቶ አቻውን በማስተናገድ የጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ያለምንም ግብ ተለያይቷል፡፡ ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ “ከምንግዜውም በተሻለ ጥሩ ተጫውተናል፤ በርካታ የግብ እድሎችንም መፍጠር ችለናል፤ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ የመጣው የአጥቂ መስመር ክፍተት ጎል ሳናስቆጥር እንድንወጣ አድርጎናል” ብሏል፡፡ በቀጣይ ጊዜ ግብ የማስቆጠር ችግራችን ለመቅረፍ በርትተን እንሰራለንም ብሏል አሰልጣኙ፡፡ ተጫዋቾቼ 90 ደቂቃ

The post የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ድባብ – ዋልያዎቹ ከሌሴቶ ያደርጉት ጨዋታ -ታርቆ ክንዴ appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የመጀመሪያው ልዑክ ዶሃ ገብቷል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

ባሕር ዳር፡ መስከረም 14/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኳታር አስተናጋጅነት የፊታችን ዓርብ መስከረም 16/2012 ዓ.ም 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ይጀመራል፤ በዚህ ውድድር የሚሳተፉ የስፖርት ልዑካን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ልዑክ ኳታር ዶሃ መግባቱ ነው የተገለጸው። የአትሌቲክስ ልዑኩ ከሌሊቱ 8፡00 ላይ በዶሃ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ እና በኳታር የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካርያ አቀባበል አድርገውለታል። ኢትዮጵያ በሻምፕዮናው በመካከለኛ፣ በረጅም ርቀት እና በሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድሮች ትሳተፋለች። በወጣው የውድድር መርሀ ግብር መሠረት ከዓርብ መስከረም 16/2012 ዓ.ም ጀምሮ አትሌቶች የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድራቸውን ያደርጋሉ። በሴቶች ማራቶን አትሌት ሮዛ

The post በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የመጀመሪያው ልዑክ ዶሃ ገብቷል appeared first on ዘ-ሐበሻ - Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

Viewing all 419 articles
Browse latest View live