ትላንት በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ የተቋረጠው የቅዱስ ጊዮርጊስና የሃዋሳ ከነማ ጨዋታ ዛሬ በዝግ ስታደየም ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ግጥሚያም ሁለቱም ክለቦች ምንም ጎል ሳያስቆጥሩ ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል፡፡ ሀዋሳዎች አንጫወትም ብለው ወደሃዋሳ ጉዞ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ካልተጫወቱ ፎርፌ እንደሚሰጥ በማስታወቁ ከዝዋይ ተመልሰው እንደተጫወቱ ለመረዳት ችለናል፡፡
↧