Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ

$
0
0

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ፡፡ የኡጋንዳው ካዎዎ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ተጨዋቹ ከአዲሱ ክለቡ ሽሬ ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል ተፈራርሟል፡፡ የውሉ መጠን በምስጢር እንዲያዝ የተወሰነ ቢሆንም ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ለፊርማ ከ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደተከፈለው ዘግቧል፡፡ ተጨዋቹ ከደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ ክለብ በመጀመሪያ ወደኢትዮጵያ የመጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመፈረም ነበር፡፡ በመቀጠል ከፋሲል ከነማ ጋር የሁለት አመት ውል ፈፅሞ ወደጎንደር ሊያመራ ችሏል፡፡   ተጨዋቹ ከፋሲል ከነማ ክለብ ጋር ያለው ውል ያልተጠናቀቀና አምስት ወር የሚቀረው ቢሆንም ለክለቡ ቤተሰባዊ ምክንያት አቅርቦ በስምምነት ስምምነቱ መቀደዱ ይታወቃል፡፡ 

The post ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles