የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሦስተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ፋውዚ ሌክጃ፤ በፊፋ እውቅና የተሠጠውን በዓምላክ ተሰማ (ዳኛ) ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በሳለፍነው ሳምንት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን በግብፁ ዛማሌክ እና በሞሮኮው ቤርካኔ የእግር ኳስ ክለብ መካከል በተደረገው የፍፃሜ ዋንጫ ላይ በአምላክ ተሰማ የመሐል ዳኛ ሆነው በመሩበት ጨዋታ የግብፁ ዛማሌክ አሸናፊ ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም፣ በሜዳሊያ ሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ ግን የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የትውልድ አካባቢቸውን የሚወክልላቸው እና የሚደግፉት ቤርካኔ መሸነፉን ተከትሎ የበአምላክን ጭንቅላት ጉልበት በተሞላበት ሁኔታ እንደመቷቸው እና በኋላም በፀጥታ ኃይሎች አማካይነት ዳኛው እንደተረፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ጥቂት ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ዳኞች
The post የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሞሮኮ እግር ኳስ ፕሬዝዳንትን ከሠሠ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.