Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all 419 articles
Browse latest View live

Sport: አንቶኒ ማርሻል –አዲሱ የቀይ ሰይጣኖቹ አለኝታ

$
0
0

antony Marcial

ማንችስተር ዩናይትድ ለአንቶኒ ማርሻል ግዥ 38 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብን ለሞናኮ ሲከፍል ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል የእብደት ተግባርን የፈፀሙ ተደርገው በአንዳንዶች ተቆጥሮባቸው ነበር፡፡ ለአንድ የ19 ዓመት ወጣት 36 ሚሊዮን ፓውንድ እጅግ ውድ የሚባል ዋጋ ነው የሚል አስተያየትን የሰጡ ወገኖችም በርካታዎች ሲሆኑ ታይተዋል፡፡ በግሩም የአጨራረስ ብቃት ሁለት ጎሎችን በሳውዝ ሀምፕተን መረብ ላይ ለማሳረፍ መቻሉ ቫንሃል ትክክለኛውን ውጤታማ የአጥቂ መስመር ተጨዋችን ማግኘታቸውን ያረጋገጠላቸው ሆኗል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በሴንት ሜሪ ስቴዲየም ሳውዝሀምፕተንን 3ለ2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ በቻለበት ግጥሚያ ከመረብ ያሳረፋቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎች በስሙ ያስመዘገቧቸው ጎሎቹን ብዛት ሶት በማድረስ የኦልድ ትራፎርድ የፉትቦል ህይወቱን ባማረ ሁኔታ ለመጀመር ችሏል፡፡ ማርሻል ለማንችስተር ዩናይትድ ሶስቱን የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን ለማስቆጠር የፈጀበት ለ80 ደቂቃዎች ብቻ በሜዳ ላይ መቆየት ነው፡፡

በአንፃሩ ራዳሜል ፉልካኦ ባለፈው ሲዝን ሙሉ ሲዝንን ለማንችስተር ዩናይትድ በስሙ ያስመዘገባቸው ጎሎች ብዛት አራት ብቻ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሉዊ ቫንሃል ማንም ባልገመተው መልኩ የቡድናቸው ጎሎችን የማስቆጠር ችግርን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ ኃይል ያለው አስገራሚ ወጣትን ማግኘት መቻላቸውን ነው፡፡ ከዝውውሩ ወዲህ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3ለ1፣ እንዲሁም ሳውዝሀምፕተንን 3ለ2 በረታበት ሁለት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከመረብ ያሳረፋቸው ሁሉም ሶስት ጎሎች በግሩም የአጨራረስ ብቃት ከመረብ የተገናኙ በመሆናቸው በ19 ዓመቱ ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል አጥቂ ብቃት የፉትቦሉ አለም አግራሞቱን በመግለፅ ላይ ነው፡፡

በሴንት ሜሪ በተደረገው ግጥሚያ ሁን ማታ ያስቆጠራት ሌላኛዋ ጎል በሜዳ ላይ የነበሩት ሁሉም የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾችን ባሳተፈ መልኩ በ45 ፓሶች በሜዳ ላይ የነበሩትን ሁሉንም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾችን ባሳተፈ መልኩ ቢሆንም የሁሉም ታዋቂ የፉትቦል ተንታኞችን ልዩ ትኩረት የሳበው ግን አንቶኒ ማርሻል የወጣበት ውድ ዋጋ ምንም አይነት ተፅዕኖ ሳይፈጥርበትና በማንቸስተር ዩናይትድ የፊት አጥቂ መስመር መሰለፍ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ጫናን በመቋቋም ከወዲሁ ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን ከመረብ ለማሳረፍ መቻሉ ነው፡፡

በማርሻል ዙሪያ አስተያየታቸውን ከሰነዘሩት የፉትቦል ተንታኞች ውስጥ የቀድሞው የሊቨርፑል ዝነኛ ግርሃም ሶውነስ ‹‹ሰፊ ልምድን ከማጣቱ በስተቀር ሁሉንም አይነት ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ አስገራሚ ወጣት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በተለይም ከፍተኛ ፍጥነቱና እውነተኛ የሆነ የሰውነት ጥንካሬን መላበሱ አስገራሚ ሆኖብኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ለማንቸስተር ዩናይትድ በተሰለፈባቸው ሁለት ግጥሚያዎች ያደረጋቸው ሶስቱንም አላማቸውን የጠበቁ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎችን ከመረብ ማሳረፉ ያማረ የጎል አጨራረስ ብቃትን መላበሱን የሚያሳይ ነው›› በማለት ፈረንሳዊው ወጣት አጥቂን አድንቆታል፡፡

የማንችስተር ዩናይትዱ የቀድሞ ዝነኛ አምበል ጋሪ ኔቭል በበኩሉ ‹‹ሉዊ ቫንሃል ለአንቶኒ ማርሻል ግዥ ውድ ዋጋ መክፈላቸው አስገራሚ ሆኖብኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአንድ ሲዝን ሌላው ቀርቶ እስከ 15 የሚደርስ ጎልን ማስቆጠሩ አጠራጣሪ ሆኖብኝ ነበር፡፡ በተግባር ያየነው ግን ማርሻል ማንችስተር ዩናይትድን ብዛት ያላቸው ጎሎችን ለማሳፈስ የሚያስችለው ትክክለኛው የአጥቂ መስመር ተጨዋች መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ አባባሌ አንዱ ምክንያት የሆነኝ ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን በተጋነነ መልኩ የመግለፅ ባህል የሌለው መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ባህል ያላቸው ተጨዋቾች ብዙውን ጊዜ የራስ የመተማመን መንፈሳቸው እጅግ ያማረ ሲሆን መታየቱ የተለመደ ነው›› የሚል አስተያየቱን በመሰንዘር ሉዊ ቫንሃል ማርሻልን በዝውውር መስኮቱ መጨረሻ ቀን የገዙበት ተግባራቸውን አድንቆላቸዋል፡፡

(ይህ ስታትስቲክስ ከ3 ሳምንት በፊት የነበረና የትናንት ምሽቱን የቻምፒዪንስ ሊግ ጨዋታ አይመለከትም)

የአንቶኒዮ ማርሻል የእስካሁኑ የሲዝኑ የፕሪሚየር ሊግ የቁጥር መረጃዎች

80- በሜዳ ላይ የቆየባቸው የፕሪሚየር ሊግ ደቂቃዎች

4- ያደረጋቸው አጠቃላይ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎች

3- አላማቸውን ያገኙለት የጎል ሙከራዎችና ያስቆጠራቸው የሊጉ ጎሎች

አንቶኒ ማርቫል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተሰለፈባቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት የሊጉ ግጥሚያዎች በእያንዳንዱ ላይ ጎልን በማስቆጠር ታሪክ ሶስተኛው የማን ዩናይትድ ተጨዋች ሆኗል፡፡ ሌሎቹ ሉዊስ ሳህና ፍሬዲሪኮ ሜኬዳ ናቸው፡፡

ማርሻል በእስካኑ ሲዝን ያስቆጠራቸው 3 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎች የቼልሲዎቹ ኤደን ሃዛርድ፣ ዲያጎ ኮስታና ፔድሮ በድምሩ በስማቸው ካስመዘገቧቸው ጎሎች ብዛት ጋር እኩል ናቸው፡፡

The post Sport: አንቶኒ ማርሻል – አዲሱ የቀይ ሰይጣኖቹ አለኝታ appeared first on Zehabesha Amharic.


Sport: ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ያስቆጠረቻቸውን 2 ጎሎች ይዘናል (Video)

$
0
0

‪በፓፓ‬ ኒው ጊኒ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮና አፍሪካን ወክሎ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረጉት ጨዋታ 2-2 በአቻ ውጤት ተያይተዋል። ሁለቱንም ጎሎች ያገባችው የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ኮከብ ጎል አግቢ የሆነችው ሎዛ አበራ ናት:: ጎሎቿን ይመልከቱ:: የመልሱ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኃላ አክራ ጋና ይደረግና በደርሶ መልሱ አጠቃላይ ውጤት አሸናፊው አገር አፍሪካን ወክሎ በአለም ዋንጫ የሚሳተፍ ይሆናል።

u20 ethiopia
loza

The post Sport: ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ያስቆጠረቻቸውን 2 ጎሎች ይዘናል (Video) appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ሜሲ!!! የእግርኳሱ መሲህ

$
0
0

 

UEFA Champions League 2014/15 Round of 16 Second Leg Barcelona v Manchester City Camp Nou, Barcelona, Spain - 18 Mar 2015

ባርሴሎና ባለፈው በቻምፒዮንስ ሊጉ ሮም ኦሎምፒክ ላይ ከሮማ ጋር 1-1 በተለያየበት ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በቀዩ እና ሰማያዊው ማልያ 100ኛ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ፈፅሟል፣ አርጀንቲናዊው በውድድሩ 80 ጎሎችን ካስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ በ77 ጎሎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

አራት ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያነሳው የ27 ዓመቱ ሜሲ የመጀመሪያ ድሉ በ2009 በሮም ኦሎምፒኮ ያሳካው ነበር፣ በጨዋታው ሊዮኔል ከዣቪ ኸርናንዴዝ የተሸጋገረለትን የአየር ላይ ኳስ ወደ ጎልነት ለውጦ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል፤ ጨዋታውም 2-0 ተጠናቅቋል፡፡

በ2011 ባርሴሎና ማንችስተር ዩናይትድን 3-1 በረታበት ጨዋታ ሜሲ አንድ ጎል አስቆጥሯል፣ በዌምብሌይ ኳስ እና መረብን ያገናኘው አጭሩ አጥቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ቡድኑ በተመሳሳይ ጁቬንቱስን 3-1 ሲያሸንፍ ጎል ማስቆጠር አልቻለም፡፡

ሊዮ ባርሴሎና በ2006 በፓርክ ደ ፕሪንስ አርሰናልን 2-1 አሸንፎ ከ1992 በኋላ ታላቁን ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ አባል የነበረ ቢሆንም በግማሽ ፍፃሜው በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሳይሰለፍ ቀርቷል፡፡

የአራት ጊዜ የወርቅ ኳስ ተሸላሚው የሆነው ኮከብ በቻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ዲሴምበር7 2007 ባርሴሎና በዶኔስክ ከሻክታር ጋር ባደረገው ጨዋታ ነበር፣ አሰልጣኝ ፍራንክ ራይካርድ ቀድሞ ከምድብ ማጣሪያ ማለፉን ያረጋገጠውን ቡድን በቋሚ ተሰላፊዎች ከመጠቀም ይልቅ አዳዲስ ፊቶችን ለመመልከት በነበረው ፍላጎት ሜሲን ከተጠባባቂ ወንበር አንስቶ ለማጫወት እቅድ ነደፈ፣ የካታላኑ ክለብም በጨዋታው 2-0 ለመሸነፍ ተገደደ፡፡

ሊዮ በቻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው ኖቬምበር 2/2005 ነበር፣ በኑካምፕ ባርሴሎና የግሪኩን ፓናቲናይኮስን 5-0 በረታበት ጨዋታ ሶስተኛውን ጎል አግብቶ በታላቁ መድረክ የጎል አካንቱን ከፈተ፡፡

በቻምፒዮንስ ሊጉ 100ኛ ጨዋታውን የፈፀመው የግራ እግሩ አጥቂ በውድድሩ አምስት ጊዜ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ሲፈፅም 48 ጎሎችንም አስቆጥሯል፤ ይህ በሁለት ጨዋታ አምድ ጎል የማስቆጠር ያህል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በአንድ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረባቸው ጨዋታዎች 16 ደርሰዋል፤ በሶስት አጋጣሚዎች ሃትሪክ ሰርቷል፡፡ ከምንም በላይ በ2010/11 የውድድር ዘመን ግማሽ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ባየርን ሙኒክ ላይ በኑ ካምፕ ያስቆጠራቸውን ሁለት ጎሎች መቼም ቢሆን አይዘነጋም፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተጨማሪ የማይረሳቸው አጋጣሚዎች ተከስተዋል፡፡ በ2011/12 የውድድር ዘመን ሁለተኛው ዙር ላይ ባርሳ ባየር ሌቨርኩሰን ላይ ሰባት ጎሎችን ሲያስቆጥር (ጨዋታው 7-1 ተጠናቅቋል) ሜሲ አምስት ጎሎችን አግብቶ ነበር፣ ባለፈው ዓመት የሻክታር ዶኔስኩ አጥቂ ሉዌስ አድሪያኖ በባቴ ቦርሶቭ ላይ ተመሳሳይ የጎል መጠን እስኪያስቆጥር ድረስ የባርሴሎናው ልጅ ሪከርዱን በብቸኝነት ይዞ ነበር፡፡

በ2009/10 የውድድር ዘመን በቻምፒዮንስ ሊጉ በአንድ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረበት ወቅት ነበር፡፡ በኢምሬትስ ከአርሰናል ጋር 2-2 የተለያየው ባርሳ በኑካምፕ የሰሜን ለንደኑን ክለብ 4-1 ሲያሸንፍ የላ ሜሲያው ግኝት የተጋጣሚ ቡድን ተከላካዮችን እጅግ በጣም አሰቃይቶ አራቱንም ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ይህንን ሲፈፅም እግርኳስን ተንከባክቦ እና ውበትን ጨምሮ ተጫውቷል፡፡

‹‹ሊዮኔል በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ይፈልጋል›› ይላል ከ2008-2010 ድረስ በባርሴሎና አብሮት የተጫወተው አጥቂው ቲዮሪ ሆንሪ፣ ‹‹በኮፓ ዴል ሬይ ከመጀመሪያው ዙር ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ መጫወት ይሻል፡፡ በልምምድ ሜዳ ላይ እንኳን ማሸነፍ እንጂ ሽንፈት አይፈልግም፡፡ በአንድ የጨዋታ እንቅስቃሴ ጥፋት ከተፈፀመበት ከራሱ ግብ ጠባቂ ኳስ እንዲሰጠው በትህትና ጠይቆ ከፊቱ የሚገኙትን ተጨዋቾች በሙሉ አልፎ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ይፈልጋል፡፡ ተጋጣሚው ጎል በማስቆጠር በድጋሚ ጨዋታውን ሲጀምር ድንገት ኳስ ይነጥቅና ተጨማሪ ጎል ያገባል፣ የእርሱ ቡድን እስኪያሸንፍ ድረስ ይህንን ደጋግሞ ይፈፅማል፡፡ የዚህ አይነት ተጨዋች ከዚህ ቀደም ገጥሞኝ አያውቅም››

በእርግጥም ሜሲ የእግርኳስ ‹‹ሊቅ›› ነው፣ ኧረ እንዲያውም በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚገኝ ታላቅ ተጨዋች መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ብቃቱ ማቆሚያ ያለው አይመስልም፣ እርሱን የሚያውቁ ይህንን ይመሰክራሉ፣ ነገሩ የተጋነነ አይደለም፣ የተጋነኑ የሚመስሉ አስተያየቶችን መስጠትም ፍትህን ማዛባት አይሆንም፡፡

‹‹የፕላኔታችን ምርጡ ተጨዋች›› የሚል ማሞካሻን ያገኘው እንዲሁ አይደለም፣ እስካሁን በነበረው የእግርኳስ ህይወት የነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እና ሪከርዶቹ ከግምት ውስጥ ገብተው ነው፣ የዚህ ሁሉ ምስጢር ምን ይሆን?

‹‹ሪከርዶቼን ወደ ኋላ መለስ ብዬ አልመለከትም፤ አሁንም ድረስ እግር ኳስን እየተጫወትኩኝ የምገኘው ለዚህ ነው፡፡ እርግጥ ነው በእኔ ቦታ ላይ የሚጫወት የትኛውም ተጨዋች ጎሎችን ማስቆጠር ይሻል፤ የእኔ ቀዳሚ ግብ ዋንጫዎችን ማንሳት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የሚያነሳሳኝ ዋንጫ ነው፤ ዋንጫዎችን ማንሳት ተነሳሽነት ይፈጥርብኛል፤ እንደ ቡድን ከዚህ የተሻለ ነገር ማግኘት አይቻልም›› ይላል፡፡

በዚህ ደረጃ የሚገኝ ተጨዋች ከግል ሽልማት ይልቅ በቡድን ለሚገኝ ስኬት ቅድሚያ ሲሰጥ መመልከት ያስደስታል፡፡ ተጨዋቹ በ90ሺ ወይም 90 ተመልካቾች ፊት ቢጫወት ሁልጊዜም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ዋንጫዎችን ለማንሳት ነው፡፡

‹‹ተነሳሽት ለማግኘት አልቸገርም፤ እግርኳስን መጫወት እወዳለሁኝ፤ በልምምድ ሜዳ ላይ መገኘት ያስደስተኛል፡፡ በዚህ አይነት መልኩ በየዕለቱ የማሳልፈው ነገር ደስታ ይሰጠኛል፤ አንድ ስኬት ስታገኝ ተጨማሪ ድሎችን ደጋግመህ ማሳካት ትፈልጋለህ›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ኮከብ ‹‹ልምምድም ይሁን ጨዋታ አልያም ዋንጫዎችን ማንሳት ያስደስተኛል፡፡ ምርጡ ህይወቴ እነኚህ ናቸው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ከቡድኔ ጋር ዋንጫዎችን ማንሳት እፈልጋለሁኝ፤ በቃ ይኸው ነው›› ይላል፡፡

‹‹ወርልድ ክላስ›› ተጨዋቾችን ከሌሎች መደበኛ ተጨዋቾች የሚለያቸው የድል ረሃብ ስሜታቸው ነው፤ በየጊዜው ዋንጫዎችን ለማንሳት ያላቸው ፍላጎት በድል ላይ ድል እንዲደግሙ ያስችላቸዋል፡፡

እርግጥ ነው 2014 ለሜሲ አስደሳች አልነበረም፡፡ በላ ሊጋው የመጨረሻ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ የገባው ባርሴሎና 1-1 ተለያይቶ በመጨረሻም ዋንጫውን ተነጥቋል፤ በቻምፒዮንስ ሊጉ በዲያጎ ሲሞኒ ቡድን ሩብ ፍፃሜ ላይ ሽንፈትን አስተናግዶ ረጅም ርቀት መጓዝ አልቻለም፣ በዓለም ዋንጫው ደግሞ አርጀንቲና በፍፃሜው ጨዋታ በጀርመን 1-0 ተሸንፋ ከ1986 በኋላ ይህንን ዋንጫ ለማንሳት የነበራት ዕድል ሳይሳካ ሲቀር ሊዮ በግሉ ከፍ ያለ ትችት አስተናግዷል፡፡

2015 ዓመት ግን የእርሱ ነበር፡፡ በግልም ሆነ እንደ ቡድን ከፍ ያለ ስኬትን አስመዝግቧል፡፡ ‹‹በዓለም ዋንጫ ለፍጻሜ ቀርቦ ሽንፈትን ማስተናገድ ጥሩ የሆነ ስሜትን አይፈጥርም፣ ለአገሬ ታላቁን ዋንጫ ማስገኘት እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ከመጥፎ አጋጣሚ በማገገም ወደፊት መጓዝ ተገቢ ነው›› የሚል አስተያየትን ሰጥቶ ‹‹እንደ እግርኳስ ተጨዋች ሽንፈትን ካስተናገድክ በኋላ በቀጣይ የሚገጥምህን ፈተና በብቃት በመወጣት መጥፎውን አጋጣሚ መርሳት ምርጥ አማራጭ ነው፤ የዓለም ዋንጫው መጥፎ አጋጣሚ ጥሩ ስሜት እንደማይፈጥር ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ብስጭቱ ለድል ያነሳሳይል፡፡

ሊዮ የተናገረውን ነገር በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሚገባ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ የላ ሊጋውን ዋንጫ ለማንሳት ባልተቸገረው ባርሴሎና ሜሲ በርካታ ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ለማንሳት አልተቸገረም፡፡ ከምንም በላይ በበርሊን ጁቬንቱስን 3-1 አሸንፎ ሻምፒዮን ሆኗል፤ በእነኚህ ድሎች የአጭሩ ኮከብ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነበር፡፡

ለባርሴሎና ያለፈው ዓመት አስደሳች ነበር፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት በመሆን በስፔን ብቸኛው ክለብ ሆኗል፡፡ በ2009 በፔፕ ጋርዲዮላ እንዲሁም ባለፈው ዓመት በሉዊስ ኤንሪኪ ይህንን ስኬት ሊጎናፀፍ ሊዮ የሁለቱም ቡድን መሪ ተዋናይ ነበር፡፡

እርግጥ ነው በባርሴሎና ያለፈው ዓመት ታሪካዊ ስኬት አርጀንቲናዊውን ብቻ አጉልቶ መጥቀስ ሌሎቹን መናቅ ይሆናል፤ ሉዊስ ሱዋሬዝ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ታላቅነቱን አስመስክሯል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ጭንቀት ላይ ለነበረው የካታላኑ ክለብ ኳስ እና መረብን አገናኝቶ ቡድኑን ከጭንቀት መገላገሉ እንዴት ይረሳል? ሶስተኛውን ጎል አግብቶ የቡድኑን አሸናፊነት ያረጋገጠው ኔይማርስ እንዴት ይዘነጋል?

ሶስቱ አጥቂዎች ባለፈው ዓመት በሁሉም ውድድሮች በጋራ 119 ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ ይህ አስገራሚ ሪከርድ ነው፤ በላ ሊጋው 81 ጎሎችን አግብተዋል፡፡ ባየርን ሙኒክ በተመሳሳይ ወቅት በቡድን ደስ ሊጋው 80 ጎሎችን አግብቷል፤ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ቼልሲ 73 እንዲሁም የሴሪ አው አሸናፊ ጄቬንቱስ 70 ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

‹‹በጣም ዕድለኛ ነኝ›› ይላል- ሊዮ፣  ባለፈው ዓመትም ከታላቅ አጥቂዎች ጎን ተሰልፎ ተጫውቻለሁኝ- ከሮናልዲንሆ ጋር ድንቅ የሆነ መግባባት ነበረኝ፡፡ ከእርሱ በኋላ ደግሞ ከሳሙኤል ኤቶ፣ ቲዮሪ ሆንሪ፣ ፔድሮ፣ ዴቪድ ቪያ እና አሌክሲስ (ሳንቼዝ) ጎል ተሰልፌ በመጫወት አስደሳች ጊዜያትን አሳልፌያለሁኝ፡፡

‹‹ከምንም በላይ ከኔይማር እና ሱዋሬዝ ጋር የፈጠርኩት ጥምረት የተለየ ነው፤ ሁለቱ አጥቂዎች የብቃታቸው ጫፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጋራ የተጫወትነው ለአንድ ዓመት ብቻ ቢሆንም ጥምረታችን በጣም ይገርማል፡፡ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ጥምረት መፍጠር እንደምንችል አልጠራጠርም፡፡ ቅድሚያ የምንሰጠው ለቡድን ሥራ ነው፡፡ ኔይማር ባለው ኳሊቲ፣ የኳስ ንክኪ እና አካል ብቃት የዓለማችን ምርጡ ተጨዋች መሆን ይችላል፡፡ ሉዊስ (ሱዋሬዝም) ተመሳሳይ ነው፤ የኳስ ቁጥጥሩ፣ እይታው፣ እንቅስቃሴው፣ ደሙ ነፍሳዊ አጨዋወቱ በአጠቃላይ የማይታመን ነው፡፡ ሁላችንም የተለያዩ ግብአቶችን እናበረክታለን››

ምናልባት አሁን ባለው ሁኔታ ከሜሲ ቀድመው ሊቀመጡ የሚችሉት ፔሌ እና ዲዮጎ ማራዶና ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከ2003 ጀምሮ ለባርሴሎና መሰለፍ የጀመረው ይህ ኮከብ ዕድሜው ገና 27 መሆኑን አምኖ መቀበል ያስቸግራል፡፡

ስኬቱን ልዩ የሚያደርገው ዘመናዊው እግርኳስ በአካል ብቃቱ ረገድ ወደላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩ፣ ታክቲካዊ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑ፣ ክፍተቶችን ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ እንዲሁም መከላከል ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ያም ቢሆን ሁሉም ነገር ለዚህ ተጨዋች ከባድ አልሆነም፡፡

በዚህ ዘመን ለፈጣሪ ተጨዋቾች ከፍተትን ማግኘት ፈታኝ ቢሆንም ሜሲ ግን ሳይቸገር የሚፈልገውን ነገር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡ ኧረ  እንዲያውም ከእያንዳንዱ ጨዋታ ስኬት አልፎ አራት ጊዜ የወርቅ ኳስ በማግኘት በግሉ ሪከርዱን በእጁ አስገብቷል፡፡

ባለፉት 11 ዓመታት ለባርሴሎና እና አርጀንቲና በጋራ 311 ጨዋታዎች ፈፅሟል፤ በስድስት ትልልቅ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ ሆኗል፡፡ በእነኚህ ጊዜያት 591 ሺ 626.4 ማይል ተጉዟል፤ በአራት የተለያዩ አህጉት 1061 ሰዓታት በርሯል፡፡ በአጠቃላይ 44 ቀናት በጉዞ አሳልፏል፡፡ በሌላ አነጋገር መሬትን 23.9 ጊዜ ዞሯል፡፡

‹‹የብራዚሉ ሮናልዶ የልጅነት አርአያዬ ነበር፣ ለባርሴሎና እና ብራዚል የማይታመን ነገር ሰርቷል፡፡ ከእርሱ የበለጠ ተሰጥኦ የታደለ አጥቂ አልተመለከትኩም፣ የሚገርም ተሰጥኦ ባለቤት ነው፤ ሁሉም ሰው ይህንን መመልከት ይችላል፣ ከምንም ነገር ተነስቶ ጎሎችን ያስቆጥራል፣ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች አስገራሚ ነበሩ፡፡ ከሜዳ ውጭም ቢሆን ድንቅ ሰው ነበር፤ ዚኔዲን ዚዳንንም መጥቀስ አለብኝ፤ እርሱ ሲጫወት መመልከት ያስደስተኝ ነበር፡፡ የፈረንሳውያን ጀግና ነው፤ ከሜዳ ውጭም ቢሆን በአስደናቂ ስብዕና አለው›› የሚለው ሜሲ ነው፡፡

በኤንሪኬ ዘመን ሜሲ የቦታ ለውጥ አድርጓል፡፡ ወደ ኋላ ተመልሶ በአማካይ ቦታ ላይ እስከመሰለፍ ደርሷል፤ ሜሲን ወደፊት በአማካይ ቦታ ላይ ለመጫወት እቅድ አለህ? የሚል ጥያቄን ስታነቡበት ‹‹አዎን፤ ይህ እንደሚቻል ይሰማኛል፤ በርካታ ተጨዋቾች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ወደኋላ ተመልሰው ይጫወታሉ፤ በቀጣይ ወደ ኋላ ተመልሼ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች እንደምሆን ይሰማኛል፤ ከወዲሁ በአማካይ ቦታ በመጫወት በአማካይ ቦታ ላይ በመጫወት በርካታ ቦታዎችን አካልያለሁኝ፤ እንደ አጥቂ በፊት መስመር ላይ መጫወት ያስደስተኛል፤ በርካታ አጥቂዎች በጥልቀት ወደኋላ ተመልሰው በአማካይ ቦታ ላይ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወታቸውን ያራዝማሉ፤ ሁልጊዜም በሩጫ ላይ የተመሰረተ አጨዋወት መከተል አይቻልም የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

ከላ ሊጋ ክለቦች ሊዮ የፔፕ ጋርዲዮላውን ባየርን ሙኒክ መመልከት ያስደስተዋል፤ ‹‹ፔፕ ሁልጊዜም አዳዲስ ነገሮችን ይሞክራል፤ ይህ ለእግርኳስ አስደሳች ነገር ነው፤ በአውሮፐ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር በጣም ያስደስታል›› የሚል አተያየትን ሰጥቶ ‹‹እርሱን በተቃራኒ ወንበር ላይ ሲቀመጥ መመልከት የእንግዳ ስሜትን ይፈጥራል፤ በእግርኳስ ህይወቴ ስሜትን ይፈጥራል፤ በእግርኳስ ህይወቴ ላበረከተው አስተዋፅኦ በጣም ላመሰግነው እወዳለሁኝ፤ ሆኖም የእርሱን ቡድን በተቃራኒ ስገጠም የማስበው ማሸነፍን ብቻ ነው›› ይላል፡፡

የሜሲ ተሰጥኦ የዳበረው በልምምድ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ከባርሴሎና ተጨዋቾች መሀከል በልምምድ ሜዳ ላይ ታታሪው ማነው? የሚል ጥያቄ ስታስተከትሉበት ‹‹ይህንን መናገር ይከብዳል፤ ሆኖም ዣቪ እና ኢንዬስታን ማስቀደም አለብኝ፤ ለረጅም ዓመታት የዚህክለብ ልብ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በልምምድ ሜዳ እንደ እነርሱ አይነት ታታሪ ተጨዋቾች አልተመለከትኩም›› በማለት ይመልሳል፡፡

The post Sport: ሜሲ!!! የእግርኳሱ መሲህ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ማንቸስተር ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ – [ስታትስቲክስ –የቡድን ዜናዎች –ግምት –ጠቃሚ መረጃዎች]

$
0
0

key Battle
ከኤሊያና ሔኖክ

የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በዓመቱ ከሚጠበቁ አጓጚ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የማንቸስተር ደርቢ ነው:: ማን.ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ከሰዓታት በኋላ በትያትር ኦፍ ድሪምስ ይፋለማሉ:: በማንቸስተር ከተማ ከፍተኛ የሆነ የፖሊስ ጥበቃ አለ – ምክንያቱም ደጋፊዎች ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኋላ በሚያደርጓቸው አለመግባባቶች ከዚህ ቀደም በርከት ያለ ንብረት ጠፍቷልና ነው:: ዘ-ሐበሻ ይህን የማንቸስተር ደርቢን በማስመልከት የቡድኖቹን ፕሪማች (ከጨዋታ በፊት) ያሉትን ዜናዎች; መረጃዎች እና ስታስቲክሶች ታስቃኛችኋለች – መልካም ንባብ::

የጉዳት ዜናዎች:

ከማንቸስተር ዩናይትድ በኩል በዚህ ጨዋታ አሽሊ ያንግና ሉክ ሻው በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን ከሲቲ በኩል ዴቭድ ሲልቫ; ሰርጂዮ አጊዮሮ; ጋኤል ክሊሺ እና ሳሚር ናስሪ አይሰለፉም:: አምበሉ ቬንሰንት ኮምፓኒም በዚህ ጨዋታ ላይሰለፍ ይችላል እየተባለ ነው::

አሰልጣኞቹ ምን አሉ?

የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ልዊስ ቫንገሃል “የመጣሁት ከትንሽ መንደር ነው:: በዚያ መንደር ውስጥ ስለ ኳስ እጅጉን ይወራል:: በማንቸስተር ከተማ ግን ይለያል – ወሬው ስለዚህ ጨዋታ ነው:: ደጋፊዎች በጣም ስሜታዊ ሆነው ብዙ ነገሮችን ሲያደርጉ ይታያል:: ሲቲ በጣም ጠንካራና በፕሪምየር ሊጉ ካሉ ግምት ከሚሰጣቸው ቡድኖች ውስጥ አንዱ ነው:: ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ለኛ ትልቅ ነገር ነው” ብለዋል ከጨዋታው በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ::

የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሊግሪያኒ “ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የምናደርገው ይህ ጨዋታ 6 ነጥብ ጨዋታ አድርጌ ነው የምወስደው:: ይህ ጨዋታ ከተቀናቃኝህ/ተከታይህ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ ነው:: ግን የዚህ ጨዋታ ውጤት የሲዝንን አሸናፊ ይለያል ማለት አይደለም:: ሲቲ በጥሩ አቋም ላይ እንገኛለን – ፕሪምየር ሊጉን እየመራን ነው (አርሰናል ለጊዜው ይዞታል ዛሬ ቦታውን) – ይህ ማለት ጥሩ እንሆናለን ማለት ሳይሆን ከጨዋታ ጨዋታ ስህተቶቻችንን እያየን እናስተካክላለን ለማለት ነው:: በዚህ ትልቅ ጨዋታ ስህተት አለመስራት ትልቁ ግባችን ነው” ብለዋል ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት::

ግምት – ማን ያሸንፋል?

ታዋቂው የቢቢሲ ስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ይህን ጨዋታ ማን ያሸንፋል? ሲል የራሱን ግምት ሰጥቷል:: ይህን ተከትሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁማሩም ደርቷል:: ማርክ ላውረንሰን በሰጠው ግምት ሲቲ ሰርጂዮ አጉዬሮን እና ዴቭድ ሲልቫን ሳይዝ ገብቶ ማን.ዩናይትድን ያሸንፋል ብዬ አላስብም ብሏል:: እንደ ማርክ ላውረንሰን ግምት ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል::

እስካሁን ማን አሸነፈ?

ባለፉት 8 የፕሪምየር ሊግ ደርቢ ጨዋታዎች ሲቲ 6ቱን አሸንፏል:: ሲቲ ይህን ጨዋታ ካሸነፈ 50ኛውን ድል በማን.ዩናይትድ ላይ በመቀዳጀት ደስታውን እጥፍ ድርብ ያደርጋል::

ግምታዊ አሰላለፍ

ግምታዊ አሰላለፍ

ስታትስቲክስ:
ማንቸስተር ዩናይትድ ልዊስ ቫንገሃል ከያዙት ወዲህ ከ23ቱ የባለፉት ጨዋታዎች ውስጥ 17ቱን አሸንፏል:: 3 ጊዜ አቻ ሲወጣ የተሸነፈው 3 ጊዜ ነው::
ማን.ዩናይትድ ይህን ጨዋታ ካልተሸነፈ ከ2010 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳቸው በ5 የመጀመሪያ የመክፈቻ ጨዋታዎች ባለመሸነፍ ሪከርዳቸውን ያሻሽላሉ::
ዋይኒ ሩኒ 30ኛ ዓመቱን ይህ ጨዋታ ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት ደፍኗል:: ይህ አጥቂ 187 የፕሪምየር ሊግ ጎሎችን በማግባት በስሙ አስመዝግቧል:: ሩኒ በማንቸስተር ደርቢ ላይ 11 ጎሎችን በማግባት ብቸኛው የዩናይትድ አጥቂ ነው::

ማን.ሲቲ በዚህ ሲዝን በርካታ ጎሎችን ካገቡ የፕሪምየርሊጉ ክለቦች መካከል ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ:: 24 ጎሎችን ያስቆጠሩ ሲሆን 11ዱን ጎሎች ያገቡት ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ነው::
ማኑኤል ፔሊግሪያኒ የሚያሰለጥኑት ሲቲ ባለፉት 18 ጨዋታዎች ጎል ሳያስቆጥር አልወጣም::

ዘግየት ያሉ መረጃዎች ዴቭድ ሲልቫ በዚህ ደርቢ ጨዋታ ላይ የሚያሰልፈው ጤንነት ላይ ይገኛል ይላሉ::

እርስዎ ማን ያሸንፋል ይላሉ?

ግምትዎን ይስጡ

 

The most-eagerly awaited fixtures in the city’s football calendar, Manchester City and Manchester United have been playing each other since 1881. The first clash of the Reds and Blues’ 2014-15 season will be the 168th time they’ve met.

The post Sport: ማንቸስተር ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ – [ስታትስቲክስ – የቡድን ዜናዎች – ግምት – ጠቃሚ መረጃዎች] appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ራሂም ስተርሊንግ ‹‹በማንችስተር ሲቲ ስኬታማ እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ››

$
0
0

 

Raheem sterling

‹‹በዘመናዊ ፉትቦል እጅግ ተፈላጊው የአጥቂ መስመር ተጨዋች ነው›› በማለት የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ የገለፁት በ49 ሚሊዮን ፓውንድ ከሊቨርፑል የገዙትን የ20 ዓመቱን እንግሊዛዊ ራሂም ስተርሊንግን ነው፡፡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና በማንችስተር ሲቲ ታሪክ የውድ ዋጋ ግዥ የሆነው ስተርሊንግ በበኩሉ በአዲሱ ክለቡ ከሚገኑ ወርልድ ክላስ ፉትቦለሮች ጋር አብሮ ለመሰለፍ ያለው ጉጉት በእጅግ ከፍተኛ መሆኑን ያረጋገጠበት መግለጫን ሰጥቷል፡፡

ለበርካታ ሳምንታት የሚዲያውን ሰፊ ትኩረትን ስቦ የዘለቀው ስተርሊንግ ከአንፊልድ ወደ ኢትሃድ ያደረገው ዝውውር ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሆነው ተጨዋቹ ከማንችስተር ሲቲ የቀረበለት 180 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ የደመወዝ ክፍያን ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆኑ ነው፡፡ ማንቸስተር ሲቲ የአቡዳቢ ባለሀብቶች በሚመሩት ሼክ መንሱር ባለቤትነት በ2008 ከተገዛ ወዲህ ለስተርሊንግ የከፈለውን ጨምሮ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ ለ467 ተጨዋቾች ግዢ በድምሩ 719.1 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ አውጥቷል፡፡

በሼክ መንሱር ባለቤትነት 46ኛው የተጫዋች ግዥ ውልን የፈረመው ስተርሊንግ ለቀድሞው ክለቡ ሊቨርፑል በ129 ግጥሚያዎች ከተሰለፈ በኋላ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ለማምራት የወሰነበት ዋነኛ ምክንያቱ ሊቨርፑል ባቀረበለት የተጨማሪ ዓመታት ኮንትራት ውል ሊሰጠው ባቀደው 100 ሺ ፓውንድ የሳምንት ደመወዝ ደስተኛ ባለመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም ግን ስተርሊንግ ለማንቸስተር ሲቲ በይፋ በመፈረም በተቃራኒው አቅጣጫ ወደ ሊቨርፑል በነፃ ዝውውር የሄደው ሌላው እንግሊዛዊው ኢንተርናሽል ጀምስ ሚልነር ይለብሰው የነበረው 7 ቁጥር ማሊያን ከተረከበ በኋላ በሰጠው መግለጫው ዝውውሩን ያደረገበት ዋነኛ ምክንያቱ በሜዳ ላይ ካለው ፉትቦሉ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማመልከት ሞክሯል፡፡

‹‹የዝውውር ውሉ ከሚጠበቀው ጊዜ ቀደም ብሎ ተፈፃሚ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የደስታ መንፈስን አሳድሬያለሁ፡፡ ይህ ለእኔም ሆነ ለቤተሰቤ አባላት በጠቅላላ ትልቅ እፎይታን የፈጠረልን ጉዳይ ሆኗል›› ያለው ስተርሊንግ በመቀጠልም ‹‹ከሁሉም በላይ የእኔን ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው በርካታ ኳሊቲ ያላቸው ፉትቦለሮች የሚገኙበት የማንቸስተር ሲቲ ጠንካራ ስኳድ አንዱ አባል መሆን መቻሌ ነው፡፡ በስኳዱ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ከዚህ በፊት የትላልቅ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን የማግኘት ሰፊ ልምድን ያካበቱ በመሆናቸውም በማንችስተር ሲቲ ቆይታዬ እጅግ ተደናቂ ስኬትን ለማስመዝገብ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ካምፕ ለመጨረሻ ጊዜ በተገኘንበት ወቅት ጆ ኸርት የማንቸስተር ሲቲ ስላለው አጠቃላዩ እውነታ ምንነትን በጥንቃቄ አስረድቶኛል፡፡

በተለይ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ተደናቂነቱን ሲነግረኝ ወደዚህ ክለብ የመምጣት ውሳኔዬን እንድገፋበት ምክንያት ሆኖኛል፡፡ ወደዚህ እጅግ ትልቅ ክለብ ለመምጣት የቻልኩት ከኪው.ፒ.አር አንስቶ ለበርካታ ዓመታት ፉትቦሌን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር ሳደርገው በዘለቅኩበት ያለሰለሰ ጥረት ፍሬያማ ሆኜ በመሆኑ በራሴ ኩራትን የማላሳድርበት ምክንያት አይኖረኝም፡፡ ስኬታማ እንድሆን ከጎኔ ባለመለየት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍን ሲያደርጉልኝ ለዘለቁት ባለሙያዎች በጠቅላላ ያለኝ ምስጋናም ከፍተኛ ነው፡፡

በተለይም ራፋ ቤኒቴዝ ገና በ15 ዓመት ዕድሜዬ ለሊቨርፑል እንድፈርም በማድረግ ትልቅ ውለታን ሰርተውልኛል፡፡ ምክንያቱም ከኪውፒአር ወደ ሊቨርፑል መሸጋገር አጠቃላዩ የፉትቦል ህይወቴን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር የቻልኩበትን መሰረትን ያመቻችልኝ ሆኗል፡፡ ከዛ በኋላም ኬኒ ዳግሊሽ ለሊቨርፑል ዋናው ቡድን በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጫወት እድልን ሰጥቶኝ ሌላኛውን ትልቅ ውለታን አበርክተውልኛል፡፡

ብሬንዳን ሮጀርስም ለእኔ ብቃት ሙሉ እምነትን አሳድረው በመዝለቃቸው በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ በተለይም ሮጀርስ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በተደረገው ግጥሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሊቨርፑል ዋናው ቡድን በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጫወት ዕድልን በመስጠት መላው ዓለም ምርጥ ብቃቱን ለማየት እንዲችል ትልቅ አስተዋፅኦን ስላበረከቱልኝ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ በአጠቃላይ የሊቨርፑል ቆይታዬም ችሎታዬን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር የቻልኩበት በመሆኑ ለክለቡ ደጋፊዎችና አባላት የሚኖረኝ ክብር ከፍተኛ ሆኖ ይዘልቃል፡፡ ተስፋ የሚደረገውም የሊቨርፑል ደጋፊዎች ይህንን ዝውውርን ለማድረግ እንድወስን ምክንያት የሆነኝ ጉዳይ ምን እንደሆነ ጠንቅቀው ይረዱታል ብዬ ነው›› የሚል አስተያየቱን አክሏል፡፡

ስተርሊንግ ለሊቨርፑል ለመጨረሻ ጊዜ የተሰለፈበትን የ2014/15 ሲዝንን ያሳለፈው በ35 ግጥሚያዎች ተሰልፎ 7 ጎሎችን ብቻ በማስቆጠር ነው፡፡ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ማንቸስተር ሲቲ ለ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ ኢንተርናሽል ያወጣበት 49 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ በትክክል የሚመጥነው መሆኑ አጠራጣሪ ሲሆንባቸው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ስተርሊንግን የገዙበት የዋጋ መጠን ትክክለኛ መሆኑ በአዲሱ ሲዝን ተጫዋቹ ለቡድናቸው በሚኖረው ቁልፍ ሚና በትክክል እንደሚጋገጥ እርግጠኛ ሆነዋል፡፡

‹‹ራሂም ስተርሊንግ በአሁኑ ወቅት በዓለም ፉትቦል ከሚገኙት እጅግ የተዋጣለት ብቃት ካላቸው የማጥቃት ላይ ያተኮረ ውጤታማ እንቅስቃሴ ካላቸው ምርጥ ፉትቦለሮች አንዱ ነው፡፡ ለዚህ ምንም አይነት ጥርጣሬ ስለሌለኝም ክለባችን በውድ ዋጋ እንዲገዛው ባደረግኩት ውሳኔዬ ሙሉ ኃላፊነትን እንደምወስድለት ማረጋገጥ እወዳለሁ›› ያሉት ቺሊያዊው አሰልጣን በመቀጠልም ‹‹እርግጠኛ ሆኜ ለመናገር የምወደውም የማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች በዚህ ተጨዋች አስገራሚ ብቃት ገና ከመጀመሪያ ግጥሚያው አንስቶ ሙሉ ለሙሉ ደስተኛ የሚሆኑበት መሆኑን ነው፡፡ የዝውውር ውሉ ከወዲሁ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ መሆን መቻሉም ከሌሎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች ጋር በመሆን በአውስትራሊያና ወደ ሩቅ ምስራቅ በመጓዝ የምናደርገውን የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ጉዞ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የሚረዳው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ስተርሊንግ ከቡድናችን የጨዋታ ስታይል ጋር በፍጥነት ለመዋሃድ እንደሚችል ምንም አይነት ጥርጣሬ የለኝም›› የሚል አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ አንሄል ዲ ማሪያን እንዲሁም ቼልሲ ፈርናንዶ ቶሬስን ከገዛባቸው ውሎች ቀጥሎ ማንቸስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታሪክ ሶስተኛው ትልቅ ዋጋ የወጣበት ስተርሊንግ በበኩሉ ለአዲሱ ክለቡ ደጋፊዎች ባስተላለፈው መልዕክቱ ‹‹ማንቸስተር ሲቲን ወደ መሰለ ግዙፍ ስኳድ ወዳለው ክለብ የመጣሁት የትላልቅ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት ያለኝን ጉጉት ለማሳካት እንድችል የበኩሌን ትልቅ እገዛን ለማበርከት የምችልበት አስተማማኝ ብቃትን ለመላበስ ለመቻል ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ በመሆኔ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በዚህ ክለብ ቆይታዬ ተደናቂ ስኬት እንደሚኖረኝ ከወዲሁ ለማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች ቃል ልገባላቸው እወዳለሁ›› ብሏል፡፡

የራሂም ስተርሊንግ ውጣ ውረድ የበዛበት የአንፊልድ ቆይታው ሲዳሰስ

በአሁኑ የዝውውር መስኮት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከተፈፀሙት ውሎች ውስጥ በአወዛጋቢነቱ ቅድሚያ የተሰጠው ራሂም ስተርሊንግ ለሊቨርፑል በበቂ ሁኔታ ጥቅም ሳይሰጥ ለማንቸስተር ሲቲ የፈረመበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ተጨዋቹ ሊቨርፑልን የመልቀቅ ሃሳብ እንዳለው ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ማርች 20/2015 በሰጡት መግለጫ ስተርሊንግ ክለባቸው ያቀረበለት የሳምንት ደመወዝን ወደ 100 ሺ ፓውንድ ኮንትራት ውል ማራዘምን እንደማይቀበለው እንደነገራቸው ይፋዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ነው፡፡

ከዛ ወዲህ ባሉት ወራት ውስጥ ሮጀርስና ሌሎቹ ኃላፊዎች የስተርሊንግን ሃሳብ ለማስቀየር የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ቢያደርጉም የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊው ኢንተርናሽል የከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመሆን ጉጉትን ለመቀልበስ ሳይችሉ በመቅረታቸው በክለባቸው ደጋፊዎች ትልቅ ተስፋ አሳድሮ የዘለቀው ቁልፍ ተጨዋችን በ49 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ ለማንቸስተር ሲቲ ለመሸጥ ተገድደዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በይፋ በተፈረመው ውል ስተርሊንግ ለማንቸስተር ሲቲ ለመጫወት የተስማማው በአምስት ዓመታት ኮንትራት ውል ነው፡፡ በዛኑ ቆይታው ማንቸስተር ሲቲ 180 ሺ ፓውንድ የሳምንት ደመወዝ የሚከፍለውም ይሆናል፡፡

ይህንን እውነታን ከግንዛቤ በማስገባትም የፉትቦል ተንታኞች ስተርሊንግ ዕድሜው 15 ለመድፈን ሲቃረብ ኪው.ፒ.አርን በመልቀቅ ለሊቨርፑል ከፈረመ በኋላ በአንፊልድ የፉትቦል ህይወቱ ያጋጠመው አጠቃላዩ ሁኔታን ከዚህ በታች ባለው መልኩ መለስ ብለው ቃኝተውታል፡፡

 

ፌብርዋሪ 2010

ሊቨርፑል ራሂም ስተርሊንግን ከኪውፒአር ለመግዛት በተደረገው ጨረታ ከማንችስተር ዩናይትድ፣ ከማንቸስተር ሲቲ እና ከአርሰናል ጋር ያጋጠመውን ጨረታ በማሸነፍ ከ500 ሺ ፓውንድ ሂሳብ ገዝቶታል፡፡ በወቅቱ የዝውውር ስምምነት ውል ላይ ሊቨርፑል ተጨዋቹን መልሶ በሚሸጠው ወቅት ከሚያገኘው ሂሳብ 20 ፐርሰንቱን ለኪው.ፒ.አር ያካፍላል የሚለው አንቀጽ ተጠቅሶበታል፡፡

ፌብርዋሪ 2011

የሊቨርፑል ወጣት ቡድን የሳውዝ ኢንድ አቻውን 9ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በረታበት የኤፍ.ኤ ዩዝ ካፕ ላይ ስተርሊንግ 5 ጎሎን በስሙ አስመዝግቧል፡፡

ማርች 2012

ዕድሜው 17 ዓመት ከ107 ቀናት በነበረበት ወቅት ስተርሊንግ ተቀይሮ በመግባት ሊቨርፑል ዊጋን አትሌቲክን 2ለ1 በረታበት ግጥሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋናው ቡድን ተሰልፏል፡፡ ያንን ግጥሚያ ያደረገው በዛን ወቅት የሊቨርፑል አሰልጣን የነበሩት ኬኒ ዳግሊሽ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት በሆላንዳዊው ዲርክ ካይት ምትክ ቀይረውት አስገብተውት ነው፡፡

ኦክቶበር 2012

በአንፊልድ ሮድ በተደረገው ግጥሚያ ለሊቨርፑል የመጀመሪያው የነጥብ ጨዋታ ጎልን በስሙ ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ ስተርሊንግ በጨዋታው 29ኛ ደቂቃ ላይ ከመረብ ያሳረፉት ጎሉ በመታገዝ የአሰልጣን ብሬንዳን ሮጀርስን ቡድን ሬዲንግን 1ለ0 ለማሸነፍ ችሏል፡፡

አፕሪል 2014

ለሊቨርፑል ዋናው ቡድን ለሙሉ ሲዝን ባደረጉት ግጥሚያዎች በአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ የአሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ቡድን ጠንካራ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክርን እንዲያደርግ ረድቶታል፡፡ በተለይም በአፕሪል 2014 ስተርሊንግ ለሊቨርፑል ድል መገኘት ከፍተኛ ወሳኝነት ያላቸው ሶስት ጎሎችን ለማስቆጠር ችሏል፡፡ የስተርሊንግ ሶስት ወሳኝ ጎሎች ከመረብ ያረፉት ሊቨርል ማንቸስተር ሲቲና ኖርዊችን 3ለ2 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት በረታባቸው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ነው፡፡

ጁን 2014

ለእንግሊዝ ዋናው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰለፈበት የ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር በሶቱም የአገሩ የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ላይ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት ለወደፊቱ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበትን ውጤታማ እንቅስቃሴን ለማበርከት ችሏል፡፡ ሆኖም ግን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከምድብ ማጣሪያው ውጭ ከመሆን አደጋ ሳያተርፈው ቀርቷል፡፡

ኦገስት 2014

ለእንግሊዝ ዋናው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰለፈበት የ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር በሶስቱም የአገሩ የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ላይ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት ለወደፊቱ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበትን ውጤታማ እንቅስቃሴን ለማበርከት ችሏል፡፡ ሆኖም ግን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከምድብ ማጣሪያው ውጭ ከመሆን አደጋ ሳያተርፈው ቀርቷል፡፡

ኦገስት 2014

ሰርተርሊንግ የ2014/15 ሲዝንን የከፈተው በመጀመሪያዎቹ ሶት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎቹ ሁለት ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር የታጀበ ውጤታማ ፉትቦልን በማበርከት ነው፡፡ ጎሎቹን ከመረብ ያሳረፈው ሊቨርፑል ሳውዝ አምፕተንን በአንፊልድ 2ለ1 እና ቶተንሃምን በኋይት ኸርትሌን 3ለ0 በረታበት ጨዋታዎች ላይ ነው፡፡

ኦክቶበር 2014

የውድድር ዘመኑን በእያንዳንዱ የሊቨርፑል ግጥሚያዎች ላይ በመሰለፍ ከጀመረ በኋላ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ግጥሚያዎች ለማጠናቀቅ የሚያስችለው ትንፋሽ እንደማይኖረው ለአሰልጣን ሮይ ሆጅሰን ነግሯቸዋል፡፡ በዚህም ሆጅሰን ከሳንማሪኖ ጋር በተደረገው ግጥሚያ ለ45 ደቂቃዎች እንዲሁም ኢስቶኒያን ሲገጥሙ በመጨረሻዎቹ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ተጠቅመውበታል፡፡

ጃንዋሪ 2015

በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ላይ የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ብዛት ያላቸውን ግጥሚያዎች ማድረጉን ከግንዛቤ በማስገባት የጥቂት ቀናቶች የእረፍት ጊዜውን ወደ ትውልድ አገሩ ጃማይካ በመሄድ ባሳለፈበት ወቅት የሊቨርፑል ሁለት ወሳኝ ግጥሚያዎች አምልጠውበታል፡፡

አፕሪል 2015

ስተርሊንግ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከሊቨርፑል የቀረበለት የተጨማሪ ዓመታት ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ለመቀበል መወሰኑን በይፋ አረጋግጧል፡፡ ሊቨርፑልን ለመልቀቅ ያሰበው ከገንዘብ ጥቅም ጋር በተያያዘ አለመሆኑን መግለጫውን ሰጥቷል፡፡

ሜይ 2015

የስተርሊንግ ወኪል ተጨዋቹ ከሊቨርፑል በቀረበለት የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ዙሪያ መነጋገርን ጨርሶ እንደማይፈልግ ማጋገጫውን ሰጥቷል፡፡

ጁን 2015 

ማንቸስተር ሲቲ ስተርሊንግን በ2ኛው ሙከራው በ40 ሚሊየን ፓውንድ ለመግዛት ያቀረበው ሂሳብ በሊቨርፑል ኃላፊዎች ውድቅ ሆኖበታል፡፡

ጁላይ 2015

ስተርሊንግ የሊቨርፑልን የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ቢጀመርም ከቡድኑ ጋር ግን ለዝግጅት ወደ ሩቅ ምስራቅ ለመጓዝ ፈቃደኛ ሳይሆንለት ቀርቷል፡፡ በዛኑ ማግስት ማንቸስተር ሲቲ በሶስተኛው ጥሪው ባቀረበው 49 ሚሊየን ፓውንድ ሂብ በሊቨርፑል ኃላፊዎች ተቀባይነት አግኝቶለት ስተርሊንግን በእጁ አስገብቶታል፡፡

The post Sport: ራሂም ስተርሊንግ ‹‹በማንችስተር ሲቲ ስኬታማ እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ›› appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያና ለሴካፋ ዋንጫ የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ተመረጡ

$
0
0

ethiopia
ሶከር ኢትዮጵያ እንደዘገበው:- ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ህዳር 4 እና 7/2008 ከኮንጎ አቻው ጋር ለሚያካሄዳቸው የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከህዳር 11-26/2008 ለሚከናወነው የሴካፋ ዓመታዊ ውድድር የሚከተለት ተጫዋቾች ከአገር ውስጥ ክለቦች ተመርጠዋል፡፡

ግብ ጠባቂዎች፡-
ታሪክ ጌትነት – ደደቢት
አቤል ማሞ – ሙገር ሲሚንቶ
ይድነቃቸው ኪዲኔ – መከላካያ

ተካላካዮች፡
ስዩም ተስፋዬ – ደደቢት
ዘካርያስ ቱጂ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሳህላዲን ባርጌቾ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አስቻለው ታመነ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ነጂብ ሳኒ – መከላከያ
ያሬድ ባዬ – ዳሽን ቢራ
አንተነህ ተስፋዬ – ሲዲማ ቡና
አዲሱ ተስፋዬ – መከላከያ

አማካዮች፡-
አስቻለው ግርማ – ሃዋሳ ከነማ
በሃይሉ ግርማ – መከላከያ
ጋቶች ፓኖም – ኢትዮጵያ ቡና
ኤልያስ ማሞ – ኢትዮጵያ ቡና
ቢኒያም በላይ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በረከት ይሰሃቅ – ሃዋሳ ከነማ
ታከለ ዓለማየሁ – አዳማ ከነማ
ይሁን እንዲሻው – ድሬዳዋ ከነማ

አጥቂዎች፡-
ራምኬል ሎክ – ቅደስ ጊዮርጊስ
መሀመድ ናስር – መከላከያ
ምንይሉ ወንድሙ – መከላከያ
ዳዊት ፈቃዱ – ደደቢት

The post Sport: ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያና ለሴካፋ ዋንጫ የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ተመረጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ሐበሻ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን በ10 ወር 2 ሚሊዮን ብር እየከፈለው ስፖንሰር ለማድረግ ተሰማማ

$
0
0

Habesha

ኢትዮጵያ ቡና ከሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ ፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እንዳስታወቀው ዛሬ ጥቅምት 23/2008 ዓ.ም በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥትዋል ፡፡ ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ለኢትዮጵያ ቡና በ10 ወር 2 ሚሊዮን ብር ስፖንሰርሺፕ የፈረመ ሲሆን አጠቃላይ ውሉ ለ5 አመት ይዘልቃል ፡፡በስምምነቱ መሰረት የሐበሻ ሲሚንቶ ሎጎ በኢትዮጵያ ቡና መለያ በቀኝ በኩል የሚያርፍ ይሆናል ይህም በአምበሉ መሱድ መሀመድ አማካኝነት ተዋውቋል ፡፡ በቀጣይ ሚያዝያ ወር በሚደረግ ውይይት ስፖንሰርሺፑን ለማሳደግ እና ውሉን ለማሻሻል እንደሚነጋገሩ በቦታው ተገልፅዋል ፡፡ የድርጅቱ የስራ ሃላፊዎች እና የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ከግንቦት ወር በኋላ ስራ ከሚጀምረው ሐበሻ ሲሚንቶ ጋር በትብብር በመስራት ለውጤታማነት እንደሚተጉ ገልፀዋል ፡፡

The post Sport: ሐበሻ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን በ10 ወር 2 ሚሊዮን ብር እየከፈለው ስፖንሰር ለማድረግ ተሰማማ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው›› አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ

$
0
0

ከላይ ንጉሴ ይባላል፡፡ የረዥም ርቀት እና ማራቶን ሯጭ ሲሆን አሁን የሚገኘው በስደት ቶሮንቶ፣ ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያሳለፈውን የህይወት ተሞክሮ በማስመልከት ከኢትዮጵ ዛሬ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፤ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
Niguse
ኢ.ዛ.፡- በቅድሚያ ይህን ቃለመጠይቅ እንድናደርግ ፈቃደኛ በመሆንክ በትዝታ ጋዜጣ ስም እያመሰገንኩ፤ እሰቲ እራስክን በማስተዋወቅ እንጀምር፡፡ የት እንደተወለድክ ፣ ሙያህን እና የአስተዳደር ሁኔታክን ግለፅልኝ
አትሌት ከላሊ፡- ከላይ ንጉሴ እባላለሁ፡፡ የተወለድኩት ራያ ከሚባል አካባቢ ሲሆን ትንሽዬ ገጠር ውስጥ ነው፡፡ እድገቴም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲሆን እዛው ራያ አካባቢ ነው፡፡ ትምህርቴንም ቢሆን እስከ ሁለተኛ ደረጃ እዛው ነው የጨረስኩት፤ በሙያ ደግሞ የረዥም ርቀት እና የማራቶን ሯጭ ነኝ፡፡

ኢ.ዛ.፡-ትንሽ ስለ ራያ ህዝብ እና አካባቢው ብትነግረኝ?
አትሌት ከላሊ፡- ራያ የሚገኘው በትግራይ ክልል ሲሆን፤ በህዝብ ቁጥር እንዲሁም በመሬት ይዞታው በክልሉ ደረጃ ሰፊ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የራያ ህዝብ ዋነኛ መተዳደያው በእርሻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሰፋ ያለ ይዞታ ቢኖረውም ህዝቡ ግን ከፍተኛ የሚባል በደል የደረሰበት ነው፡፡ ራያ በትግራይ ክልል የተካለለ ቢሆንም የተገለለ አካባቢ ይመስላል፡፡ እንደሌሎቹ የትግራይ ግዛቶች የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ሊሆን አልቻለም፡፡

ኢ.ዛ.፡- አካባቢው የልማት ተጠቃሚ አይደለም ስትል ምሳሌ ልትጠቅስልኝ ትችላለክ?

አትሌት ከላሊ፡- ለምሳሌ በከተማ እድገት ብንመለከት ማይጨው የራያ ዋና ከተማ ነው፡፡ እንደዋና ከተማነቱ ይኼ ነው የሚባል መሻሻል ወይም እድገት እንዲሁም ለእድገቱ የሚያስፈልጉ ከመንግስት የሚደረጉ አቅርቦቶች የሉም፡፡ ሌሎች በትግራይ ክልል የሚገኙ አካባቢዎችን ብንመለከት ልዩነቱን መገንዘብ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል አዲግራት ወይም ኡቅሮ የሚባሉ አካባቢዎች በአማካይ አንድ አይነት የህዝብ ቁጥር እና የመሬት ስፋት ይዘው ግን በመሀከላቸው ያለው የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ሰፊ ነው፡፡ አንድ መሰረተ ልማት ብናነሳ እንኳን፣ ህክምናን ብንመለከት በራያ አካባቢ ማይጨው የሚባል ቦታ ላይ አንድ መካከለኛ የሚባል ሆስፒታል ነው የሚገኘው፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ ይኸው አሁን ከ20 አመት በላይ አሳልፏል፤ ራያን በሚያክል አካባቢ አንድ ክሊኒክ ብቻ፣ አስበው ከተለያዩ የራያ ክፍሎች ሰው ታሞ የሚመጣው እዚችው ሀኪም ቤት፣ እዛ ድረስ እስኪደርስ ያለውን እርቀት፣ መንገድ ላይ የሚሞትም አለ፣ እንደዛም ሆኖ ብትደርስ ብዙ ጊዜ ወደሌላ የትግራይ አካባቢዎች ለሚገኝ ሆስፒታል ሪፈር ትደረጋለክ፡፡ የሌሎች አካባቢ እንቅስቃሴዎችን የማየት እድሉን ስላገኘው ከራያ ጋር ሳመዛዝነው ውስጤ ያዝናል፡፡ ይኼም ሳያንስ መንግስት እንዲህ እና እንዲያ እያደረኩ ነው ብሎ በሚዲያ ሲናገር ጉዳዩን ለምናውቀው የሚያሳዝን ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-በቋንቋ ስንመለከት ራያ በሦስት የተከፈለ ነው ብለው የሚናገሩ አሉ ይኸውም የአማርኛ ተናጋሪ፣ የኦሮምኛ እንዲሁም የትግርኛ ተናጋሪ፤ ሦስቱም አንድ ላይ ተጠቃለው ነው ወይስ እንደቋንቋቸው አካባቢያቸውም ይለያያል?

አትሌት ከላሊ፡- ራያን በአጠቃላይ ስንመለከተው በሁለት ልንከፍለው እንችላለን፤ ይኸውም ራያ ቆቦ የሚባለው ወደ አማራ አካባቢ የሚገኘው ሲሆን በአብዛኛው የአማርኛ ተናጋሪ ያለበት ክፍል ሲሆን፤ እኔ ወደምኖርበት አካባቢ ያለው ደግሞ ራያ አዘቦ የሚባለው አካባቢ ሲሆን ትግርኛ፣ አማርኛ እንዲሁም ኦሮምኛም ተናጋሪዎች ያሉበት ነው፡፡ እንዲህ ቢከፋፈሉም ያው እንደ አንድ ክልል ነው የሚታወቁት፡፡

ኢ.ዛ.፡-ወደ አትሌቲክሱ ህይወትክ እንመለስ እና እንዴት ወደ ሩጫው ገባህ?

አትሌት ከላሊ፡- ፕሮፌሽናል የአትሌቲክስ ህይወት የጀመርኩት እዛው ራያ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ በጊዜው የከፍተኛ ሁለተኛ ተማሪ ነበርኩኝ ጊዜውም ወደ 1999 ዓ.ም. አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ በጊዜው ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሯጮች በክልሉ በተካሄደው ውድድር ይሳተፉ ነበር፡፡ እኔም የምኖርበትን ወረዳ በመወከል ለመሳተፍ በቃሁ፡፡በጊዜው ጥሩ የሚባል ሰዓት በማስመዝገቤ ከዛን ጊዜ በኋላ በሌሎች ውድድሮችም እንድሳተፍ ተደረኩኝ ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-እንደሚታወቀው እትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በብዙ የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ታፈራለች፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ችሎታ ኖሯቸው እንኳን እድሉን አግኝተው ወደ ከፍተኛ መድረኮች ወጥቶ ለመወዳደር በራሱ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባቸው በየጊዘው የሚሰማ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ አንተም ከእነሱ አንዱ እንደመሆንክ እንዴት እድሉን አገኝተክ ልትወጣ ቻልክ?

አትሌት ከላሊ፡- እርግጥ ነው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት፤ የኔም ጉዳይ ቢሆን እድል ተጨምሮበት እንጂ ሚናልባትም እዛው እቀር ነበር፡፡ ወረዳ ላይ ከተሳተፍኩ በኋላ ሌሎች ውድድሮችም ላይ አመርቂ ውጤት በማስመዝገቤ የትግራይ ክልልን ወክዬ እንድሳተፍ ተደረኩኝ፡፡ ከዛም ወደ አዲስ አዲስ አበባ በመምጣት ትግራይን ወክዬ ተወዳድሬያለሁ፡፡ በይበልጥ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2002/2003 ዓ.ም. ጥሩ ፐርፎርማንስ አሳይቼ ነበር በዚህም የተነሳ ማረሚያ ለሚባል የስፖርት ክለብ ውስጥ ለመሮጥ በቃሁ፡፡ እዛ በነበርኩበትም ወቅት በተለያዩ ውድድሮች ላይ የተሳተፍኩ ሲሆን ይኸውም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በበርካታ መድረኮች ላይ ለመወዳደር ችያለሁ፡፡

ኢ.ዛ.፡-በተለያዩ ሀገራት የመወዳደር እድል እንዳገኘክ ነግረኸኛል፤ እንዴት ነበር በግልክ ነው ወይስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመቻችቶልክ ነው?

አትሌት ከላሊ፡- በእርግጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው በውድድሩ ላይ እንድንሳተፍ የሚያደርገው፡፡ ይሁን እንጂ የምትወዳደርለትን ክለብ ወይም ሀገርህን አልያም ደግሞ በግልቅ መሳተፍ ትችላለክ፡፡ ዋናው ነገር በቅርብ ጊዜያት የምታስመዘግበው ውጤት ይወስነዋል፡፡ ለምሳሌ በረዢም ርቀቶች ላይ ስትሳተፍ ቢያንስ ጥሩ ሰዓት እና ከ1-7 ወይም እስከ 8ኛ ደረጃ ላይ የሚወጡት ሯጮች ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡ ሀገር እንዲወክሉ ይደረጋል ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በተያያዘ በርካታ መረጃዎችን እንሰማለን፤ ይኸውም እኩል የሆነ እድል ለሯጮች አይሰጥም፣ በሙስና የተጨማለቀ ነው፣ በብሔር የተከፋፈለ ነው፣ ሯጮች በሀገር ውስጥ እድል ሳይሰጣቸው ለሌላ ሀግር እየሮጡ ውጤት እያመጡ ነው እና የመሳሰሉ ቅሬታዎችን፤ ከዚህ አንፃር አንተስ የታዘብከው ወይም የደረሰብክ ነገር አለ?

አትሌት ከላሊ፡- በቅድሚያ የሰማኸው መረጃ ትክክል መሆኑን እኔው እራሴ ላረጋግጥልክ እወዳለው፡፡ ያው በየጊዜው የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ እንደው በቅርቡ እዛ በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተውን አንድ ጉዳይ ብነግርክ፤ የሴቶች የረጅም ሩጫ ተካሂዶ ነበር፡፡ ታዲያ ውጤት ያመጡትን ይመርጣሉ ብለን እየጠበቅን 2ኛ ነው 3ኛ የወጣችውን ጥለው ውድድሩ ላይ አቋርጣ የወጣችውን ተወዳዳሪ መርጠዋል፡፡ እሷም ሄዳ ውጤት አላመጣችም በውድድሩ 24ኛ ነበር የወጣችው፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ በቅርቡ የታዘብኩትን ነው የነገርኩህ፡፡ ይህ የሚያሳየው ፌዴሬሽኑ ምን ያክል በዝምድና፣ በሙስና፣ በብሔር እና በፖለቲካ አቋምህ እንደሚወሰን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አትሌቲክሱ አያድግም፣ ለታዳጊዎች እድል አይሰጡም ከዚህ የተነሳ ይኸው የድሮ ዝናውን እያጣ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ብዙ ችግር አለበት፤ እውነተኛ ነገር እየተሰራ አይደለም፡፡ የመወዳደር አቅም እና ችሎታ እያለክ፣ ውድድር አግኝተክ፣ ኢንቪቴሽን ወረቀት መጥቶልክ እንኳን በውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ብር ጉቦ መስጠት አለብክ፡፡ ይህን ደግሞ ማድረግ የሚችሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡

ኢ.ዛ.፡-እንደገለፅክልኝ ይህ የሚያሳየው በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ችግር እንዳለ ነው፡፡ ታዲያ አትሌቶቹስ ይኼን እያዩ እንደው ዝም ብለው ያልፋሉ፤ ተሰባስበው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ከዚህ አንፃር?

አትሌት ከላሊ፡- የአትሌቶች ማህበር የተቋቋመ አለ፡፡ ሁሉንም አትሌቶች ያቀፈ ማለት ነው፡፡ ሰብሳቢዎቹም ትላልቅ የሚባሉ አትሌቶች ናቸው፡፡ በየጊዜው ስብሰባ ይደረጋል፣ ችግሮች ይነሳሉ፣ መፍትሄ ተብሎ ይወራል ነገር ግን እስካሁን ምንም ሊፈጥሩ አልቻሉም፡፡ አሁንም ችግሮቹ እንዳሉ ናቸው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ፌዴሬሽኑ ከገዢው ፓርቲ ጋር በተያያዘ ባለው የፖለቲካ ትስስር ሲታማ ይሰማል፡፡ ለምሳሌ የቴክኒካል ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጁሎ የኢህአዴግ አባል መሆናቸው በራሱ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንተ ምን አስተያየት አለህ?

አትሌት ከላሊ፡- እውነቱን ለመናገር ዳይሬክተሩ ብቻ ሳይሆኑ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው፡፡ ምንመ እንኳን ፌዴሬሽኑ ከፖለቲካ ገለልተኛ አካል በመሆን መስራት ሲገባው አሁን ባለው ሁኔታ ግን ይህ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ ማናቸውንም ጥያቄዎችን ማንሳትም ሆነ ወደ በላይ አካል ማቅረብ በራሱ ከባድ ነው፡፡ አንደኛ ሁሉም የተሳሰሩ ስለሆኑ ምላሽ አታገኝም፤ ድምፄን አሰማለሁ ያልክም እንደሆነ የፖለቲካ ታፔላ ተለጥፎብክ ሌላ ችግር ይደርስብካል፡፡

ኢ.ዛ.፡-አንተ እንደ አንድ አትሌት ለዚህ መፍትሄው ምንድነው ትላለክ?
አትሌት ከላሊ፡- በርግጥ እኔ ፖለቲካኛ ስላልሆንኩና ብዙ ፖለቲካ ስላማላውቅ እንዲህ ነው ብዬ ስፊ ትንተና ልሰጥህ አልችልም፡፡ ግን እርግጠኛ ሆኜ የምነግርክ መንግስት ከአትሌቲክሱ ውስጥ ጣልቃገብነት ማቆም አለበት፡፡ አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ካልመጣ በፌዴሬሽኑ አካባቢ ብቻውን ለውጥ ይመጣል ወይ የሚለው ነግር ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን በአትሌቲክስም ይሁን በሌላው የህይወት መስክ ወጣቱም፤ የሚቀጥለው ትውልድም ይኼን ስርዓት በርትቶ መታገል አለበት ነው የምለው፡፡ ሌላ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡

ኢ.ዛ.፡-በመጨረሻ እንደው ሌላ የምትጨምረው ወይም የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ?
አትሌት ከላሊ፡- በይበልጥ ወጣቱ የተወሰደበትን የእኩልነት እና የነፃነት መብቱን፣ ለእውነት እና ለማንነቱ መታገል አለበት፡፡ ሰው በድህነቱ በብሔሩ ወይም በፖለቲካ አስተሳሰቡ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ መመልከት ሳይሆን አንድ ሆኖ መታገል አለበት፡፡ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ስለሰጠሀን ቃለምልልስ እናመሰግናለን፡፡

አትሌት ከላሊ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

The post ‹‹የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው›› አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኮንጎ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ትጫወታለች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተይዞ በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ለጥቂት ከመሳተፍ የተደናቀፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2018 ዓ.ም በሩሲያ በሚደረገው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ከኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያደርግ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::

File Photo

File Photo


ብሄራዊ ቡድናችን በሳምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚያደርገው ወሳኝ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ልምምድ መጀመሩን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የዋሊያዎቹ የፊት መስመር ተጫዋችም ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቡድኑን እንደተቀላቀለ ገልጸዋል::

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ይህን ወሳኝ ግጥሚያ ካደረገ በኋላ በሳምንት ልዩነት ውስጥ የመልሱን ጨዋታ በኮንኮ ብራዛቭል እንደሚያደርግም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ የዘንድሮውን የሴካፋ ዋንጫ ሻምፖዮናን እንደምታስተናግድ ታወቀ:: ኢትዮ-ኪክ እንደዘገበው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከNov 21- Dec 5 ለሁለት ሳምንት ለሚደረገው የምስራቅና መካከለኛው የሴካፋ ሻምፒዮና የምድብ ድልድል ሲታወቅ ኢትዮጵያ ሻምፒዮናውን በአዲስ አበባ ስታዲየም፣ በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም እና በሃዋሳ ስታዲየሞች እንደሚደረግ ታውቌል።
-•-•-•-•-
በምድብ 1) ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ከዛምቢያ፣ ሶማሊያ
•-•-•-•-•-
በምድብ 2) ኡጋንዳ ፣ኬንያ ፣ቡሩንዲ ፣ ጅቡቲ
•-•-•-•-•-
በምድብ 3 ) ሱዳን ፣ርዋንዳ ፣ ዛንዚባር፣ ደቡብ ሱዳን

The post ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኮንጎ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ትጫወታለች appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የአሮጊት ፉትቦል…..የሴት ጨዋታ –ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

$
0
0

genene Mekuria
የብሄረዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሰሞኑን በሬድዮ ሲናገር እንደሰማሁት‹‹እኔ የአሮጊት ፉትቦል መጫወት አልፈልግም››አለ፡፡አሰልጣኙ አሁን እየተኬደበት የምትትሮሽ ጨዋታ ይልቅ ልጆቹን መነሻ ባደረገ በኩል እንዲሰራ ሀሳብ ሲቀርብለት ያንን ለመቃወም የተናገረው ነው‹‹እኔ ቶሎ ባለጋራ ሜዳ የሚገባ ቡድን ነው የምፈለወገው ››አሉ፡፡ባለጋራ ሜዳ ቶሎ መግባት ጥሩ ነው ግን በምንድነው ባለጋራ ሜዳ የሚገባው? ፡፡ቶሎ ባለጋራ ሜዳ የሚገባውተጠልዞ ነው በዚህ መንገድ ደግሞ ከእኛና ባለጋራ ማን እንደተሻለ ብዙ ግዜ ታይቷል፡የእኛ ተጨዋቾች በተለይ ከምእራብ አፍሪካ ቡድን ጋር ሚዛን ላይ ተቀምጠው በምንድነው መቋቋም የሚችሉት ቢባል ያለን ነገር በቴክኒክ በኩል ነው፡፡ይሄ ቴክኒክ መገለጫው በመቀባበል ነው፡፡መቀባበሉ ደግሞ በመረዳዳት ባለጋራን ለመቋቋም ያስችላል፡፡ ቶሎ ወደፊት ኳሱ ሲጣል የእኛ ተጨዋች ተሻምቶ ነው የሚያገኘው(ያውም ካገኘ) ኳስ ሲያገኝ የሚረዳው ስለሌለ በግል ይሞክራል፡፡ በግል ደግሞ እነርሱ በፍጥነትም ጉልበት ይበልጡናል ፡፡እንደሚበልጡንም ለረጅም አመት አይተነዋል፡፡ስለዚህ በግል ተገኝቶ በጉልበት ከተበለጥን ኳስ የያዘ ሰው ረዳት ተበጅቶለት እየተቀባበሉ ባለጋራ ሜዳ ቢገቡ ያዋጣል እንጂ አይጎዳም፡፡

መረዳዳቱን(መቀባበሉን)የአሮጊት ፉትቦል ከተባለ የአሮጊት ባልሆነው ፉትቦል አሰልጣኙ መብለጫ መንገድ ሊያሳዩን ይገባል፡፡ከዮሀንስ በፊት የነበሩት አሰልጣኝ ባሪቶ ሀዋሳ በልምምድ ጌም ተጨዋቾቹ ሲቀባበሉ‹‹ እኔ የሴት ፉትቦል አልፈልግም፡፡ ቶሎ ኳሱን ለአጥቂው ወደፊት ጣሉት››ብለው ትእዛዝ ሰጡ ፡፡ቶሎ ለአጥቂው የሚጥልላቸውን ተጨዋች ቀይረው አስገቡ፡፡ እዚህ በሜዳችን ከአልጀርያ ጋር ቶሎ ለአጥቂው እየተጣለ ምን እንደደረሰብን አይተነዋል ፡፡ ቶሎ ለአጥቂው መጣል ‹‹የወንድ›› መቀባል ደግሞ ‹‹የሴት›› ከሆነ እናም በመቀባበሉ የምንበልጥ ከሆነ አዋጪው የሴት የተባለው ነው፡፡ዮሀንስም እንደባሪቶ ቶሎ ባለጋራሜዳ ለመግባት ወደፊት እየጣለ ያለረዳት ለመጫወት መሞከሩ የባሪቶን ነገር ሊደግምልን ነው፡፡ተጫዋቾቹ የሚችሉት ነገር አለ፡፡በሚችሉት ነገር ላይ እንዲጫወቱ መፍቀድ በሜዳ ላይ ብልጫ እንዲይዙ ማደረግ ነው፡፡የልጆቹን መብለጫ ‹‹የአሮጊት ፉትቦል ነው አልፈልግም….የሴት ፉትቦል ነው አልፈቅድም››በሚል ማጣጣሉ የት እንዳረሰን አይተነዋል፡፡ የሚገርመው አሰልጣኞቹ ያዋጣል በሚሉት ነገር ሊያሳዩን አልቻሉም ፡፡አማራጩንም(የአሮጊት፤ የሴት )በሚል ማጣጣል ስያሜ እየሰጡ እነርሱ በሚሰሩት ነገር እየተዋረዱ እዚህ አድርሰውናል፡፡ያሁኑ አሰልጣኝ ለለውጥ አልመጣም፡፡ ሌሌቹ ትተው የሄዱትን የውድቀት አጨዋወት ሊያስቀጥል ነው፡፡

…የሆንስ መረዳዳቱን ወይም ልጆቹ በሚችሉት በሚያውቁት መንገድ መጫወቱን የአሮጊት ፉትቦል ካለ የአሮጊት ባልሆነው ነገር ባለጋራን መብለጥ እንዳልቻለ አይተነዋል ነገም ይሄንኑ ነገር ያሳየናል፡፡የዮሀንስ ስትራቴጄ ደጋግሞ እንዳወራው ቶሎ ባለጋራ ግብ ጋር መድረስ ነው፡፡

እንዴት ነው የሚደረሰው የሚለው ጉዳይ ነው አስቸጋሪ የሆነው፡፡አሁን እንደታየው ግብ ጋር የሚደረሰው(በተለይ ከሜዳ ውጭ) በሚጣል ኳስ ነው፡የሚጣለውን ኳስ አጥቂዎቹ ለማግኘት ይቸገራል፡፡ቢያገኙም ረዳት ስሌሌለ ቶሎ ይነጠቃሉ፡ምክኒያቱም ብቻለ ብቻ ጉልበት ስለሚጠይቅ የእኛዎቹ በጉልበት የመቋቋም ችግር ስላለባቸው እያስረከቡ ይመጣሉ ቶሎ ግብ ጋር እንዲደርስ የተጣለው ኳስ ቶሎ ባለጋራ እጅ ገብቶ እኛ ላይ የጥቃት ጫናው ይጠነክራል፡፡ቶሎ ግብ ጋር ለመድረስ ሲባል እንቅስቃሴው በግል ነው የሚሆነው፡፡ በግል ጉልበት ስለሚጠይቅ አስቸጋሪ መሆኑን ከዮሀንስ የተሻለ ሰው አስረጅ ሊሆን አይችልም፡በ1975 ዮሀነስ ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ ነበር፡፡በዚያን ግዜ የነበሩት ተጫዋቾቻን በፊዚካል አሁን ካሉት በብዙ እጥፍ ይሻላሉ፡፡ እነርሱ እንኳን በዚህ አጨዋወት ሊቋቋሙ አልቻሉም፡፡ በጉልበት በፍጥነትም ቶጎን የነዮሀንስ ቡድን እንዳልቻለ ሁሉ ያሁን ቡድን ከዚህ አጨዋወት ማስወጣትሲገባው እሱ ያልቻለበትን መነገድ ተጨዋቾችን እንዲተገብሩ ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ እሱም ያውቃል፡፡ቶሎ ቶሎ ባለጋራሜዳ እየጣሉ መግባቱ ለሌሎች አሰልጣኞችም እንዳላዋጣ ታይቷል፡፡ ዮሀንስ ሌሎች አሰልጣኞች አሁን እሱ እየሄደበት ባለው ነገር ውስጥ ተግብረው ወድቀት ውስጥ ገብተው እንደነበር መማር ይገባዋል፡፡ከአሰልጣኞቹ መማር ብቻ ሳይሆን እራሱም በኢንተርናሽናል ፉትቦል ካገኘው ተሞክሮ ትምህርት መወሰድ ነበረበት፡፡በ1975 ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቶጎ ሲጫወቱ 4ለ2ተሸንፈው ነው የወደቁት፡፡በተለይ ቶጎ በሜዳው 3ለ0 ሲየያሸንፍ ከሜዳ አላስወጣቸውም ፡፡ከተከላካዪቹ አንዱ ዮሀንስ ከግራ በኩል ለአጥቂዎቹ በረጅሙ እየጣለ ነበር የሚሰጣቸው (ቶሎ እዲያገቡ) እሱ የሚጠልዛቸው ኳሶች በርግጥ ባለጋራ ሜዳ ደርሰዋል ግን የእኛ አልነበሩም፡፡ ዮሀንስ ወደ ባለጋራ ግብ ያሻገራቸው ኳሶች ቶጎ በር ላይ ደርሰዋል ነገር ግን ቶጎ እነዚህን ኳሶች እየተቀበለ በማጥቃት እኛ ላይ ብዙ ጫና ፈጥረውብን 3ለ0 ተሸነፍን፡፡ቶጎ በጣም ነው የበለጠን፡የተበለጥነው እኛ ይዘንለት የገባነው ነገር ለእነርሱ ስለተመቸ ነው፡ በዚያ አጨዋወት ብሄራዊ ቡድኑ ባለጋራን መግጠሙ አዋጪ እንዳልሆነ ይልቅ አክሳሪ እንደሆነ ራሱ ተጫውቶ አይቶታል፡፡፡እሱ ተጫውቶ ያላዋጣውን ነገር ያሁኑ ተጨዋቾች እንዲተገብሩ ማድረጉ ጉዳት ነው፡፡ ያ ቡድን ከቶጎ በፊት ሞሪሸስን ገጥሞ ነው ያለፈው ሞሪሸስን ሲያሸንፉ አጨዋወቱ ትክክል ነው ብለው አመኑ፡፡ ቶጎ ላይ ሞሪሸስ የሰጣቸውን ክፈተት ማግኘት አልቻሉም(ልክ አሁን ብሩንዲን ሲያሸንፉ ትክክል እንደመሰላቸው) ቶጎ በፍጥነት አና ጉልበት ከሞሪሸስ የተለየ በመሆኑ አልቻሉትም፡፡ ይሄ ከሆነ 33 አመት ሆነው ፡፡ዮሀንስ 33 አመት ሙሉ አልተማረም ፤አልገባውም፡፡ቢገባው ኖሮ እኔ ብሄራዊ ቡድን በነበርኩበት ግዜ በሀይል አጨዋወት ስላስቸገሩን በዚህ መንገድ አስቸጋሪ ስለሆነ አሁን በአሰልጣኝነት ግዜ ይሄን መንገድ መቀየር አለብኝ ማለት ሲገባቸው ተመልሰው ባልተቻለበት መንገድ መግባቱ አስገራሚ ነው፡፡በዚያ ላይ በተክለሰውነት የነ ዮሀንስ ቡድን ካሁኑ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በእጅጉ የገዘፉና ጠንካራ ናቸው ግን እነርሱም(የነዮሀነስ ብሄራዊ ቡድን) በዚያ ሰውነታቸው መብለጥና መቋቋም አልቻሉም(የሰውነት አቀማቸውን ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ያሁን ብሄራዊ ቡድን እና ቶጎን በ1975 የገጠመውን ቡድን ፎቶ አቀርቤላችኋለሁ ፡፡ዮሀንስ ከቆሙት ከግራ ሁለተኛው ነው )እናም ዮሀንስ ተጫውቶ ያልቻለበትን ነገር እንዴት ያሁኑ ትወልድ ሊተገብረው ይችላል፡፡

…………አሁን ይሄ ቡድን በዚህ አጨዋወት ለአፍሪካ ዋንጫ በሆነ ምኪኒያት ቢያልፍ የሚቋቋም ይመስላችኋል?፡፡ ብናልፍም እንኳን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ሳይሆን አልፈን ምንድነው የምንሰራው?የሚለው ነው መታየት ያለበት፡፡ባለፈው አፍሪካ ዋንጫ የገባው ቡድን አንድ አግብቶ ሰባት ገብቶበት ውራ ሆኖ መጣ ፡፡ጥሩ ነው የተባለለነት ነገር ቀጣይነት አልነበረውም፡፡ጀግና የተባለው ቡድናችን ገብቶ ውራ ሲሆን ጀግንነታቸችን ለውራ ከሆነ ምን ያደርግልናል፡፡በዚያ የአፍሪካ ዋንጫ የውጭ ጋዜጠኖች የእኛን ቡድን ኳስ ጥሩ ናቸው አሉን፡፡ ግን ኳስ የሚጫወት ቡድን ሰርተን አይደለም የገባነው፡፡ በተፈጥሮ ያለን ነገር ይሄ በመሆኑ በዚህ የተወሰኑ ልጆች በግል የሆነ ነገር ስላሳዩ ኳስ ጥሩ ናችሁ አሉን፡፡ታዲያ ለምን ጥሩ ናችሁ የተባልንበትን ነገር(አሁን የአሮጊት የተባለውን) በስልጠና ብናሳድግ እንጠቀማለን፡፡ጋዜጠኞቹ የእኛን ቡድን በጉልበት ጥሩ ናችሁ አላሉንም፡፡ በንጽርር ከሌሎች ቡድን ጋር አስተያይተውን እንደማንበልጥ ስላዩን በጉልበት ጥሩ ናችሁ አላሉም ፡፡እኛ ግን አሁን እየሰራን ያለነው በጉልበት ነው፡፡ይሄ ደግሞ አዋጪ እንዳልሆነ ነው ለብዙ ግዜ የታየው፡፡ዮሀነስ እስካሁን አለቆቻችን የሆኑትን ምእራብና ሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን አላገኘም፡በርግጥ ደደቢትን ይዞ የናጀርያን ቡድን ገጥሞ ተበልጦ ነው ከውድድር የወጣው እዚያ 2ለ0 ሲሸነፍ ከነብልጫው ነው፡፡ከዚህ ጨዋታ እንኳን መማር አልቻለም፡፡(በቅርቡ ካደረገው)ከምእራብ ቡድኖች ጋር ወደ ፊት ቶሎ ቶሎ የጣሉ ባለጋራ ሜዳ መግባት እንዳላዋጣ ተጫውቶም አሰልጥኖም ካየው ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረበት ፡፡ግን አማራጩና ጠቃሚውን የአሮጊት ፉትቦል ካለ ከእነርሱ ጋር ሲገናኝ ዳግም አሰቃቂ ነገር ነው የሚታው፡፡ያን ግዜ ሰበብ ደርድሮ ቆይታን ለማስቀጠል ካልሆነ ለውጥ ከእዚህ ቡድን ምንም አይጠበቅም ፡፡
የምእራብ አፍሪካ ቡድኖች የበለጡን በጉልበት ነው፡፡፡እነርሱ በዚህ አጨዋወት የበለጡን እኛም በጉልበት ስለገባን ነው፡፡በዚህ እንቅስቃሴ ለረጅም አመት እየበለጡን ነው፡፡ዛሬም ለረጅም አመት የተበለጥንበትን ነገር አንለቅም ብለን የለውጡን መንገድ‹‹የአሮጊት ነው››በሚል በነበረበት(በተዋረድንበት) ለመቀጠል መዘጋጀት አስገራሚ ነው፡፡መቼ ነው ታዲያ ማመዛዘን የሚችል አሰልጣኝ የምናገኘው? ያስብላል፡፡ ግን ለማመዛዘን የቸገራቸው ምንድነው፡፡ልጆቹ ያላቸው ችሎታ የታወቀ ነው ፡፡ያንን በስልጠና አዳብሮ በሚችሉት መንገድ እንዲጫወቱ ቢደረግ የተሻለ ነው፡፡አሁን ግን በማይችሉበት መንገድ እንዲጫወቱ ተደርገው በዚያ ላይ ተጠያቂ መደረጋቸው ጉዳት ነው ፡፡
– የሚሰጡት ስልጠና ጨዋታን የሚወከል አይደለም፡፡ ስልጠናው በረኛ ይለጋል፤ ሲለጋል ተሻምታችሁ አግኙ ነው፡፡ማሻማት ማሰልጠን አይደለም ይሄን ማን ያቅተዋል?…..መለጋት፤መልስ ምት፤እጅ ውርወራ፤ኮርና፤ክሮስ እነዚህ ሁሉ ማሻማት ናቸው፡፡ በማሻማት ወስጥ ከእኛ ይልቅ የውጭ ቡድናች ተጠቃሚ ናቸው፡፡ከማሻማት ውጭ ያለው ነገር ኳስ ይዞ ተረራድቶ መጫወት እውቀት ነው፡፡ በእወቀት ማሰልጠን ብልህነት ነው፡፡ግን በእወቀት ማሰልጠን አስቸጋሪ ሲሆንባቸው ባለጋራ ሜዳ እየጠለዙ በመግባት ነው የመረጡት፡፡በእወቀት ማሰልጠንና መጫወትን ግን ‹‹የአሮጊት›› ይሉታል
–እነርሱ በመረጡት አጨዋወት መቋቋም እንዳማይችሉ አሰልጣኞቹም ያውቃሉ፡፡ባለጋራን መብለጥ የምንችልበት አጨዋወት ፈልጎ መተግበር ሳይሆን እንዴት ሰበብ እየፈለጉ መቆየት ሚችሉበትን ነገር ነው የሚያስቡት

እከዛሬ የሰሩት አሰልጣኞች እግር ኳሱን ለመለወጥ ሳይሆን ደሞዝ በልተው የሚሄዱ ብቻ ነው ያየነው፡፡ያሁኑም አሰልጣኝ እንደበፊቶቹ በእግር ኳሱ ላይ የምንናፍቀውን ለውጥ የሚያሳየን እንዳልሆነነ ከአየያዙ መረዳት ይቻላል

– አሰልጣኞች ያመኑበትንና ያወጣል ያሉትን አጫወወት ሀላፊነት ሲወስዱ አይታዩም፡፡ይሄነገር ያወጣናል ካሉ በዚህ ለሚመጣው ነገር ሀላፊነት ወስደው ሲሸነፍም እኔ ነኝ የምጠየቀው ብለው መናገር አለባቸው፡፡ይሄ ማለት የመረጡት ነገር ስህተት ከሆነ ወደ ተሻለና ወደሚያዋጣ ነገር እንዲመጡ ያደርጋል፡፡አሁንግን ሀላፊነት ስላማይወሰዱ ከተሳሳተው ነገር መውጣት አይችሉም፡፡ስለማይወጡም በተሸነፉ ቁጥር ሰበብ እየደረደሩ የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ አልቻለም፡፡

– – አንዳንዴ ቡድኑ ሲያሸንፍ አሰልጣኞቹ ያሸነፉበትን መንገድ እንኳን አያውቁም፡፡እንዴት እንዳሸነፈ ስለማያውቁ ሲሸነፍ ሰበብ ይደረድራሉ፡፡ያሸነፈበትን ነገር ካላወቁ ሲሸነፍ ስህተቱ የቱ ጋር እንዳለ አይረዱም፡፡ለዚህም ነው ከማስተካከል ይልቅ ሰበብ የሚደረድሩት፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ የገባው ቡድን ባለጋራውን(እነ ቡርኪናን) መቋቋም ያቃተው ማጣሪያውን ሲያልፍ እንዴት እንዳሸነፈ ስለማያውቅ ነው፡፡ውጤት የሚባለው አንድ ጨዋታ አሸንፎ መፎለል ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መንገድ ብልጫ ይዞ ማሸነፍ የሚችል ቡድን ሲገኝ ነው፡ትናንትም ዛሬም ቀየጣይነት ያለው ነገር ይዞ የሚሄድ ቡድን አላገኘንም፡፡ቀጣይነት ያለው ሰበብ ብቻ ነው ከአሰልጣኞቹ ያገኘነው፡፡አሰልጣኙ ባመኑበት፤ ያዋጣል ብሎ በመረጠው ነገር ለውጥ ካላመጣ በአማራጩ ሀሳብ መሞከር አለበት
– እኛ ሀገር ለውጥ እንዲመጣ ሚዲያው ትልቅ ስራ መስራት አለበ ፡፡ከማሸነፍና መሸነፍ ውጭ በእወቀት ቢዘግቡ አሰልጣኞችን ወደ እውነተኛው ነገር ሊያመጧቸው ይችላሉ፡፡ቡድኑ ሲያሸንፍ ጉሮ ወሸባ ይላሉ፡፡ያሸነፈበትን ነገር መነሻችን ነው ወይ ብለው አየይመረምሩም ፡ብሩንዲን ያሸነፍንበት የጨዋታ እንቅስቃሴ ሌሎች ቡድኖች ለረጅም አመት ሲጨፈጭፉን የነረበት እንቅስቃሴ መሆኑ ታውቆ ከጉሮ ወሸባዬ ነገር ወጥተን ይሄ ነገር ከሌሎች ጋር አላዋጣንም(ከሰሜንና ምእራቡ) ብሩንዲው ውጤት አሳሳች ነው ቢሉ አሰልጣኞችም ወደ ትክክለኛው ነገር ሊመጡ ይችላሉ፡፡ለወደፊቱ ይሄ ቢስተካከል አሰልጣኞቹን ማረም ይቻላል ፡፡

ያሁኑ አሰልጣኝ በቅርብ ከሀላፊነት ይነሳል፡፡ግን አሰልጣኙን በምን እናስታውሰዋለን፡፡ምኪኒያቱም ምንም የሰራልንና ያስቀመጠልን ነገር የለም፡፡ሌሎች አሰልጣኞች ያልቻሉበትን መንገድ እያስቀጠለ ነው፡፡በአምስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን ያሳለፉት አሰልጣኝ ሽፈራው በሴኔጋል 5ለ1 በቱኒዝያ 4ለ0 ተሸንፈው ከምድቡ ከአጠቃላይም ውራ ሆነው ተመለሱ፡፡ ለሰባተኛውም ያሳለፉት አሰልጣኝ በአይቮሪኮስት 6ለ1 በሱዳን 3ለ0 ተሸንፈው ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጡት፡፡መንግስቱ ወርቁ ለ13ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ቡድኑ እንዲያልፍ አደረገ፡፡ ነገር ግን አንድም ጨወታ ሳያሸንፍ ቡድኑ በሶስቱም ጨዋታተበልጦ ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጣው(ከስምንት ቡድን ስምንተኛ) ከሊቢያወው ቀጥሎ በ29ነኛ አፍሪካ ዋንጫ በ2005 አለፍን በማለፋችን እግር ኳሱ እንደተለወጠ ተወራ፡፡ይሄኛውም እንደሌሎቹ ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጣው፡፡ባለጋራን መብለጥ ቀርቶ መቋቋም አልቻለም አንድ ግብ አስቆጥሮ ሰባት ገብቶበት ነው የተመለው፡፡እነዚህን ለአፍሪካ ዋንጫ ያሳለፉትን አሰልጣኞች በምን አንስታውሳቸው ምክኒያቱም ምንም ያስቀመጡልን ነገር የለም፡፡ የምእራብ አፍሪካን ቡድኖች መቋቋም አቅቷቸው ነው የወጡት፡፡እነዚህን አሰልጣኞች የማናስታውሳቸው እኛ በምንበልጥበት ሳይሆን በተበለጥንበት ይዘውን ስለገቡና ስላስጨፈጨፉን ነው፡፡እነዚህ ለአፍሪካ ዋንጫ አሳልፈው ምንም ሳይሰሩ ውራ ወጥተው ተበልጠው የተረሱ ናቸው፡፡ ሌሎች አሰልጣኞችም ምንም ሳያሳዩን ከሀላፊነት ተነስተዋል የሆንስም ከእነኚህ አንዱ ነው ምንም ሳያሳየን ወደ ለውጥ ሳይወስደን ችግሩን ሳይፈታ ከሀላፊነት ይነሳል እናም በዚው ይረሳል፡፡ከሌሎች አሰልጣኞች ይልቅ በአሁን ሰዓት የካሳዬ ስም የሚነሳው ትንሽ የለውጥ መንገድ ስላሳየና ስላስቀመጠ ነው፡፡ለሌሎች ከተከተሉበት መንገድ ወጣ ስላለ ነው፡፡ፍንጭ ለማሳየት በመሞከሩ ነው፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ በራሱ ምንም ነገር የለውም….ማለፉችን ከእድገት ጋር ቢሆን ከለውጥ ጋር ቢሆን ጥሩ ነው፡፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን እድገታችንን ሳይሆን ውድቀታችንን ነው የሚየሳየው(በብዙ ግብ እየተሸነፍን ውራ ሆነን ስለምንወጣ)፣፡እከዛሬ የታየው ተስፋ የሌለውና በባለጋራ በእቅስቀሴና በውጤት ተበልጠን ነው የታየው፡፡ዛሬም ሀላፊነቱን የያዙት ከሌሎች ሳይማሩ ለሌሎች ያሳዩትን ደካማ ነገር ለመድገም ነው፡፡ገና አንድ ጨዋታ ሲሸነፉ‹‹የኢትየዮጵያ እግር ኳስ ችግር አለው፤አጥቂ የለም፤በረኛ የለም››ይላሉ ሲረከቡ እኮ ይሄን አውቀው ነው ፡፡ሲቀጠሩ ለአፍሪካ ዋንጫ እናሳልፋለን ይሉና ሲሸነፉ የቅድሙን ችግሮች ያነሳሉ
– አንድ ነገር ደግሞ አለ፡፡ወደ ለውጥ የሚወስድ ቡድን መስራት ሲያቅታቸው እንትናን ወደ ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ በሚል ክሬዲት በዚህ እንዲያዝላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ኤፌም ኦኔራ በተጋጣሚ ቡድኖች እንደዚያ ተቀጥቅጦና ተበልጦ ከሄደ በኋላ እነ አሉላ፤ ሽመልስ፤ኡመድን ብሄራዊ ቡድን ያመጣኋቸው እኔ ነኝ ብሎ በሰራው ቡድን ሳይሆን በልጆቹ ክሬዲት እንዲያዝለት ሲወተውት ነበር፡፡ባሪቶም ናትናኤልን አንዳርጋቸውን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔነኝ አሉን፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹ራምኬሎን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ››በሚል እየተወተወትን ነው …አኛ እንትናን ማምጣታቸው ሳይሆን ባለጋራን መቋቋም የሚችል ተስፋ ያለውና የምንመካበት ቡድን ሲሰሩልን ነው፡፡ካለበለዚያ እገሌን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ በሚል የለጥው ቡድን ሳይሰሩልን ቢቆዩ ፋይዳ የለውም፡፡የእኔ ከእከሌ አሰልጣኝ ይለያል ለማለት ነው፡፡በአንድ ወቅት በሴኔጋል 3ለ0የተሸነፈው ቡድን አሰልጣኝ ‹‹የእኔ ቡድን ጥሩ ነው፡፡ያለፈው አሰልጣኝ 4ለ0 ነው የተሸነፈው፡፡ እኛ እንደነርሱ በዙ አልገባብንም›› በሚል የእሳቸው ቡድን በምን ከሌሎች እንደሚለይ ነግረውን ነበር ፡፡4ለ0 የተሸነፈው 3ለ0 የጠጣውም በተመሳሳይ እንቀሰስቃሴ ተበልጠው ምን የተሻሻለ ነገር ሳያስቀምጡልን ነው የሄዱት፡፡
– ያሁኑም አሰልጣኝ ደሞዝ ተቀብሎ ለመሄድ ሳይሆን ለለውጥ ቢሰራ አይረሳም፡፡

The post Sport: የአሮጊት ፉትቦል…..የሴት ጨዋታ – ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ጉሮ ወሸባዬ በሉ!! –ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

$
0
0

ባለፈው ሳምንት እሁድ ቀን ቡሩንዲን 3ለ0 አሸንፈን ወደ ቻን ውድድር ገባን፡፡ 2ለ0 ነው የተሸነፍነው፡፡ 3 አስገብተን በማለፋችን ቡድኑ ጥሩ መሆኑን ለማለፍ የሚያስፈልገውን ጎል እንደሚያስገባ ስለተነገረ በቡድናችን ላይ ሉም እምነቱን ጣለ፡፡ ግን ያልተረጋገጠው ጠጋጣሚያችን ማነው? ምድነው? የሚለው አልታየታ ፡፡ ቡሩንዲ ከሚዳው የማይወጣ ብቻ ሳይሆን ለኛ ተጫዋቾች ሰፊ የመጫወቻ ቦተ የሰጠን ነው፡፡

File Photo

File Photo

ስለማያስቸግረን ጎል አገባንበት ( አላሸነፍነውም)፡፡ ማሸነፍ ባላጋራ የዘጋውን ቦታ አስከፍተን፣ባልጣን ጎል ስናስቆጠ ብቻ ነው፡፡ ቡሩንዲ ግን ራሱ ለቆ በሰጠን ቦታ ጎል ስላገባንበት ያለንን ጥሩ ነገር ማሳየት አልቻልንም፡፡ ባለፈው ሳምንት የፃፍኩትን አስታውሱ፡፡ ቡድናችን 3 ጎል አስቆጠረ ግን ብልጫ መውሰድ አልቻለም፡፡ ራዲዮኑ ፣ምናምኑ ስላሸነፍን ጉሮ ወሸባዬ ሲል ነበር፡፡ የኛ ቡድን ያሸንፍ እንጂ በቡሩንዲ ላይ ምንም ማሳየት አልቻለም፡፡ ቡሩንዲ ላይ ያገኘውን ነፃ ቦታ ሌላው ሊሰጠን አይችልም ስለዚህ ቡሩንዲን ያሸነፍንበተ ጨዋታ ሌሎች ሲመጡ ብልጫ ወስደው ሊያዋርዱን ስለሚ፣ከችሉ ቡሩንዲን ያሸነፍንበት ጨዋታ እናውግዝ ብያችሁ ነበር፡፡ ቡሩንዲን 3ለ0 አሸንፈን ስለወድን ብሔራዊ ቡድኑ ቃሉን የሚጠብቅ ለሌሎቹም እንደማይመለስ ነው የተነገረን፡፡ ዛሬም 6 ሰዓት በቲቪ አሰልጣኙና አምበሉ ብሔራዊ ቡድኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እመርታ ያሳየ እና ለማንም እንደማይመለስ ነው የነገሩን፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ተመለስ አትመለስ አንለውም ግን ምን ይዞ ነው ይህን ሁሉ የሚያወራው፡፡

ባለፈው ሳምንት ቡሩንዲን ሲያሸንፍ ጉሮ ወሸባዬ ተብሎ በሚዲያ ሲፎከር ነበር፡፡ ነገር ግን ጉሮ ወሸባዬ የሚያስፈልገው ዛሬ ነበር፡፡ ምክንያቱም በዚያው አጨዋወት ነው ዛሬ የተሸነፍነው፡፡ ኮንጎ የምዕራብ አፍሪካ ቡድን ነው፡፡ ግን ጥግ ያለ ነው፡፡ ምዕራብ አፍሪካ የሚባሉት መሀል ያሉት ናይጄሪያ፣አይቮሪኮስት፣ካሜሮን ፣ ጊኒ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ጊኒ የዛሬ 5 ዓመት እዚሁ 4ለ1 አሸንፎን ነበር፡፡ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው( በርግጥ ቦታው ይለያያል)፡፡ ኡመድ ኡክሪ ባስቆጠረው ጎል 1ለ0 መራንና 4ለ1 ተሸነፍን፡፡ የተሰጠው ሰበብ ዶፍ ዝናብ ስለዘነበ ነው፡፡ ሜዳው የኛ፣ ዝናቡ የኛ፣ ጎርፉ የኛ፡፡ ብቻ ሰበብ ለማቅረብ፡፡ ለዛሬው መሸነፋችን ተጠያቂው ዮሐንስ አይደለም፡፡ ሚዲያው ነው፡፡ ቡሩንዲ ፣ በሰኦቶሚ ተሸንፎ መጥቶ እዚህ ውጤቱን ገልብጦ መጥቶ ሁለቱንም 3ለ0 ሲያሸንፍ ዮሐንስ ውጤት ቀያሪ ተባለ፡፡ ጉሮ ወሸባዬ ተባለ፡፡

 

በወቅቱ ዮሐንስን ያሳሳተው ሚዲያው ነው፡፡ እነዚህ ቡድኖች ከቆሼ በታች ያሉ ናቸው፡፡ በነኚህ ቡድኖች ላይ የምናስመዘግበው ውጤት እንዴት ነው ብሔራዊ ቡድኑ የሚለካው? ቡሩንዲን ስናሸንፍ ከነዚህ የተሻለ ሲመጣ እጅ እንሰጣለን በማሸነፉና በመሸነፉ አትለኩ በሚል ለመግለጽ ተሞክሮ ነበር፡፡ ኮንጎ እንደ ቡሩንዲ መጫወቻ ቦታ አልሰጠንም፡፡ እንቅስቃሴው እንደ ቡሩንዲ ተመሳሳይ ነው፡፡ ባለፈው ያሸነፍነው በዚሁ እንቅስቃሴ በመሆኑ ዛሬም ጉሮ ወሸባዬ ማለት ይገባናል፡፡ምክንያቱም እንቅስቃሴው ተመሳሳይ በመሆኑ፡፡ ዮሐንስ ባለፈው ሲያሸንፍ ስላሞገሱት ዛሬም ይህንኑ ይዞ መጣ፡፡ ለምንድነው ዛሬ የሚወቀሰው? ልናደንቀው ይገባል፡፡ ከጅማሬው እንቃሴው አገር የሚያዋርድ በመሆን በዚሁ እንዲቀጥል እኛም ጉሮ ወሸባዬ እያልን ማጀብ ነው ያለብን፡፡

ቡሩንዲና ሳኦቶሚን በዚያ አጨዋወት ሲያሸንፍ ይህ ነገር ትላንትና ወስዶ ገደል ስለከተተን ያሁኑን ማሸነፋ ይቅርብህ ብንለው ዛሬ እንዲህ ተዋርዶ ባላዋረደን ነበር፡፡ ለነገሩ ዮሐንስ ሳይሆን ሚዲያው ነው ያዋረደን፡፡ የሚገርመው ነገ ይሰድቡታል ምክንያቱም በነፈሰበት ነው የሚነፍሱት፡፡ባለፈው ሳምንት ስፀፍ የሆነ ፎቶ አቅርቤላችሁ ነበር፡፡ የዛሬ 33 ዓመት 1975 ከቶጎ ጋር ስንጫወት ዮሐንስ ተከላካይ ሆኖ እየጠለዛ በተወሰደበት ብልጫ አሁንም አሰልጣኝ ሆኖ እያስጠለዘ በተመሳሳይ ብልጫ ተወስዶብን ተሸንፈናል፡፡ ባለፈው በራዲዮ ኢትዮጵያውያኖች ቴክኒካል ጥሩ ስለሆኑ ኳስ ይዘው፣ ተቀራርበው ፣ተጋግዘው ቢጫወቱ ብልጫ እንወስዳለን በዚህ መንገድ ብንሄድ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ተረዳድቶ መጫወቱን ‹‹የአሮጊት ፉትቦል›› በሚል እንዲህ አይነት ነገር አልፈልግም ፡፡ ኳሱ በሜዳችን ከሁለት ጊዜ በላይ እንዲነካ አልፈልግም አለ፡፡

እሱ ባለው ለነ ጌታነህና ዳዊት በረጅሙ እየተጣለ ኳሱን የኮንጎ ተጫዋቾች እያገኙ እኛ ስንጠቃበት ነበር፡፡ እኛ የተበለጥነው በራሳችን ኳስ ነው፡፡ ኮንጎን በዚህ አጨዋወት እንዳልበለጥነው አይተናል፡፡ ሌሎቹን የምዕራብ አፍሪካ ቡድኖች በዚህ እንደማንበልጥ ይታወቃል፡፡ እኛ የምንችለው በመረዳዳቱ ነው መረዳዳቱን ደግሞ የአሮጊት ነው አልፈልግም አለ፡፡ ምን ይሻለናል? የአሮጊት የሚባለው እኛን የሚጠቅመን ኮነ አሰልጣኙ ሊቀበል ይገባዋል፡፡ አሁን ለማለፍ ኮንጎን 1ለ0ይብቃን እንበል ፡፡ ግን 1ለ0 መርተን በምንድነው የምናስጠብቀው? በግል እኮ አልቻልናቸውም፡፡ በቡድን እንዳንገባ አሮጊት ይሉናል፡፡ ከዚያ ውጪ የሆነ ነገር ልንገራችሁ፡፡

አሰልጣኛቸው እዚህ መጥቶ እንደሚያሸንፍና ትምህርት እንደሚሰጠን ተናገረ፡፡ እሱ በቃሉ ተገኝቷል፡፡ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በኛ እንቅስቃሴ እነሱ የተሻለ ነገር ስላላቸው ብልጫ እንደሚወስዱ ስለሚያውቁ አደረጉት፡፡ ባለፈው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ እጣ ሲወጣ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ሲባል የናይጄሪያው አሰልጣኝ ለምን እንደሳቀ ታውቃላችሁ? እነሱ ጠንካራ በሆኑበት ነገር ስለምንገባለት ነው፡፡ አሁን የሚያሳስበው የዛሬ መሸነፋችን ሳይሆን በዚህ አጨዋወት የት ድረስ ነው የምንሄደው? አሰልጣኙ እንደሆነ 33 ዓመት ስህተቱን ማረም ያልቻለ ነው፡፡ የሚገርመው ከዛሬውም አጨዋወት ያለመማሩ ነው፡፡ በጣም የገረመኝ በመሀበራዊ ደረ ገጸ ላይ አንድ የኮንጎ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ የምንሄደው ቆንጆ ሴቶችን ለማግኘት ነው ለማሸነፉ ችግር የለብንም ብሏል፡፡ አጠቃላይ ነገሩ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ጉሮ ወሸባዬ በሉ፡፡ ያለፈውና የአሁኑ አጨዋወት ምንም ለውጥ የለውም፡፡

The post Sport: ጉሮ ወሸባዬ በሉ!! – ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የዛሬው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውጤቶች

$
0
0

arsenal
united

Updated – (ዘ-ሐበሻ) 13ኛው ሳምንት የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ተካሂዷል:: የሳምንቱ መክፈቻ ጨዋታ ማን.ዩናይትድ ወደ ዋትፎርድ ሜዳ ወርዶ የተጫወተው ሲሆን ባለቀ ሰዓት በተገኘች ጎል 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል::

ፕሪሙሚየር ሊጉን በ13ኛው ሳምንት ጨዋታ ሲመራ የነበረው አርሰናል በዌስትብሮሚች 2ለ1 ተሸንፎ ወደ 4ኛ ደረጃ ወርዷል:: የዛሬው ጨዋታ ውጠቶች የሚከተሉት ናቸው::
ዋትፎርድ 1 – ማን.ዩናይትድ 2
ቸልሲ 1 – ኖርዊች 0
ኤቨእርተን 4 – አስቶንቭኢላ 0
ኒውካስትል 0 – ሌስተር ሲቲ 3
ሳውዝሃምፕተን 0 ስቶክ ሲቲ 1
ስዋንሳ 2 በርንማውዝ 2
ዌስት ብሮሚች 2 አርሰናል 1

ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሊቨርፑል 4ለ1 ተሸንፏል::

city

The post Sport: የዛሬው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውጤቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ ራሷ ባዘጋጀችው የሴካፋ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በብሩንዲ ተሸነፈች

$
0
0

ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) የመጀመሪያው ቀን ጨዋታዎች አሰተናጋጇ ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ፤ዛንዚባር በቡሩንዲ 1ለ 0 በሆነ በተመሳሳይ ውጤት ተሸንፈዋል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ዛሬ የተጀመረው የ2015 ሴካፋ ዋንጫ (2015 CECAFA) ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል::

ባለፈው ሳምንት በዲሞክራቲክ ኮንጎ በደርሶ መልስ ጨዋታ ተሸንፎ ከዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የተሰናበተው ብሄራዊ ቡድናችን አሁን ያለበት ወቅታዊ አቋም በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል::

ብሔራዊ ቡድኑ ራሱ ባዘጋጀው ውድድር ላይ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 1ለ0 መሸነፉ አሳሳቢ መሆኑን የሚናገሩት የስፖርት ተንታኞች በየፊናቸው መፍትሄ የሚሉትን ሃሳቦች በመሰንዘር ላይ ናቸው::

በኢትዮጵያ ዛሬ በተጀመረው የሴካፋ ዋንጫ በሩዋንዳ 1ለ0 ስትሸነፍ ዛንዚባርም እንዲሁ በብሩንዲ በተመሳሳይ 1ለ0 ተረታለች::

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ያደረጉት ጨዋታ ከረፍት በፊት 0ለ0 ተጠናቆ ሩዋንዳዎች በ54ኛው ደቂቃ ላይ ያገኟትን የቅጣት ምት ወደ ጎል ቀይረው አሸንፈው ወጥቷዋል::

የዛሬው ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን ውድድሩ በአዋሳና በባህርዳር ስታዲየሞች እንደሚቀጥሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መሸነፍ የተናደደ አንድ ደጋፊ በዘ-ሐበሻ የፌስቡክ ገጽ ስሜቱን ሲገልጽ እንዲህ ብሏል

“ተከብረሽ የኖርሺው በሠውነት ቢሻው
ዮሃንስ መጣና አረገሽ እንዳሻው !”

The post ኢትዮጵያ ራሷ ባዘጋጀችው የሴካፋ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በብሩንዲ ተሸነፈች appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይሌ ገ/ስላሴ ለእኔ |ጌታቸው ሽፈራው

$
0
0

የስፖርተኞች ስም የተለጠፈበት ልብስ ለብሼ አላውቅም፡፡ ግን በስማቸው የታተመ ልብስ ብለብስላቸው ከማያሳፍሩኝ መካከል ኃይሌ አንዱ ነበር፡፡ ገና በልጅነቴ በሬድዮ የሀይሌን ማሸነፍ ሰምቼ ዘልያለሁ፣ ተሸነፈ ሲባል በጣም አዝኜ አውቃለሁ፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለኃይሌ የተለየ ስሜት ነበረኝ፡፡ በቅርብ ግን ኃይሌ እየወረደብኝ መጣ፡፡ በቅርብ አመታት ኃይሌ ለምን ድሆችን (አካል ጉዳተኞችም፣ ህጻናትና አዛውንቶችን ጨምሮ) እንደማይረዳ ሲጠየቅ በተደጋጋሚ ‹‹ሰርተው ይብሉ!›› ሲል አዳምጬ ገርሞኛል፡፡ የሜቄዶንያው ቢኒያም ይህ የኃይሌ አባባል እንዴት ያናድደው?!
Haile_Gebrselassie_1
ከ3 አመት በፊት ግን የኃይሌ ስም ያረፈበትን ቲሸርት ብለብስ ኖሮ ይቆጨኝ እንደነበር የሚያስታውስ ነገር ሲናገር ሰማሁት፡፡ ‹‹ለምን ሰርተው አይበሉም!›› የሚለው ኃይሌ ሰርተውም የዋጋቸውን የማይከፈላቸው መምህራን ‹‹የስራ ዋጋችን ይከፈለን፣ ደመወዝ ይጨመርልን!›› የሚል ጥያቄ ሲያነሱ፣ እሱን የለመኑት ይመስል ይህን ጥያቄ ቅብጠት አድርጎ ሲወርፋቸው በሬዲዮ ሰማሁ፡፡ በሰይፉ ፕሮፍራም፡፡ ወቅቱ ኃይሌ ፕሬዝደንትነት ትልቅ ስልጣን መስሎት ‹‹ፕሬዝደንት›› ለመሆን የቋመጠበት ወቅት ነበር፡፡ መምህራን ደመወዝ ይጨመርልን ሲሉ መንግስት እንኳ እንዲህ የከፋ ዘለፋ አላወረደባቸውም፡፡

ያ ለመለስ ዜናዊ የተንሰቀሰቀው ኃይሌ፣ ለድሃ የሚራራ አንጀት የለውም፡፡ በዚህ ወቅት 15 ሚሊዮን ህዝብ ተራበ ቢባልም ‹‹ለምን ሰርተው አይበሉም!›› የሚል ይመስለኛል፡፡ እውነት ነው ኃይሌ የኢትዮጵያን ስም አስጠርቷል፡፡ በክፉ ቀን ስሟ ሲጠራ ግን መድረስ አይፈልግም፡፡ የእሱ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ ለጨፈሩት፣ ሲሸነፍ ላለቀሱት አሁን ደግሞ ስቃይ ላይ ለሚገኙት ያመጣው ፋይዳው ያን ያህል ነው፡፡ በክፉ ቀን አለመድረሱ አንድ ነገር ሆኖ ቁስላቸው ላይ ጨው ለሚጨምርባቸው ደገሞ ሜዳሊያው ምንም ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባለ በጭቆና ባለ ሀገር በተለይ ታዋቂ ሰዎች ልዩ ሚና ሊወጡ የግድ ነው፡፡ ለሚደግፋቸው ህዝብ የመኩላቸውን ሊወጡ ግዴታ አለባቸው፡፡ ያን ባያደርጉ እንኳ ዝምታ ከምንም ይሻላል፡፡ ከስርዓቱ ጋር ከቆሙ፣ ስርዓቱ በስንት ጊዜ አንዴ ‹‹ችግር›› ሲደርስበት እየተነፋረቁ እድሜ ልኩን እንዳይሰራ፣ ቢሰራም ለውጥ እንዳያመጣ በስርዓቶች የታሰረ ህዝብ ላይ ‹‹ለምን ሰርቶ አይበላም›› እያሉ ካላገጡ ክብርና ዝናቸውን መቀበል ይከብደኛል፡፡ ለእነ መለስ በአደባባይ እያለቀሰ፣ አደባባይ ላይ የወደቁትን አዛውንቶችና ህፃናት ‹‹ለምን አይሰሩም›› የሚለው ኃይሌም ለእኔ ክብሩን ንዷል፡፡ አሁን ድሮ በምናውቀው ሩጫው ሳይሆን የሥርዓቱ አሯሯጭም ሆኗል፡፡ ከስርዓቱ ጋር እየተሞዳሞዱ ባለሃብት በመሆን ከሆነ ህንዶችም፣ ቱርኮችም፣ ግብፆችም፣ ህወሓቶችም፣ ብአዴኖችም…..አሉ፡፡ በዚህ ኃይሌ የተለየ አይሆንም፡፡

በአጠቃላይ ኃይሌ ለህዝብ፣ ለክብሩ የሮጠ አይመስለኝም፡፡ እናም ጫማውን ቢሰቅል ባይሰቅል ጉዳዬ አይደለም፡፡ በሚቀጥለው አመት ተመልሻለሁ ብሎ ሪኮርድ ቢሰብር፣ ቢያሸንፍ፣ በታዕምር በ90፣ በ103…..አመቱ ቢሮጥ….ከማጨብጨቤ በፊት የሚታየኝ እሱ ለኢትዮጵያውያን ሳይሆን ለጨቋኝ ስርዓት አጨብጫቢ መሆኑ ነው፡፡ የሚታወሰኝ በህዝብ ላይ የሚቀልድ፣ ለስርዓቱ እንባ፣ ለህዝብ የአዞ እንባ እንዳለው ነው፡፡ እናም ኃይሌን፣ ለማስታወስ፣ ለማድነቅም……ኃይሉም ሞራሉም የለኝም፡

The post ኃይሌ ገ/ስላሴ ለእኔ | ጌታቸው ሽፈራው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport |ኬቪን ደብሩኒ የሲቲዎች አዲሱ አለኝታ

$
0
0

 

ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽል አማካዩ ኬቪን ደብሩኒ በቀድሞው ክለቡ ዎልስበርግ ቆይታው ያለፈው ሲዝንን ያጠናቀቀው በባየር ሙኒክ ስኳድ የሚገኙ በርካታ ወርልድ ክላስ ፉትቦለሮችን በመብለጥ የጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር ኮከብ ተጨዋች በመባል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ከሁለት ዓመታት በፊት በቼልሲ ቆይታው ሌላው ቀርቶ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ መደበኛ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን የሚያስችለውን አስተማማኝ ብቃትን ለመያዝ መቸገሩን ከግንዛቤ በማስገባት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ የ24 ዓመቱ ቤልጅየማዊ ኢንተርናሽልን በእጃቸው ያስገቡበት ውሳኔያቸው ፍሬያማ መሆን መቻሉን ተጠራጥረውት ነበር፡፡ በተለይም በበርካታዎች ዘንድ ከዚህ በፊት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተሳትፎው ስኬታማ ለመሆን አለመቻሉን ከግንዛቤ በማስገባት ማንችስተር ሲቲ በታሪኩ አቻ በማይገኝለት ከፍተኛ የግዢ ሂሳብን ማለትም 54 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ለዎልስበርግ መክፈሉ ለደብሩኒ ብቃት የሚበዛበት ዋጋ ነው የሚል አመለካከታቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል፡፡

Manchester City v West Ham United - Premier League

ሆኖም ግን ደብሩኒ ለማንችስተር ሲቲ በእስካሁኑ ሲዝን በመስጠት ላይ ያለው ግልጋሎት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ መገኘት ፔሌግሬኒ ያወጡበት ከፍተኛ የግዢ ሂሳብን በሜዳ ላይ ባለው ውጤታማ ፉትቦሉ በአግባቡ ለመክፈል እንደሚችል የጠቆመ ሆኗል፡፡ ይህንን በማመንም የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሰጠው መግለጫው ‹‹በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ካሉት ተጨዋቾች በምርጥ ብቃቱ የቅድሚያው አድናቆት የምገልፅለት ተጨዋች ኬቪን ደብሩኒ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለዎልስበርግ በተሰለፈባቸው 18 ወራት በሜዳ ላይ ሁሉንም አይነት ስኬታማ ተግባሮን በመፈፀም ሲያስገርመኝ ዘልቋል፡፡ ለማንችስተር ሲቲም በዘንድሮው ሲዝን ይህንን ውጤታማ ፉትቦሉን በተሟላ ሁኔታ ሲደግመው ማየቴ በደብሩኒ አስገራሚ ብቃቶች መገረሜን እንድቀጥል ምክንያት ሆኖኛል፡፡ በእኔ አመለካከትም የዘንድሮው ሲዝን ከጀመረበት ያማረ ታላቅ ፐርፎርንሱ አንፃር ለማንችስተር ሲቲ የተሰለፈበት የመጀመሪያውን ሲዝን የሚያጠናቅቀው በእንግሊዝ ፉትቦል ያሉትን ሁሉንም አይነት የኮከብ ተጨዋችነት ስያሜዎችን በማግኘት ይሆናል፡፡ ዎልስበርግ ደብሩኒን በመሸጡ ደግሞ ምትክ የማያገኝለት ቁልፍ ተጨዋቹን ለማጣት ተገድዷል፡፡ በዛኑ መጠን ግን የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሬኒ እውነተኛ የማሸነፊያ መሳሪያቸውን በእጃቸው ለማስገባት ችለዋል፡፡›› ብሏል፡፡

በእርግጥም ደብሩኒ ከማንችስተር ሲቲ የጨዋታ ስታይል ጋር በፍጥነት በመዋሃድ ለአዲሱ ክለቡ በተሰለፈባቸው በእስካሁኑ ግጥሚያዎች 5 ወሳኝ ጎሎችን ከማስቆጠር አልፎ አራት የጎል አሲስቶችን በስሙ ማስመዝገቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሚገኙት ተጨዋቾች ምርጥ ብቃቱ አቻ የማይገኝለት በሚል በብዙዎች ዘንድ እንዲወደስ ምክንያት ሆኖታል፡፡

ደብሩኒ ከዚህ በፊት ለዎልስበርግ በአብዛኛው የሚሰለፈው የ10 ቁጥር ሚናን በመያዝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ለማንችስተር ሲቲ ከፈረመ ወዲህ የተጫዋቹ ሁለገብ ብቃት ባለቤትነትን በመገንዘብ ቺሊያዊው አሰልጣኝ በተደራቢ አጥቂነት ብቻ ሳይሆን በግራና በቀኝ ክንፎች በኩልን በመጠቀም የቡድናቸው አጠቃላዩ የማጥቃት እንቅስቃሴን ከፍተኛ ኃይልን እንዲያስገኝለት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማንችስተር ሲቲ በኢትሃድ ስቴዲየም የስፔኑ ኬቪያን 2ለ1 በሆነ ውጤት በረታበት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ውስጥ በፊት አጥቂ ሚና ተጠቅመውበታል፡፡

kevin de brunye

ይህ ቡድናቸው ወሳኙ የማሸነፊያ ጎልን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረትን በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት በግጥሚያው ሂደት የፈፀሙት ታክቲካል ውሳኔያቸው ፍሬያማ ሆኖላቸውም ደብሩኒ የማንችስተር ሲቲ የዘንድሮ ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊግ ዘመቻ ወደ ትክክለኛው መስመር ያስገባላቸውን ወሳኙ የማሸነፊያ ጎልን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል፡፡ በዚህም በማንችስተር ሲቲ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾን የቡድናቸው የዘንድሮ ሲዝን አጠቃላዩ ዘመቻ የሚወሰነው ከኬቪን ደብሩኒ ጥሩ ብቃት ጋር በተያያዘ ምክንያት እስከማለት በመድረስ ላይ ናቸው፡፡ ይህንን እምነትን በማሳደር በተለይም እንግሊዛዊያን የቡድኑ ግብ ጠባቂ ጆ ሀርት በሰጠው መግለጫው ኬቪን ደብሩኒን ‹‹የቡድናችን የስኬት መሳሪያ›› በማለት ገልፆታል፡፡ ማንችስተር ሲቲ በአሁኑ ወቅት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ዋነኛ ተቀናቃኙ አርሰናልን በጎል ክፍያ በልጦ በመሪነት ስፍራ ላይ ለመቀመጥ እንዲችልና ከእስካሁኑ ሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ማጣሪያ ግጥሚያዎቹ ሁለቱን ድል እንዲቀናው ግንባር ቀደሙን አስተዋፅኦን ካበረከቱለት ተጨዋች ግንባር ቀደሙ ደብሩኒ መሆኑን በማመን ሀርት አስተያየቱን ሲቀጥል፡- ‹‹… በእኔ አመለካከት ኬቨን ደብሩኒ ከክለባችንም አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የእስካሁኑ እጅግ ምርጡ ተጨዋች ለመሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡ በእርግጥ ስኳዳችን ሌሎችንም በርካታ ብቃታቸው አስተማማኝ የሆኑ ተጨዋቾችን ይዟል፡፡ በተለይም ሌሎቹ አዲስ ፈራሚዎችን ከሆኑት ውስጥ ራሂም ስተርሊንግና ኒኮላስ አታሜንዴ ለቡድናችን የጨዋታ ስታይል ጋር በፍጥነት ለመዋሃድ ችለው የቡድናችንን ጥንካሬን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር የቻሉበት አስተዋፅኦን እያከረክቱልን ይገኛሉ፡፡ ከሁሉም ግን ኬቨን ደብሩኒ እጅግ የተለየ አይነት ተጨዋች ሆኖብኛል፡፡ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ለቡድናችን ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ጎልን በማስቆጠር ወይም ወሳኝ የጎል አሲስትን በስሙ በማስመዝገብ ማሳለፉን የተለመደ ባህሉ ማድረጉ በከፍተኛ ደረጃ እንድገረምበት ምክንያት ሆኖኛል፡፡ ባለፈው ሲዝን የጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር ኮከብ ተጨዋችነት ስያሜን ማግኘቱን ባወቅም የያዘው ብቃት ግን እንደ አሁኑ ሁሉ ፍፁም እንከን የማይወጣለት ይሆናል በሚል ግምት ግን በጭራሽ እንዳልነበረኝ ከማመን አልቆጠብም›› በማለት ተናግሯል፡፡

ከማንችስተር ሲቲ ቁልፍ ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ሆኖ የዘንድሮውን ሲዝንን የጀመረው እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ በሌሎች ጉዳዮችም ዙሪያ አስተያየቱን ሰሞኑን ሰጥቷል፡፡ በተለይም በግሉ በያዘው ባህሪን በማስመልከት ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው ‹‹…የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ለመፈፀም ሁሉንም አይነት ከፍተኛ ጥረቶችን የማደርግበት ባህሪ እንዳለኝ አምናለሁ፡፡ ይህ ባህሪዬ በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሌ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በህይወቴ በማደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ጭምር ሲደገም መታየቱ የተለመደ መሆኑን እኔን በቅርበት የሚያውቁኝ ሰዎች ምስክርነታቸውን ይሰጡኛል፡፡ ለእያንዳንዱ ግጥሚያዎች አስቀድሜ ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠት በተጠናከረ ሁኔታ ልምምድን በመስራት ባህል አለኝ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ሰሞን የስፔኑ ኬቪያን ባስተናገድንበት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ከፍተኛ ወሳኝነት ያለውን ድልን ለመቀዳጀት ችለናል፡፡ ሆኖም ግን እኔ በድሉ ከመኩራራት ይልቅ በሳምንቱ መጨረሻ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ለማናደርገው ግጥሚያ በሙሉ ትኩረትን መስጠት የጀመርኩት ሐሙስ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ አንስቶ ነው›› በማለት ነው፡፡

Kevin and sterling

ሀርት በዚሁ መግለጫው ላይ ቡድናቸው የዘንድሮው ሲዝን አጀማመሩን በመዳሰስ አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹የዛሬ ዓመት ከነበረን አጀማመር አንፃር የዘንድሮው ሲዝን አጀማመራችን በመልካም ጎኑ ሊጠቀስ የሚገባው ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህንን ስል ግን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት በአሁኑ ወቅት ያለን አቀማመጥ በሰፊው ሲዝን የሚፈጠረው ሁኔታን የመወሰን ኃይል እንደማይኖረው በማመን ነው፡፡ በእኔ አመለካከትም የዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክር እስከመጨረሻው ጥቂት ሳምንታት ድረስ የተካረረ ፉክክር የሚያስተናግድበት ይሆናል፡፡ ይህንን ለመቋቋም የምንችለው ደግሞ ከሃያላን ክለቦች ጋር ለምናደርጋቸው ግጥሚያዎች ብቻ ሳይሆን በሊጉ ከሚገኙት እያንዳንዱ ክለቦች ጋር የሚጠብቀን ግጥሚያዎችን በሙሉ ትኩረትን በመስጠት ወደ ሜዳ ለመግባት ስንችል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ለምሳሌ የእሁዱ የማንቸስተር ደርቢን የጀመርነው ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሳይለየን ነው፡፡ ይህንን በቀጣይ የሊጉ ግጥሚያዎችም በተሟላ ሁኔታ የመድገም ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህንን በአግባቡ ለመፈፀም ስንችል በቀጣዮቹ አምስትና ስድስት ወራት የሚጠብቀን የተጠናከረ ፉክክርን በመቋቋም ማንቸስተር ሲቲን ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር የማገናኘት አላማችንን በአግባቡ ለመፈፀም እንችላለን›› በማለት ነው፡፡

ሀርት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መሳተፍ የጀመረው ገና የ19 ዓመት ወጣት እያለ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዕድሜው 28 በመድረሱ በዛ ጊዜ ከነበረው አንፃር በአሁኑ ወቅት የተሟላ ብቃት ያለው ግብ ጠባቂ መሆን መቻሉን በማመን በመቀጠልም አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹የግብ ጠባቂዎች ብቃት የሚለካው የሚቃጣባቸው የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን ለማዳን ተሰጥኦአቸው አኳያ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ግብ ጠባቂዎች ከኋላ ሆነው በሚያስተላልፉት መመሪያቸው የቡድናቸው የተከላካይ መስመርን የማደራጀትና የማነቃቃት ኃላፊነት ጭምር አለባቸው፡፡ ይህንን ኃላፊነትን ከአንዱ ዓመት ወደ ሌላው በተሸጋገርኩ ቁጥር ያሳደኩት ተሰጥኦም ከኋላ ሆኜ ለቡድናችን በምሰጠው መመሪያዎች እንዲነቃቁ የማስቻል ተሰጥኦን ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ዕድሜዬ እያደገ ሲሄድ አጠቃላዩ የግጥሚያችን እንቅስቃሴን በአግባቡ የማነብበት ብቃቴም በማዳኑ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና ለማንችስተር ሲቲ በምሰለፍባቸው ግጥሚያዎች ላይ በፊቴ ከሚገኙት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ጋር የበለጠ ባማረ ሁኔታ የመግባባት ደረጃዬ ሊያድግልኝ ችሏል ለማለት እችላለሁ›› ብሏል፡፡ የማንችስተር ሲቲው ቁጥር አንድ በአሁኑ ወቅት የዓለም ፉትቦል ከሚገኙት ግብ ጠባቂዎች በምርጥ ብቃታቸው ሶስቱን እንዲጠቅስ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው የባየር ሙኒኩ ማኑኤል ኢዬር፣ የማንቸስተር ዩናይትዱ ዳቪድ ዳሂአና የጁቬንቱሱ ጂያን ሉዊስ ቡፎንን የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች በማድረግ ነው፡፡

The post Sport | ኬቪን ደብሩኒ የሲቲዎች አዲሱ አለኝታ appeared first on Zehabesha Amharic.


Sport: ‹‹የምኖረውና የማስበው ስለ አሁኑ ብቻ ነው›› ሜሲ – (አዲስ ቃለምልልስ ከያሁ ስፖርት ጋር)

$
0
0

የትናንት ምሽቱን የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሳይጨምር ለአራት ጊዜው የዓለም ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ የዘንድሮ ሲዝን በመልካም ጎኑ የሚጠቀስለት አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ከጥቂት ሳምንታት በፊት በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ከሜዳ ለመራቅ ከመገደዱም አልፎ በጥሩ ጤንነት ሆኖ ግጥሚያዎችን የሚያደርግበት ጊዜ መች እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኖ የማያውቀው ነገር የለውም፡፡ የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ኢንተርናሽል በአሁኑ ወቅት ከጉዳቱ ለማገገም በተጠናከረ ሁኔታ ጥረትን በማድረግ ላይ ባለበት ሁኔታ ስሙን ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጋር በስፋት የሚያያዙት ዘገባዎች በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
mesi2
ከዚህ በፊትም የሜሲ ስም ቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲና ማንችስተር ዩናይትድን ከመሳሰሉት የእንግሊዝ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጭምጭምታ ጋር አብሮ መነሳቱ የተለመደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የእስካሁኑ የፉትቦል ህይወቱን በባርሴሎና ማሊያ ያሳለፈው ሜሲ አስተያየቱን ከመስጠት ተቆጥቦ መዝለቁ ይታወቃል፡፡ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ከያሆ ስፖርት ድረገፅ ጋር ባደረገው ሰፊ ቃል ምልልሱ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ‹‹ወደፊት ከስፔን ውጪ በሌላ ሀገር ትልቅ የሊግ ውድድር የመሳተፍ ፍላጎት ይኖርሃል›› በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ሜሲ ምላሹን የሰጠው ‹‹ወደፊት ስለሚፈጠረው ጉዳይ አስቀድሜ የማስብ ባህል የለኝም፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜም የምኖረውና የማስበው የአሁኑ ህይወቴን ብቻ ነው፡፡ የማውቀው ለበርካታ ዓመታት ከባርሴሎና ባለመለየት ያማረ ህይወትን አሳልፌያለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በባርሴሎና ባለኝ የተረጋጋ ህይወት ሙሉ ለሙሉ ደስተኛ ነኝ ከሁለት ልጆና ከአጠቃላዩ ቤተሰቦቼ ጋር በአሁኑ ወቅት አስደሳች ህይወትን በመኖር ላይ ነኝ፡፡ ተስፋ የማደርገውም ይህ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥልልኝ ብዬ ነው፡፡››
ይህንን የሜሲ መግለጫን ተከትሎም የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሚ በሰነዘሩት አስተያየት የቡድናቸው ቁልፍ ተጨዋች ‹‹በየጊዜው ስሙ ከተለያዩ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጭምጭምታዎች ጋር ሲያያዝ መስማት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰለች ሆኖብኛል›› የሚል መግለጫቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለይም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አብዛኛዎቹ የስፔን ሚዲያዎች ሊዮኔል ሜሲ በጉልበቱ ላይ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም እያደረገው ከሚገኘው ጥረት በተጓዳኝ ባርሴሎናን በዘንድሮ ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የመልቀቅ ሃሳቡን ከመያዝም አልፎ ቀጣዩ ክለቡ ማን መሆን አለበት የሚለውን ጉዳይ ልዩ ትኩረትን ሰጥቶበት በማመዛዘን ላይ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመሳተፍ ፍላጎቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያደገ ሄዷል በሚል የቀረበው ዘገባ ለባርሴሎናው ፕሬዝዳንት የሚያበሳጭ ሆኖባቸዋል፡፡

ባርቶሜ በአንርጀንቲናዊው ኮከብ ዙሪያ እንደዚሁም አይነቱ ጭምጭምታዎች መሰማታቸውን የሚጠሉበት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የጭምጭምታዎቹ መሰማት ከጉዳቱ በማገገም ጥረቱ ሙሉ ትኩረትን ከመስጠት እንዲቆጠብ የበኩሉን ስነ ልቦናዊ መረበሽን ይፈጥርበታል በሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑን ከመጠቆምም አልተቆጠቡም፡፡

ባርቶሜ በጉዳዩ ዙሪያ በያዝነው ሳምንት ኤይቲ ቲቪ ለተባለው ቻናል መግለጫቸውን የሰጡት ‹‹ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎናን የመልቀቅ ፍላጎት ይኖረዋል ብለው የሚያስቡት ሰዎች ራሳቸውን ላልተፈለገ የግራ መጋባት መንፈስ ያጋለጡት ብቻ ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም ራሱ ሜሲ ብቻ ሳይሆን ወላጅ አባቱ በተደጋጋሚ የሚናገሩት ባርሴሎናን የመልቀቅ ሃሳብ በጭራሽ ሊኖረው እንደማይችል ነው፡፡ ከባርሴሎና ጋር ያለው ወዳጅነት እንዳለፉት በርካታ ዓመታት ሁሉ እጅግ ያማረና የተዋበ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ከሜሲ ባሻገር የቤተሰቡ አባላት በጠቅላላ ከክለባችን ጋር እርስ በርስ የተዛመዱ ናቸው ለማለት እችላለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከባርሴሎና ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀው ከሶስት ዓመታት በኋላ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ለሜሲ አዲስ ኮንትራት ለመፍቀድ የምንጣደፍበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖረንም፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን በታክስ ጉዳይ ከስፔን መንግሥት የተነሳበትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ብቻ ተጨባጭነት የሌላቸው ዘገባዎች እየቀረቡበት መሆኑ የክለባችን አባላት የሚያበሳጭ ሆኖብናል፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነቱ ከሃቅ የራቀ ጭምጭምታ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም በሚያደርገው ጥረት ላይ ሙሉ ትኩረት እንዳይኖረው የሃሳብ መበታተን ችግር እንዳይፈጥርበት ስጋትን ያሳደረብን ሆኖናል›› በማለት ነው፡፡

mesi

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት በዚሁ መግለጫው ላይ በሌላው የቡድናቸው ተጨዋች ማለትም ብራዚላዊው ኢንተርናሽል ኔይማር ኮንትራት ሁኔታ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን የሰጡት ‹‹የኔይማር ጉዳይ ከሜሲ አንፃር በብዙ መልኩ የተለየ በመሆኑ በዘንድሮው ዓመት አዲስ የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ልናቀርብለት አቅደናል፡፡ አስቀድመን ለኔይማር ቃል በገባንለት መሰረት ከወዲሁ የኮንትራት ማራዘሚያ ድርድሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተግባራዊ በመሆን ላይ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው የኔይማር ተጨመሪ በርካታ ዓመታት ከክለባችን መሰለፍን እንዲቀጥል ከፍተኛ ጉጉትን አሳድረን መዝለቃችንን ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ከቡድናችን እጅግ ቁልፍ ተጨዋቾች ውስጥ መሆኑን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያዘው አጠቃላይ አስተማማኝ አቋሙ በቀላል ለመረዳት የምንቸገር አይሆንም በማለት ነው፡፡

‹‹በእርግጥ ኔይማር በቅርብ ሳምንታት ወዲህ ባርሴሎና በተከታታይ ግጥሚያዎች ድልን ለማስመዝገብ እንዲችል ከፍተኛ አስተዋፅኦን እያበረከተለት ይገኛል፡፡ የቀድሞው የሳንቶ ክለብ ስታር ባለፉት ዓመት የባርሴሎና ግጥሚያዎቹ አምስት ጎሎችን በስሙ ለማስመዝገብ መቻሉ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ባለፉት ስድስት የባርሴሎና የሁሉም ውድድሮች ግጥሚያዎች ላይ በአጠቃላይ 5 የጎል አሲስቶችን በስሙ ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ከሜዳ ከራቀ ወዲህ ለባርሴሎና ውጤታማ ተግባርን በመፈፀም የ23 ዓመቱ ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ግንባር ቀደሙ ስፍራን ለመያዝ መቻሉን ነው፡፡ ከኔይማር ባሻገር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባርሴሎና አይበርን 3ለ1 በፈታበት የስፓኒሽ ላሊጋ ግጥሚያው ሀትሪክ የሰራው ኡራጓዊው አጥቂ ሉዊስ ስዋሬዝ በጥሩ አቋም መገኘት የካታላያኑ ክለብ ደጋፊዎች የሜሲ ጉዳት ከሜዳ መራቅ በቡድናቸው ውጤታማነት ላይ ያስከተለው ያንን ያህል ጎልቶ የሚጠቀስ ችግር አለመኖሩን እንዲገነዘቡት የረዳቸው ቢሆንም የአብዛኛዎቹ የባርሴሎና ደጋፊዎች ከፍተኛ ጉጉት ግን ቡድናቸው በቀጣዩ ወር ከሪያል ማድሪድ ጋር ለሚያደርገው የዘንድሮ ሲዝን የመጀመሪያው ኤልክላሲኮ ፍልሚያ የሜሲ በጥሩ ጤንነት ሆኖ መድረስ መቻልን ማየት ነው፡፡ ሜሲ በሰሞኑ ቃለ ምልልሱ ግን ከጉዳቱ አገግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰለፍበት ግጥሚያ የትኛው እንደሚሆን ለመገመት መቸገሩን ተናግሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቲያጎና ማቲዬ የሚል መጠሪያ ያላቸው ሁለት ልጆችን ያፈራው ሜሲን በቃለ ምልልሱ ላይ ከተነሱለት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ሁለት ልጆች አባት መሆኑ በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሉ ዙሪያ ያስከተለበት ለውጥ አለ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ለጥያቄው ምላሹን የሰጠው እንደማንኛውም አባት ሁሉ ልጆቼን የማሳድግበት ተጨማሪ ኃላፊነት ያሸከመኝ ሆኗል፡፡ ይህ ግን በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሌ እንደወትሮው ሁሉ የማደርገው ሙሉ ትኩረትን የቀነሰብኝ አልሆነም›› በማለት ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጨዋታው ሚና ስለመቀየሩና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ላደረገው ቃለ ምልልስ ይህንን ይመስላል፡፡

ጥያቄ፡-ስለ አሁኑ የጨዋታ ሚናህ ምን አስተያየት አለህ?
መልስ፡- በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ከቡድናችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ለማስገኘት ይችላል ብለን ባመንበት መልኩ የጨዋታ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ባህል አለን፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሼ ኳስ የማዘጋጀት ተግባርን የምፈፅምበት እንዲሁም ጎሎችን በማስቆጥርበት ቦታ ላይ የመገኘት ኃላፊነቱን የምፈፅምበት አጋጣሚዎችም አሉኝ፡፡ እንደዚህ አይነቱ በበርካታ ተግባሮች ላይ በመሳተፍ የጨዋታ እንቅስቃሴን ማድረግ የባርሴሎና የተለመደ ባህል በመሆኑ አዲስ ተቀይሯል የምለው የጨዋታ ስታይል ለውጥ ያንን ያህል የለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሚጫወትበት የእግርኳስ ትውድል አብረህ መጫወት ላይ መሆንህ ችሎታህን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር እንድትችል ያደረገልህ ድጋፍ አለ?
መልስ፡- እንደዚህ አይነት አመለካከት በሰዎች ዘንድ መኖሩ ያስገርመኛል፡፡ ምክንያቱም እኔ በግሌ ራሴን ከክርስቲያኖ ሮንልዶ ጋር ፉክክርን በማድረግ ላይ ነኝ በሚል የቆጠርኩበት ወቅት የለኝም፡፡ በእኔ ግምትም እሱም (ክርስቲያኖ ሮናልዶን) ከእኔ ጋር ፉክክር በማድረግ ላይ ነኝ የሚል አመለካከትን መያዙን እጠራጠራለሁ፡፡ የእኔ ሙሉ ትኩረት ለምሰለፍበት ቡድን ውጤታማነት በተቻለኝ አቅም ሁሉ ጥረትን ማድረግ መቻል ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ መንፈሴን ወደፊትም ቢሆን ልቀይረው እንደማልሻ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከአገርህ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያለህ ግንኙነት ምን ይመስላል? ሰዎች እንደሚናገሩት ሁሉ በበርካታ ውጣ ውረዶች የተሞላ ነው?
መልስ፡- አጀርንቲናዊያን በአብዛኛው ከፍተኛ የሆነ የእግርኳስ ፍቅር ያላቸው በመሆናቸው የአገራችንን ብሔራዊ ቡድንን በትልቅ ኢንተርናሽናል ውድድር ደረጃ በመወከል ለምንጫወተው ተጨዋቾች ከፍተኛ የሆነ ክብርን የሚሰጡበት አመለካከትን ተላብሰዋል ለማለት እችላለሁ፡፡ በዚሁ መልኩ ግን በጣም ጥቂቶች ለአገራችን ብራዊ ቡድን ስኬታማነት በሜዳ ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረትን በምናደርግበት ወቅት ጩኸትን በማሰማት ሊሰድቡን የሚሞክሩ አሉ፡፡ሆኖም ግን እኔ በግሌ ሁሌም የአገራችንን የፉትቦል አፍቃሪዎች በእኩል አይን የመመልከት ባህል አለኝ፡፡

ጥያቄ፡- በአመጋገብ ስርዓትህ ላይ መጠነኛ ለውጥን አምጥተሃል ስለሚባለው ነገር የምትነግረን ይኖርሃል?
መልስ፡- ጠንካራ ሰውነት እንዲኖረኝ ምንም አይነት ጠቀሜታን የማይሰጡን አንዳንድ የምግብ አይነቶችን ከመቀነስ በስተቀር በአመጋገብ ስርዓቴ ላይ ያመጣሁት አጠቃላይ ለውጥ የለም፡፡ ከሌሎች ፕሮፌሽናል ፉትቦለሮች በዚህ ጉዳይ እለያለሁ የሚል እምነት የለኝም፡፡

ጥያቄ፡- በሌላ አገር የሊግ ውድድር ለመሳተፍ የምትችልበት አጋጣሚ ይኖርሃል?
መልስ፡- ወደፊት ስለሚፈጠረው ነገር ከወዲሁ አስቀድሜ በማሰብ አስተያየቴን ለመስጠት አልሻም፡፡ የምኖረውና የማስበው በአሁኑ ወቅት ስላለኝ ህይወት ብቻ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በስፓኒሽ ላ ሊጋ ውድድር ተሳትፎና በባርሴሎና ክለብ መገኘቴን ብቻ ነው የማውቀው፡፡ የማስበው በቅር ስለሚፈጠሩ አውነታዎች ብቻ መሆኑን በድጋ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከዚህ በፊት የግል ህይወትህን የያዘው መፅሐፍን ማንበብህን መጀመርህ ተነግሮን ነበር፤ አሁንስ መፅሐፍን አንበብህ ጨርሰኸዋል?
መልስ፡- ስለ እውነቱ ለመናገር መፅሐፉን አንብቤ አልጨረስኩትም፡፡ ምክንያቱም ባለፈው ታሪክም ሆነ ወደፊት ከበርካታ ዓመታት በኋላ ስለሚፈጠረው ነገር ማሰብን አልወድም፡፡

ጥያቄ፡- በሜዳ ላይ በምታደርገው ፉትቦልን ይበልጥ እንዲደሰት የምትጓጓው እነማን ነው የምትሰለፍበት ቡድን ደጋፊዎችን ወይስ ቤተሰቦችህን?
መልስ፡- ወደ ሜዳ የምገባው በውጤታማ ፉትቦሌ የማስደስተው ሰው እንዲኖረኝ መመኘትን ዋነኛ አላማዬ በማድረግ አይደለም፡፡ እግርኳስን በከፍተኛ ደረጃ ስለምወደው እጫወታለሁ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ ሜዳ ይዤው የምገባው ዋነኛ አላማ ለምሰለፍበት ቡድን ስኬታማ ተግባርን ለመፈፀም የተቻለኝን ሁሉ ጥረትን ማድረግ መቻል ነው፡፡

ጥያቄ፡- በቅርቡ ጉዳት ሲደርስብህ ለመጀመሪያ ጊዜ በውስጥህ ያሳደርከው ስሜት ምንድነው?
መልስ፡- ከዚህ በፊት ጉዳት ሲደርስብኝ ከነበረኝ ሁኔታ በተለየ ለየት ያለ ስሜትን አሳድሬያለሁ፡፡ ምክንያቱም ጉዳቱ አንድ መደበኛ ግጭት አለመሆኑንና አስከፊነት ያለው መሆኑን ያወቅኩት ገና ከዛኑ ጊዜ አንስቶ ነው ለጉዳት መጋለጥ ለማንኛውም ፕሮፌሽናል ስፖርታዊ ትልቁ ሃዘንን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን በጠንካራ ስነ ልቦና ሆኜ በፍጥነት ለማገገም የሚረዳኝን እንቅስቃሴዎችን ላይ በመሆኔ ጥረቴ ፍሬያማ እንደሚሆንብኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከሪያል ማድሪድ ጋር ለሚረገው የዘንድሮው ሲዝን የመጀመሪያው ኤልክላሲኮ እደርሳለሁ የሚል ግምት አለህ?
መልስ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እርግጠኛ ሆኜ አስተያየትን መስጠት ይከብደኛል፡፡ ሙሉ ትኩረት የህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡንን መመሪያን በማክበር ሁሉንም አይት የማገገም ጥረቶችን በማድረጉ ተግባር ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን በጥሩ ጤንነት የምገኝበት ወቅትን በትክክል ለመገመት የሚችሉት በማገገም ጥረቴ ከጎኔ ሳይለዩ ድጋፍን እየሰጡን በሚገኙት የህክምና ባለሙያዎች እንጂ እኔ ልሆን አልችልም፡፡

ጥያቄ፡- ባርሴሎና ያለፈው ሲዝንን የሶስት ትላልቅ ውድድር ዋንጫዎች ድሎችን ዘንድሮ ይደግመዋል የሚል እምነት አለህ?

መልስ፡- የውድድር ዘመኑ ገና የመጀመሪያው ሶስት ወራት ያላለቀ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም የሲዝኑ ሰፊው አካል ያለው ከፊታችን ያለው ስድስት ሰባት ወራት ውስጥ ነው፡፡ ካለፈው ሲዝን በትሪፕል ዊነርነት(ሶስት ዋንጫ) ድል ለማጠናቀቅ የቻሉት አብዛኛዎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች እስካሁንም ድረስ በስኳዳችን የሚገኙ በመሆናቸው ግን በተሳተፍንባቸው እያንዳንዱ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት እንችላለን የሚል ሙሉ እምነትን ለማሳደር የምንቆጠብበት ምክንያት አይኖረንም፡፡

የውድድር ዘመኑን የጀመርነውም በጥሩ አቋም ሆነን መሆኑን አምናለሁ፡፡ ከመጀመሪያዎቹ ዘጠን የስፓኒሽ ላ ሊጋ ግጥሚያዎች በኋላ በደረጃው ሰንጠረዥ ከዋነኛ ተቀናቃኞቹ ሪያል ማድሪድ እኩል 21 ነጥቦችን መያዛችን ከግንዛቤ ሲገባም የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረን የነጥብ ድምር አንፃር የዘንድሮው የተሻለ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ያለፈው ሲዝን እስኪጋመስ ድረስ በቡድናችን ላይ የታየው የአቋም አለመረጋጋት ችግር ዘንድሮ ሲደገም አልታየም፡፡ ከዚህ አንፃር የዘንድሮ ሲዝንን ለሌላ የትሪፕል ዊነርነት ድል ለመብቃት በማለም የማናካሂድበት ምክንያት አይኖርም፡፡

The post Sport: ‹‹የምኖረውና የማስበው ስለ አሁኑ ብቻ ነው›› ሜሲ – (አዲስ ቃለምልልስ ከያሁ ስፖርት ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: በቼልሲ ዙሪያ የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ |ጉስ ሂድኒክ የቼልሲ ስራን ለመያዝ ተዘጋጅተዋል

$
0
0

ቼልሲ ያለፈውን የውድድር አመት ያጠናቀቀው ሁለት የዋንጫ ሽልማቶችን በማግኘት ማለትም ለፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር በመብቃትና የካፒታል ዋን ውድድር ድልን በመቀዳጀት ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በእነዚህ ሁለት ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን የማግኘት ተስፋው ዝቅተኛ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ከስቶክ ሲቲ በመለያ ምት ተሸንፎ የካፒታል ዋን ውድድር ዘመቻውን ወደ ሩብ ፍፃሜው ደረጃ ለማሸጋገር ሳይችል ቀርቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሊጉ መሪዎች ማንችስተር ሲቲና አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 11 በመሆኑም የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ክብሩን የማስከበሩ ተስፋ ዝቅተኛ ሆኗል፡፡
chealsea

ይህንን እውነታን ከግንዛቤ በማስገባትም በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ምትክ የቼልሲ ስራን ለመረከብ በግንባር ቀደምትነት ሆላንዳዊው ጉስ ሂድንኪና ጣሊያናዊው ካርሎ አንቾሎቲ ታጭተዋል፡፡ የእነዚህ ሁለት ባለሙያዎች ስም ከቼልሲ ስራ ላይ እንዲያያዝ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ምክንያት ሁለቱም በአሁኑ ወቅት ካለስራ መቀመጣቸው ነው፡፡ በተለይም ከዚህ በፊት ቼልሲን ለአጭር ጊዜ በተጠባባቂ ዋና አሰልጣኝነት የመሩት ጉስ ሂድኒክ ከሰሞኑ በሰጡት አንድ መግለጫቸው በሞውሪንሆ ምትክ የቼልሲ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለመሾም ዝግጁ መሆናቸውን የሚጠቁም ሆኗል፡፡

ሂድንኪ የፊታችን ሰኔ ወር በፈረንሳይ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ዩሮ 2016 ውድድር የሆላንድ ብሔራዊ ቡድንን ተሳታፊ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመፈፀም ስለተሳናቸው ከአሰልጣኝነት ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወቃል፡፡ በሰሞኑ መግለጫቸው ለ2ኛ ጊዜ ሊመሩት መመኘታቸውን የጠቆሙት ቼልሲን በ2009 ለስድስት ወራት ያህል በተጠባባቂ ዋና አሰልጣኝነት በመምራት ለኤፍ.ኤ.ካፕ ድል ያበቁት ከመሆኑም ባሻገር በፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክሩ እስከመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ድረስ በጠንካራ አቋም ሆኖ ለመዝለቅ እንዲችል ረድተውት ነበር፡፡

ያንን መልካም ጊዜቸውን መለስ ብለው በማስታወስ ሂድኒክ ደግሞ የቼልሲ ስራን ለመያዝ መመኘታቸውን የጠቆሙበት መግለጫን ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡ ‹‹ፉትቦል ኢንተርናሽናል›› የተባለው የሆላንድ ጋዜጣ ከሰሞኑ ‹‹ከስድስት ዓመታት በኋላ ወደ ቼልሲ በመመለስ በዋና አሰልጣኝነት የመስራት ፍላጎቱን አሳድረዋል በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ ሂድኒክ ምላሻቸውን ሲሰጡ የተደመጡት ‹‹በትልቅ ደረጃ በሚደረግ ውድድር የሚሳተፍ ትልቅ ክለብን በዋና አሰልጣኝት የመምራት ፍላጎትን የማሳደር ባህል አለኝ፡፡ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በርካታ ጥሪዎችንም ቀርበውልኛል፡፡ የቀረበልኝ ጥሪዎችን ሳልቀበላቸው የቀረሁት የትልቅ ክለብ ሥራን ለመያዝ በመመኘት ነው፡፡ ለምሳሌ እንደ ቼልሲ አይነቱ ትልቅ ክለብ ጥያቄ የሚያቀርብልኝ ከሆነ ካለምንም ማመንታት መልሴን የምሰጠው እንደሚሆን አልደብቅም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ቀጣዩ ሥራዬ ምን እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ጉዳይ የለኝም›› በማለት ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው 68 የደረሰው ሂድኒክ ከዚህ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ የቼልሲ ስራን በፌብርዋሪ 2009 የተረከቡት የብራዚሉ አሰልጣኝ ሉዊስ ፍሊፕ ስኮላሪ ለሰባት ወራት ከዘለቁበት የስታምፎርድብሪጅ ስራ መነሳትን ተከትሎ ነበር፡፡ ሃዲንኪ ስታምፎርድ ብሪጅ እንደደረሱም ቼልሲ እስከሲዝኑ መጋመስ ድረስ የነበረው የአቋም አለመረጋጋት የ2008-09 ሲዝን ዘመቻውን በፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ በ3ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ እንዲጨርስ አስችለውታል፡፡

የቻምፒዮንስ ሊግ ዘመቻውን እስከ ግማሽ ፍፃሜው ደረጃ ድረስ ለመዝለቅ እንዲችልም አድርገውታል፡፡ በወቅቱ በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የደርሶ መልስ ግጥሚያ ቡድናቸው በባርሴሎና በአጠቃላይ ውጤት ተሸንፎ በሮም ከተማ ከተደረገው የውድድሩ ፋይናል የቀረውን ግልፅ የሆኑ የዳኝነት በደሎች ተፈጽሞበት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሂድኒክ ያንን ፀፀታቸውን ግን በሜይ 2009 በዌምብሊ ስቴዲየም ከኤቨርተን ጋር የተደረገው የኤፍ.ኤ.ካፕ ፋይናልን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫውን ሽልማትን በማግኘት በመጠኑም ቢሆን ሊረሱት ችለዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሂድኒክ ቼልሲን ለአጭር ጊዜ በተጠባባቂ አሰልጣኝነት በመሩበት ግማሽ ሲዝን ለቡድኑ ጠንካራ አቋምን አስገኝተውለት እንደነበር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የቼልሲው ባለቤት ሮማን ኢብራሞቪች በሚጠበቀው መልኩ ጆሴ ሞውሪኖን ከስራቸው ካነሷቸው ጉስ ሂድኒክን አዲሱ የክለባቸው ዋና አሰልጣኝ አድርገው መቅጠርን በቅድሚያ ምርጫቸው ቢያደርጉት አስገራሚ ሊሆን አይችልም፡፡
mourinho

ሂድኒክ የ2008-09 ሲዝን ከተጋመሰ ወዲህ የቼልሲን ስራ ተረክበው የቡድኑ ያልተረጋጋ አቋምን በፍጥነት ለማረም የቻሉበትን ያንን ተደናቂ ተግባራቸውን በማስታወስ በርካታ የፉትቦል ተንታኞች በዘንድሮ ሲዝን የቼልሲ የእስካሁን ችግሮች ትክክለኛው የመፍትሄ እርምጃን ሊያበጁለት የሚችሉበት ተደናቂ ተሰጥኦን ተላብሰዋል የሚል እምነት አሳድረውባቸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ለበርካታ ዓመታት በዘለቀው የአሰልጣኝነት ሙያቸው በርካታ ክለቦችና የተለያዩ አገሮችን ብሔራዊ ቡድኖችን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ሂድኒክ በቼልሲ ደጋፊዎችና በክለቡ አባላት በጠቅላላ እስካሁንም ድረስ ከፍተኛ የሆነ ከበሬታን አሳድረው ዘልቀዋል፡፡

‹‹እንደ ቼልሲ ያለው ትልቅ ውድቀትን በሌላ ክለብ አላስታውስም››
አለን ሽረር
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪኖ ባለፈው ሲዝን ቼልሲ ከፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ጋር ያገናኙት ሙሉው ሲዝንን በደረጃው ሰንጠረዥ አናት ላይ በማስቀመጥና የቅርብ ተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲን በስምንት ነጥቦች በልጦት እንዲጨርስ በማስቻል ነው፡፡ በዘንድሮው ሲዝን ግን ገና የመጀመሪያዎቹ 10 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከመደረጋቸው ከሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በ11 ነጥቦችና በአስር ደረጃዎች ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡
ከእስካሁኑ 10 የሊጉ ግጥሚያዎች 15 ጎሎችን አስቆጥሮ መረቡን በ19 ጎሎች ማስደፈሩም ሌላው የቼልሲ አስደንጋጭ የአቋም መውረድ ችግር እንዲከሰትበት የሚያሳይ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ አንዱ ምክንያት አብዛኛዎቹ የቡድኑ ተሰላፊዎች አቋም ወርዶ መገኘት ነው፡፡ ባለፈው ሲዝን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድሪም ቲም ምርጫ ከተካተቱት 11 ተጨዋቾች ውስጥ ስድስቱ የቼልሲ ተጨዋቾች ነበሩ፡፡ በዘንድሮ ሲዝን ግን አንድም በጥሩ አቋም ሊጠቀስ የሚችል ተጨዋች እስከመጥፋት ደረጃ ደርሷል፡፡

እነዚህ እውነታዎችን በመተንራስ የቀድሞው የኒውካስል ዩናይትዱ ስታር አለን ሽረር ሰሞኑን በሰነዘረው አስተያየቱ የቼልሲ በፍጥነት የአቋም መውረድን ‹‹ከዚህ በፊት በሌላ ክለብ ያልታየ አስደንጋጭ አጋጣሚ›› በማለት ገልፆታል፡፡ የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ የአጥቂ መስመር ተጨዋች በመቀጠልም ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ እንደ ቼልሲ ሁሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ከነበረበት ትልቅ አቋም በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ታች የወረደ ክለብ በእንግሊዝ ክለብ አልታየም፡፡ የቼልሲ በአስደንጋጭ ሁኔታ ወርዶ መገኘት በክለቡ ውስጥ አንድ ግልፅ ያልታየ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል የሚል ጥርጣሬን እንዳሳድር አስገድዶኛል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ ምናልባትም አንዱ ሞውሪንሆ በስኳዳቸው የሚመኙት ትክክለኛዎቹ ተጨዋቾች አለማግኘታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ማንኛውም የፉትቦል አፍቃሪና አስተያየት ሰጪ ቢሆን በዘንድሮው ሲዝን በቼልሲ ላይ የተፈጠረውን መሰረታዊ ችግሮች ምንነትን በትክክል ይረዳዋል የሚል እምነት በጭራሽ የለኝም›› የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

የስፖርትስ ሜይል የፉትቦል ተንታኞች በበኩላቸው ጆሴ ሞውሪኖ በኦገስት ወር በቼልሲ የዘንድሮ ሲዝን የመጀመሪያው ከስዋንሲ ሲቲ ጋር 2ለ2 ሲለያይ ለክለባቸው ዶክተር ኢቫ ካርኔሮ ጋር ግጭትን ከፈጠሩ ወዲህ ቡድናቸው ካደረጋቸው ግጥሚያዎች ግማሽ ያህሉን መሸነፉን ከግንዛቤ በማስገባት ከዛ ወዲህ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ላይ የተፈጠሩትን ችግሮችን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡

ኦገስት 8፡-
ጆሴ ሞውሪኖ የክለባቸው ዶክተር ኢቫ ካርኔሮና ረዳቷን ጆን ፍርንን የሚተች መግለጫን በመስጠት በክለባቸው ችግር እንዲቀሰቀስ በር ከፋች ሆነዋል፡፡ በሞውሪኖና በህክምና ባለሙያዎቹ መካከል ተፈጠረው ግጭት ተካርሮ በመዝለቁ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር እስከመከሰስ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን ካርኔሮን በብልግና ቃላት ሰድበዋል በሚል ከቀረበባቸው ክስ ካለምንም ቅጣት አምልጠዋል፡፡ በዚህ በመበሳጨት የህክምና ዶክተሯ በቼልሲ የነበራትን ስራ በራሷ ፈቃድ ለመልቀቅ ወስናለች፡፡

ኦገስት 16
ቼልሲ በኢትሃድ ስቴዲየም በማንችስተር ሲቲ 3ለ0 በተረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው ወቅት ጆሴ ሞውሪኖ ባልተለመደ መልኩ የቡድናቸው አምበል ጆን ቴሪን ቀይረው አስወጥተውታል፡፡ ከዛ በኋላ ባሉት ጥቂት ግጥሚያዎች ላይም ቴሪን በመደበኛ ቋሚ አሰላለፋቸው ውጪ በማድረግ የክለባቸው ደጋፊዎችን ቅር አሰኝተዋቸዋል፡፡ ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎችን ለማሸነፍ ሲሳነው ዘንድሮ ከድፍን 17 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ኦገስት 29
ሞውሪኖ ቼልሲን በስታምፎርድ ብሪጅ የመሩበት 100ኛው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው በሽንፈት ተደምድሟል፡፡ በክሪስታል ፓላስ 2ለ1 የተሸነፈበትን ጨምሮ ሞውሪኖ በራሳቸው ሜዳ ባደረጓቸው 100 የፕሪምየር ሊግ ግጥሚያዎች ሽንፈት ሲደርስባቸው ያ ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በዛ ግጥሚያ ኮሎምቢያዊው ኢንተርናሽናል ራዳሜል ፉልካኦ ለቼልሲ በውሰት ውል ከፈረመ ወዲህ የመጀመሪያውን ጎሉን ለማስቆጠር ቢችልም በስሙ ያስመዘገባት ጎል ግን ቼልሲን ከሽንፈት ሳታድነው ቀርታለች፡፡

ሴፕቴምበር 13
የሞውሪኖ ቡድን የጉድሰን ፓርክ ስቴዲየም ከኤቨርተን ጋር ያደረገው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያውን 3ለ1 በሆነ ውጤት በሽንፈት ለማጠናቀቅ ተገድዷል፡፡ በዛ ግጥሚያ የኤቨርተን አጥቂ ስቴቨን ሃይስሚዝ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሃትሪክ የሰራው የቼልሲው የተከላካይ መስመር ከተሰለፉት ጆን ቴሪና ለፈረንሳዊው ወጣት ተከላካይ ኩርትዙማ ከአቅማቸው በላይ የሆነ እጅግ ውጤታማ የማጥቃት እንቅሰቃሴን በማድረግ ነው፡፡ እስከዛ ደረጃ ድረስም ቼልሲ በመጀመሪያዎቹ 5 የሊጉ ግጥሚያዎቹ በእያንዳንዱ ላይ ቢያንስ ሁለት ጎሎች ተቆጥረውበታል፡፡ ከአምስቱ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ ያገኘው ነጥብ አራት ብቻ ነበር፡፡

ሴፕቴምበር 19
ቼልሲ አርሰናልን 2ለ0 በረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ወቅት የቡድኑ የፊት አጥቂ ዲያጎ ኮስታ ከሎረን ኮስኒሌይ ጋር በፈጠረው ግጭት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር የሶስት ተከታታይ ግጥሚያዎች የእገዳ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ እስከዚህ ጨዋታ ድረስ ኮስታ ከአንድ የፕሪሚየር ሊግ ጎል በስተቀር ለማስቆጠር አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ሞውሪኖ ኮስታ ለሶስት ግጥሚያዎች የታገደበት ውሳኔን በመተቸት በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር ላይ የሰላ ትችትን ሲሰነዝሩ ተደምጠዋል፡፡

ሴፕቴምበር 29
ጆሴ ሞውሪኖ በ2004 ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር ወደመሩት ፖርቶ ሜዳ ተመልሰው ባደረጉት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ቡድናቸው 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በዛ ግጥሚያ ሞውሪኖ ኤደን ሃዛርድና ኔማኒያ ማቲችን ለቡድናቸው መደበኛ ቋሚ አሰላለፍ ውጪ ያደረጉበት ተግባር ስህተት የፈፀሙበት ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡ ከፖርቶ ጎሎች ለአንዷ መገኘት ጥፋትን የፈፀመው ኩርት ዙማን በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በማስጀመር ጆን ቴሪን በተጠባባቂ ወንበር ላይ ያስቀመጡበት ተግባራቸውን ለቡድናቸው ሽንፈት ተወቃሽ የሆኑበት ሌላው ጉዳይ ሆኗል፡፡

ኦክቶበር 3
ቼልሲ በሳውዝአምፕተን 3ለ1 በተረታበት የዘንድሮ ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር 4ኛው ሽንፈቱ በኋላ ለሞውሪኖ ኃላፊነት ለትልቅ አደጋ ተጋልጧል፡፡ ከግጥሚያው ሶስት ቀናት በኋላ የቼልሲ ቦርድ ባወጣው ይፋዊ መግለጫው ግን ለሞውሪኖ ሙሉ ድጋፍን መስጠትን ምርጫው አድርጎታል፡፡ ሞውሪኖ በሳውዝአምፕተን የተረቱበት ግጥሚያ የመሩት አርቢትር ሮቤርቶ ማድሌይን በይፋ በመተቸታቸው በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር 50 ሺ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡

ኦክቶበር 17
ያለፈው ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች የሆነው ኤደን ሃዛርድ ቡድናቸው አስቶንቪላን 2ለ0 በረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ከመደበኛ ቋሚ አሰላለፋቸው ውጪ አድርገውታል፡፡ በኋላ ላይ በሰጡት መግለጫም የቤልጂየሙ ኢንተርናሽናል የዘንድሮው ሲዝን አቋሙን ከወትሮ በብዙ መልኩ የወረደ በማለት ተችተውታል፡፡

The post Sport: በቼልሲ ዙሪያ የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ | ጉስ ሂድኒክ የቼልሲ ስራን ለመያዝ ተዘጋጅተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? |ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ

$
0
0

ከግሩም ሰይፉ

38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ ቅዳሜ ሲጠናቀቅ ለዋንጫ ጨዋታ ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ሲገናኙ፤ አዘጋጇ ኢትዮጰያ እና ሱዳን ለደረጃ ይጫወታሉ፡፡ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ በሴካፋ የዋንጫ ጨዋታ ሲገናኙ የቅዳሜው ፍልሚያ በታሪክ ለ4ኛ ጊዜ ነው፡፡ ባለፉት ሶስት የዋንጫ ጨዋታዎች ኡጋንዳ አሸንፋለች፡፡ለ37ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና በመሳተፍ ግንባር ቀደም የሆነችው ኡጋንዳ 13 ጊዜ ሻምፒዮን ስትሆን ፤ ለ17ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና የተሳተፈችው ሩዋንዳ 1 ጊዜ ብቻ ዋንጫውን ማግኘት ችላለች፡፡

File Photo

File Photo


በ38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ በዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጰያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ በሩዋንዳ 1ለ0 ተሸነፈ፤ እንደምንም በሁለተኛ ጨዋታ ሶማሊያን 2ለ0 አሸነፈ፤ ከዚያም ከታንዛኒያ ጋር 1ለ1 አቻ ተለያይቶ በምርጥ ሶስተኛ የማለፍ እድል የመጨረሻውን እጣ አግኝቶ ወደ ሩብ ፍፃሜ ገባ፡፡ በሩብ ፍፃሜ በድጋሚ የተገናኘው ከታንዛኒያ ጋር የነበረ ሲሆን በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 አቻ ከተለያዩ በኋላ በመለያ ምቶች 4ለ3 ዋልያዎቹ አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜ ገቡ፡፡ በግማሽ ፍፃሜ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ከተሰጠው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተገናኙ፡፡ የተጫወቱት መቶ ሃያ ደቂቃቃዎች ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት አበቃ፡፡ በመለያ ምቶች ከዋልያዎቹ አምበሉ ጋቶች ፓኖም ሳተ፤ ኡጋንዳዎች ደግሞ ሁሉንም የፍፁም ቅጣት ምቶች አገቡ፡፡ አዘጋጇ አገር ወደቀች፤ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት የተሰጣች ኡጋንዳ ለፍፃሜ አለፈች፡፡ በሌላ ጨዋታ ሩዋንዳ ለዋንጫ ያለፈችው ሱዳንን በመለያ ምቶች በመርታት ነበር፡፡
Yohanes sahele
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑና ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የተፈራረሙት የቅጥር ውል 8 ወራት ሆኖታል፡፡ ከተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጋር በወር 75ሺ ብር እየተከፈላቸው የሚሰሩት ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ሲቀጠሩ በወቅቱ በይፋ ተገልፆ በነበረው የውል ስምምነት መሰረት በ2017 ጋቦን በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ዋሊያዎቹ ወደ ዋናው ውድድር ለማለፍ የሚያስላቸውን ነጥብ በማግኘት የ31ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ተሳታፊነታቸውን ማረጋጋጥ ዋና ዓላማ ነው መባሉ አይዘነጋም፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የዮሃንስ እና የዋልያዎቹ እድል ላይ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት የሚከብድ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አሰልጣኙ ከተሳካላቸው ፌደሬሽኑ ኮንትራታቸውን እንደሚያራዝምም ቃል ገብቷል፡፡ ግን በሌሎቹ የቅጥር ዓላማዎች ዋልያዎቹ በቻን 2016 እና በሴካፋ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ውድድሮችም አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅባቸው ተመልክቶ ነበር፡፡ በእርግጥ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው የቻን ውድድር ዋልያዎቹ ማለፋቸው በዮሃንስ ሳህሌ የተመዘገበው ጉልህ ስኬት ማለት ይቻላል፡፡ መርቂ ውጤት በቻን ላይ ማስመዝገብ አለማስመዝገባቸውን ሲደርስ የምንታዘበው ይሆናል፡፡ ዋልያዎቹ አዘጋጅ ሆነው በተሳተፉበት የሴካፋ ሻምፒዮና ግን የተጠበቀው አመርቂ ውጤት ሳይመዘገብብት ቀርቷል፡፡ ዮሃንስ ሳህሌ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ የዋንጫ ተፎካካሪ የሚያደርጋቸውን አስተያየት፤ አቀም እና ቡድን የመምራት ባህርይ አሳይተዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ከጅምሩ የቡድናቸውን ተሳትፎ ልምድ ለማግኘት፤ አዲስ ብሄራዊ ቡድን ለመገንባት፤ ለወጣቶች እድል ለመስጠት እያሉ ቆይተዋል፡፡ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ሩጫው ሲያበቃም ይሄ ግትርነታቸው ተስተውሏል፡፡

ከኡጋንዳው ሚቾ ጋር በሰጡት መግለጫ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ << በሚገባ ልጆች ያየንበት እድል የሰጠንበት ውድድር ነበር ›› በማለት ተስፋ አስቆራጩ ተሳትፏቸው እንዳጠገባቸው ተኩራርተው መልሰዋል፡፡ አሰልጣኙ በሴካፋ ውድድር ላይ በጥቅሉ ስንታዘባቸው • ቡድን በመገንባት ተጠምጃለሁ ብለው ቡድኑን በማፈራረስ • ልምድ ያላቸውን ተጨዋች ሙሉ ለሙሉ ጠራርጎ በማስወገድ የቡድኑን አቅም በማዳከም • ዋንጫውን ለመብላት የሚያስችል አስተያየት ከመስጠት ከደጋፊ፤ ከሚዲያ አጓጉል አተካራ በመፍጠር • በየጨዋታው ከቤንች ተነስተው ቡድኑን በማንቃት እና በማበረታት ከመስራት በማን አለብኝነት በመኮፈስ … አሳልፈዋል፡፡

The post Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? | ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: 15ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ –አርሰናል አሸነፈ –ሲቲ ተሸነፈ –ማን.ዩናይትድ ጎል ማግባት ተስኖት ነጥብ ጣለ

$
0
0

arsenal

Updated – (ዘ-ሐበሻ) 15ኛው ሳምንት የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከደቂቃዎች በፊት ተካሂዷል::  በዛሬው ጨዋታ አርሰናል እና የዘንድሮው አስደናቂ ቡድን ሌስተር ሲቲ ድል ቀንቷቸዋል:: በሌላ በኩል ዘግየት ብሎ የተጫወተው ቸልሲ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በርንማውዝን አስተናግዶ 1ለ0 ተሸንፎ በአሰልጣን ሆዜ ሞሪንሆ ላይ ጫናው እንዲበረታ አድርጓል::

ፕሪምየር ሊጉን በ32 ነጥብ የሚመራው ሌስተር ሲቲ ስዋንሳን 3ለ0 አሸንፎታል:: የሊጉ 2ኛ የሆነው አርሰናል ሰንደርላንድ 3ለ1 አሸንፎ ነጥቡን 30 አድርሶ ሌስተር ሲቲን ይከተላል::

ማንቸስተር ዩናይትድ አሁንም ጎል ማግባት ተስኖት ከዌስትሃም ጋር 0ለ0 ተለያይቷል:: ማንቸስተር ሩኒን እና ማርሻልን በጉዳት ምክንያት ያጣ ሲሆን ቡድን የፕሪምየር ሊጉ ደባሪ ቡድን እስከሚባል ድረስ የጎል እጥረት ተከስቶበታል::

ሌላው አስገራሚ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በስቶክ 2ለ0 ተሸንፏል:: ሲቲ ደረጃው ወደ 3 ዝቅ ያለ ሲሆን ከማን.ዩናይትድ ጋር በኩል 29 ነጥብ ቢቀመጥም በጎል ብልጫ ነው 3ኛ የሆነው::

የሌሎች ጨዋታዎች ውጤቶች:-
ዋትፎርድ ኖርዊችን 2ለ0
ሳውዛምተን እና አስቶን ቭላ 1ለ1
ዋትፎርድ ኖርዊችን 2ለ0 ሆኗል::

The post Sport: 15ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ – አርሰናል አሸነፈ – ሲቲ ተሸነፈ – ማን.ዩናይትድ ጎል ማግባት ተስኖት ነጥብ ጣለ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የዩሮ 2016 ድልድል ወጣ (የምድብ ድልድሉን ይዘናል)

$
0
0

euro 2016

(ዘ-ሐበሻ) በፈረንሳይ ከጁን 10 እስከ ጁላይ 10, 2016 ዓ.ም ለሚደረገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ ዲሴምበር 12, 2015 ዓ.ም ወጣ:: በዚህም መሠረት

በምድብ 1
– ፈረንሳይ
– ሩማንያ
– አልባኒያ
– ስዊዘርላንድ

በምድብ 2
– እንግሊዝ
– ሩሲያ
– ዌልስ
– ስሎቫኪያ

በምድብ 3

– ጀርመን
– ዩክሬን
– ፖላንድ
– ሰሜን አየርላንድ

ምድብ 4

– ስፔን
– ቼክ ሪፐብሊክ
– ቱርክ
– ክሮሺያ

ምድብ 5
– ቤልጂየም
– ጣሊያን
– ሪፐብሊክ አየርላንድ
– ስዊድን

ምድብ 6
– ፖርቱጋል
– አይስላንድ
– ኦስትሪያ
– ሃንጋሪ

በ እጣ ተደልድለዋል::

በጥሎ ማለፍ በቼክ ሪፐብሊክ 3ለ2 የተሸነፈችው ሆላንድ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ  እናያትም:: በወጣው ድልድል ስፔን; ቼክ ሪፐብሊክ; ቱርክና ክሮሺያ የተደለደሉበት ምድብ እና ቤልጂየም; ጣሊያን; ሪፐብሊክ አየርላንድ እና ስዊድን የተደለደሉባቸው ምድቦች ከባድ ምድቦች ተብለው ተወስደዋል::

The post Sport: የዩሮ 2016 ድልድል ወጣ (የምድብ ድልድሉን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 419 articles
Browse latest View live