Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all 419 articles
Browse latest View live

Sport: በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ 12 መቆየትና 5 መባረር ያለባቸው ተጨዋቾች 

$
0
0

United

በዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች የቀረበ  

ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያላቸው የአሁኑ ኮንትራት የሚጠናቀቀው በጁን 2017 ቢሆንም በዘንድሮ ሲዝን ለቡድኑ ከሚጠበቅባቸው ያነሰ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በመገደባቸው ግን የኮንትራት ውላቸው ከማለቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ከኦልድትራፎርድ ሥራ የመነሳታቸው ተስፋ እየሰፋ በመምጣት ላይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ የእግርኳስ ተንታኞች በማንሳት ላይ ያሉት ጥያቄም ሉዊ ቫንሃል ተከትለው ከዘንድሮ ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ኦልድትራፎርድን የሚለቁት በክለቡ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾች እነማን ይሆናሉ የሚል ነው፡፡

ቫንሃልን በመተካት የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝነት ስራን በሚረከቡት በጆሴ ሞውሪኖ ወይም በሌላ ባለሙያ ስር እነማንስ የክለቡ አቅድ አካል ሆነው የመዝለቅ እድል ይኖራቸዋል? የሚለውም ሌላ በመነሳት ላይ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች  በማንችስተር ዩናይትድ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾችን ወቅታዊ አቋምን በመገምገም ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ክለብን የሚለቁትና ለተጨማሪ ዓመታት የማንችስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆነው መዝለቅ የሚገባቸው ተጨዋቾችን ማንነትን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡

መቆየት የሚገባቸው

  1. ዴቪድ ዳሂአ

ባለፈው ሴፕቴምበር ወር ማንቸስተር ዩናይትድ የቀረበለትን አዲስ ለተጨማሪ አራት ዓመታት የሚዘልቅ ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ፈርሟል፡፡ ከዛ ወዲህ የወደፊት እጣ ፈንታውን በተመለከተ የተፈጠረበት ምንም አይነት ውዝግብ ባለመኖሩ የዳሂአ የማንቸስተር ዩናይትድ በርን ለተጨማሪ ዓመታት አጠራጣሪ አይመስልም፡፡ ክለቡ ለዳሂአ ከስፖንሰርሺፕ ውሎቹ የተወሰነ ፐርሰንት ገቢን ሊፈጥርለት ማቀዱም ስፔናዊው ግብ ጠባቂን ደስተኛ አድርጎት በኦልድትራፎርድ እንደሚቆየው ይጠበቃል፡፡

2. ማቲዬ ደርሚን

የዘንድሮ ሲዝን ከመጋመሱ በፊት በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የነበረውን ደካማ አቋማችን በማረም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሩ አቋም ለመገኘት ችሏል፡፡ በተለይም ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርቡ በቼልሲና ከሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ያበረከተው ታላቅ ፐርፎርማንስን የጣሊያናዊው ኢንተርናሽናል በሂደት በእንግሊዝ ፉትቦል የጨዋታ ስታይል ጋር በተገቢው መልኩ ለማዋሃድ ለመቻሉ በቂ ማስረጃ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር ደርሚንን ለበርካታ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ ቀኝ ተመላላሽ ሚና የመጀመሪያው ተመራጭ ተጨዋች ሆኖ እንደሚዘልቅ ይጠበቃል፡፡

3. ሉክ ሻው

የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ ግራ ተመላላሽ የዘንድሮን ሲዝንን በጥሩ አቋም ሆኖ ለመክፈት ቢችልም በሴፕቴምበር ወር ከፒኤስቪ አይንደሆቨን ጋር በተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ዝግጅት ግጥሚያ ያጋጠመው አደገኛ የእግር ስብራት ለበርካታ ወራት ከሜዳ ለመራቅ እንዲገደድ አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከጉዳቱ ለማገገም በማድረግ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥረት ስኬታማ ሆኖለት በሲዝኑ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሜዳ ለመመለስ ይችላል በሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በጥሩ ጤንነት ላይ በሚገኝበት ወቅት ከማንቸስተር ዩናይትድ ባሻገር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር አለኝታ ሆኖ ለበርካታ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ የሰፋ በመሆኑም በክለቡ በጭራሽ ሊለቀቅ የማይችል ተጨዋች እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም፡፡

4. ካሜሮን በርዝዊክ ጃክሰን

በዘንድሮው ሲዝን ከሉዊ ቫንሃል ጥቂት ተደናቂ ተግባሮች ውስጥ የ18 ዓመቱ ወጣት የግራ ተመላላሽን ከማንቸስተር ዩናይትድ ወጣት ቡድን ወደ ዋናው ለማሳደግ የደረሱበት ቆራጥ ውሳኔያቸው በሮዝዊክ ከወዲሁ ለዋናው ቡድን በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ተደናቂ ብቃቱን በማሳየት ማንቸስተር ዩናይትድ ለዘለቄታው የአስተማማኝ ግራ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶች እጥረት እንደማይኖርበት ለማስመስከር የቻለ ሆኗል፡፡

5. ፊል ጆንስ

ከዚህ በፊት ማንቸስተር በሪዮ ፊርዲናንድና በኔማኒያ ቪዲች አማካይነት የነበረውን ጠንካራ የመሃል ተከላካይ ክፍል ጥምረትን ሁለቱ እንግሊዛዊያን ክሪስ ስሞሊንግና ፊል ጆንስ በአግባ ለመመለስ ይችላሉ የሚል እምነት በበርካታዎች ዘንድ ተፈጥሮ ዘልቋል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን ይህ እምነት በአግባቡ ተግባራዊ እንዳይሆን በፊል ጆንስ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጉዳት የበኩሉን ተፅዕኖን የፈጠረ ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን ጆንስ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል አጋማሽ የሚገኝ ተጨዋች በመሆኑ የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ ለተጨማሪ ዓመታት የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

6. ክሪስ ስሞሊንግ

ከዚህ በፊት በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር ሳይቀር ብዙ ተለፍቶበት የተረጋጋ አቋምን ለመያዝ ሲቸገር ታይቷል፡፡ በሉዊ ቫንሃል ስር ግን የማንቸስተር ዩናይትድ የተዋጣለት የመሀል ተከላካይ ሚና ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር የቻለበት ተደናቂ ፐርፎርማስን መላበስ ችሏል፡፡ በተለይም የእስካሁኑ ሲዝን የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ምርጡ ተጨዋች ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድ ልዩ ትኩረት ስሞሊንግ ጎን ትክክለኛውን ጥምረትን ለመፍጠር የሚችል ተጨዋችን ለማግኘት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

7. ዳሊን ብሊንድ

የዘንድሮው ሲዝን በአብዛኛው ግጥሚያ ለማንቸስተር ዩናይትድ የተሰለፈበት በተከላካይ መስመር ነው፡፡ ሉዊ ቫንሃ ሆላንዳዊው ኢንተርናሽናል ከአማካይ ክፍል ይልቅ በመሀል ተከላካይ ሚና እንዲጠቀሙበት በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት የሆናቸው በስኳዳቸው የሚገኙት በርካታ የተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን በጉት ሳቢያ ከሜዳ ለመራቅ መገደዳቸው ነው፡፡ ይህን የሚያሳየው የብሊንድ የተለያዩ የጨዋታ ሚናዎች የመሰለፍ ሁለገብ ብቃትን ማንቸስተር ዩናይትደ በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ሊያገኘው አጥብቆ የሚመኘው መሆኑን ነው፡፡

8. ማይክል ካሪክ

ካለፉት ዓመታት አንፃር የእንግሊዛዊው አማካይ የዘንድሮ ሲዝን አቋም ጥሩ የሚባል ባይሆንም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን የዕድሜው መግፋት ምንም አይነት ተፅዕኖን ሳይፈጥርበት በቦታው ላይ የወትሮውን ጥሩ አቋሙን የሚያስታውሰው ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ነው፡፡ ይህ እውነታ ከግንዛቤ ሲገባም ማንቸስተር ዩናይትድ የተጨማሪ 12 ወራት የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ሊፈቅዱለት ማቀዱ ማስታወቁ አስገራሚ ሊሆን አይችልም፡፡

9. ሞርጋን ሽኔደርሊን

ፈረንሳዊው አማካይ በቀድሞ ክለቡ ሳውዝአምፕተን የነበረው ታላቅ ፐርፎርማንስን በእስካሁኑ ሲዝን ለመድገም ችሏል ባይባልም በመሀል አማካይ ክፍል ትክክለኛው አማራጭ ተጨዋች የሚያገኝ ከሆነ ግን በቦታው ላይ የማንቸስተር ዩናይትድ አስተማማኝ አለኝታ ሆኖ እንደሚዘልቅ ይታመናል፡፡

ሸኔደርሰሊን ከሲዝኑ መጋመስ ወዲህ የያዘው ጥሩ አቋም መሆን ቀስ በቀስ የማንቸስተር ዩናይትድ የመሀል አማካይን በበላይነት ለመምራት የሚያስችለውን አስተማማኝ ብቃት እንደሚኖረው የሚጠቁም ሆኗል፡፡

10. አንደር ሄሬራ

በሉዊ ቫንሃል ስር ብዛት ያላቸው ግጥሚያዎች ተከታታይነት ባለው መልኩ የመሰለፍ ዕድል ባይሰጠውም አልፎ አልፎ በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ግን ውጤታማ ፉትቦልን ሲያበረክት መታየቱ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ስፔናዊው አማካይ የኦልድትራፎርድ ስራ በትክክለኛው ባለሙያ የሚያዝ ከሆነ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

11. አሽሊ ያንግ

በሉዊ ቫንሃል ስር ከዚህ በፊት የነበራቸው ብቃትን አሳድገው ከተገኙት የማንቸስተር ዩናይትድ ስኳድ አባላት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በተለይም ሆላንዳዊው አሰልጣኝ አሽ ያንግ በተፈጥሮ ከያዘው በማጥቃት ላይ ያተኮረ የክንፍ ሚናው ባሻገር ወደኋላ ተመልሶ የመከላከል ተግባርን የሚፈፅምበትን አዲስ የጨዋታ ሚናን አስገኝተውለት ሁለገብ ብቃቱን አሳድገውለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ያንግ ለተጨማሪ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

12. ሜምፌስ ዴፖይ

ባለፈው ሲዝን ፒኤስቪ አይንደንሆቨንን ለሆላንድ ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር እንዲበቃ ያበረከተው ቁልፍ አስተዋፅኦን በእስካሁኑ ሲዝን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለመድገም አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ዴፖይ ውጤታማ ፉትቦሉን በሜዳ ላይ ለማውጣት እንዲችል በሚረዳውን ትክክለኛ አሰልጣኝን ለማግኘት ከቻለ የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ ለመዝለቅ የሚችልባቸውን ሁሉንም አይነት ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡

ክለቡን መልቀቅ ያለባቸው

 5. ማርኮስ ሮሆ

የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ጥሩ የኳስ ስኬል ችሎታን ስኬታማ ታክሎችን የመግባት ብቃት ያለው ቢሆንም በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ ግን ከትኩረት ማነስ ችግር በመነጨ ስህቶችን ሲፈፅም መታየቱ የተለመደ ባህሉ ነው፡፡ አልፎ አልፎም አስፈላጊው ፋውሎችን በመፈፀም ቡድኑን የሚጎዳበት ባህል ያለው መሆኑ ከግንዛቤ ሲገባም በክለቡ ውስጥ የሚገባው ተጨዋች ነው፡፡

4. ባስቲያን ሽዌንስቲገር

ሉዊ ቫንሃል ጀርመናዊው ልምድ ያካበተ የመሃል አማካይን ለመግዛት የወሰነበት ተግባራቸው መጥፎ ሃሳብ ተደርጎ ሊቆጠር የሚገባው ቢሆን በእንግሊዝ ፉትቦል መሳተፍ የጀመረው ግን ዕድሜው 31 ከደረሰ በኋላ በመሆኑ ማንቸስተር ዩናይትድ በትክክለኛው ወቅት ላይ አላገኘውም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ሽዌንስቲቨር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ወደ ሜጀር ሊግ ስኮር ውድድር ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

3. ማሮዋን ፊላኒ

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽልን ያስፈረሙት ሁለገብ የአማካይ ክፍልና የአጥቂ መስመር ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባታቸው ቢሆንም የያዘው ብቃት ግን የማንቸስተር ዩናይትድ ትልቅ ስታንዳርድን በበቂ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አልተገኘም፡፡ ከዚህ አንፃር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሚጠበቀው እጣ ፈንታ በማንቸስተር ዩናይትድ ለሽያጭ መቅረብ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

2. አንቶኒዮ ቫሌንስያ

በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር የነበረው ውጤታማ ብቃቱን ቀስ በቀስ በማጣት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ኮርሶችን በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎች ላይ በመደረብ ራሱን የቻለ መጥፎ ሪከርድን ይዞ ዘልቋል፡፡ ከዚህ አንፃር ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚኖረው የፉትቦል ህይወት ወደማክተሙ ደረጃ ተቃሯል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

  1. አድናይ ያንዩዣይ

በመላው አውሮፓ ተደናቂ ብቃትን የተላበሰው በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙት ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑ ቢታመንበትም የሉዊ ቫንሃል እቅድ አካል ለመሆን ተስኖታል፡፡ እስከ ዘንድሮው ሲዝን መጋመስ ድረስ በቦሪሽያ ዶርትሙንድ ያደረገው የውሰት ውል ቆይታውም ተደናቂ ስኬት ሊታጀብለት አልቻለም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ያንዩዣይን በጥሩ ዋጋ ለሌላ ክለብ የመሸጥ ውሳኔ ላይ መድረስ ነው፡፡ ያንዩዣይ በቅርበት የሚያውቁት አስተያየት ሰጪዎች ተጨዋቹ በዘንድሮ ሲዝን መጀመሪያ ላይ ከሉዊ ቫንሃል እቅድ ውጪ መሆኑ ተነግሮት በማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ከተለቀቀ ወዲህ በትክክለኛው የስነ ልቦና ጥንካሬ ደረጃ ላይ ለመገኘት ተስኖታል፡፡

The post Sport: በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ 12 መቆየትና 5 መባረር ያለባቸው ተጨዋቾች  appeared first on Zehabesha Amharic.


አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የላውሪዮስ ሽልማት የ2016 ምርጥ አትሌት እጩ ሆና ተመረጠች

$
0
0

genzebe 1

በሴቶች የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በዕጩነት የተካተቱት ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ፣ ጃማይካዊቷ የአጭር እርቀት አትሌት ፍሬስር ፕራይስ፣ አሜሪካዊቷ የቴኒስ ተጨዋች ሴሪና ዋሊያምስ፣ አሜሪካዊቷ እግር ኳስ ተጨዋች ካርሊ ሊሎይድ፣ኦስትሪያዊቷ አና ፌኒንገር እና አሜሪካዊቷ ዋናተኛ ኬቲ ናቸው፡፡

ገንዘቤ በቤጅንግ የዓለም ሻምፒዮና ማሸነፏ 2 ክብረወሰኖችን ማሻሻሏ ከሌሎቹ በተሻለ ትመረጣለች የሚል ግምት ተሰጥቷታል፡፡
ገንዘቤ ዲባባ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው የላውሪዮስ ሽልማት በ2015 ዓመት ምርጥ ስፖርተኛ ተብላ መሸለሟ የሚታወስ ሲሆን በወንዶች ጃማይካዊው የአጭር እርቀት አትሌት ዩዜን ቦልት፣ ሰርቢያዊው የቴኒስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች፣ እንግሊዛዊው የመኪና ተወዳዳሪ ሊዌስ ሀማልተን ፣አርጀንቲናዊው እግር ኳስ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ፣ አሜሪካዊው ቅርጫት ኳስ ተጨዋች ስቴቨን ኬሪ በዕጩነት ቀርበዋል፡፡


የላውሪዮስ ሽልማት አሸናፊ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 18ቀን 2016 በበርሊን ይፋ ይሆናል::

World champions Usain Bolt, Shelly-Ann Fraser-Pryce and Genzebe Dibaba are among the nominations for the 2016 Laureus world sportsman and sportswoman of the year awards.

Bolt, a three-time winner of the Laureus sportsman of the year award, successfully defended his world titles in the 100m, 200m and 4x100m at the IAAF World Championships Beijing 2015.

Fraser-Pryce did likewise in the 100m and 4x100m, while Dibaba – the 2015 Laureus world sportswoman of the year and IAAF world female athlete of the year – won the world 1500m title in Beijing, having broken the world record for the distance earlier in the year.

Outside of athletics, the other male nominees are (in alphabetical order): US basketball player Stephen Curry, Serbian tennis player Novak Djokovic, British racing driver Lewis Hamilton, Argentinian footballer Lionel Messi and US golfer Jordan Spieth.

Dibaba and Fraser-Pryce are joined on the list of female nominees by Austrian skier Anna Fenninger, US swimmer Katie Ledecky, US soccer player Carli Lloyd and US tennis player Serena Williams.

World champions Jessica Ennis-Hill and David Rudisha have been nominated in the ‘comeback of the year’ category.

Ennis-Hill won the world heptathlon title in Beijing, one year after giving birth to her first child and having battled an achilles injury. Rudisha bounced back from two years of injury problems to win the world 800m title in Beijing.

Cuba’s visually impaired sprinter Omara Durand has been nominated in the disability category. At last year’s IPC World Championships in Doha, Durand won the 100m, 200m and 400m, setting world records of 11.48, 23.03 and 53.05 respectively.

The winners will be announced at the Laureus World Sports Awards ceremony in Berlin on 18 April.

The post አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የላውሪዮስ ሽልማት የ2016 ምርጥ አትሌት እጩ ሆና ተመረጠች appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ሳልሃዲን ሰዒድ ብሔራዊ ቡድናችን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ጨዋታ መሰለፍ እንደማይችል አስታወቀ |አኩርፎ ይሆን?

$
0
0

salahadin
የብሄራዊ ቡድናችን ጎል ለአዳኝ ሳላዲን ሰዒድ ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ ጋር ለምታደርገው ወሳኝ ጨዋታ በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ጥሪ ቢደረግለትም መጫወት እንደማይችል ሪፖርት አደረገ:: በዚህም የተነሳ ከብሄራዊ ቡድኑ ውጭ መሆኑ ተሰማ::

ከዚህ በፊት በነበሩ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ከጉዳት ካገገመ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ከምርጫ በመዘለሉ ምክንያት ከብሄራዊ ቡድን ርቆ በመቆየቱ እንዳኮረፈ የሚነገርለት ሳላዲን ሰዒድ ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ ጋር ለምታደርጋቸው ጨዋታዎች በአሰልጣኙ ጥሪ ቢደረግለትም እንደማይጫወት ገልጿል;;

በተያዘው የውድድር አመት በቂ ጨዋታዎችን ማድረግ ባለመቻሉ በአእምሮ እና በአካል ረገድ ለጨዋታ ያለው ዝግጁነት ብቁ ደረጃ ላይ እንደማይገኝ ገልጿል የተባለው ሳልሃዲን ብሄራዊ ቡድኑ ከአልጄሪያ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ላይ መሰለፍ እንደማይችል ለአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በማሳወቅ ከብሄራዊ ቡድኑ ውጪ ሆኗል፡፡

ሳልሃዲን በኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በተለይ ሃገሪቱ ወደ አፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ከረዳት በኋላ “ጥቁር ሰው” እየተባለ በአድናቆት ተዘምሮለታል::

The post Sport: ሳልሃዲን ሰዒድ ብሔራዊ ቡድናችን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ጨዋታ መሰለፍ እንደማይችል አስታወቀ | አኩርፎ ይሆን? appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: አዳነ ግርማ በአጥቂ ችግር ላይ ላለው ብሔራዊ ቡድናችን “ከቤተሰቤ ጋር ተማክሬ ላለመጫወት ወስኛለሁ”አለ

$
0
0

AdaneGirma

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው።

ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል::

በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

The post Sport: አዳነ ግርማ በአጥቂ ችግር ላይ ላለው ብሔራዊ ቡድናችን “ከቤተሰቤ ጋር ተማክሬ ላለመጫወት ወስኛለሁ” አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ ውጭ ሆነ

$
0
0

st george

(ዘ-ሐበሻ) በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሻምፒዮናው ውጭ መሆኑን ዛሬ አረጋገጠ::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፈው ሳምንት ባህር ዳር ላይ በተደረገ ጨዋታ ከኮንጎ ዲሞክራቲኩ ማዜምቤ ክለብ ጋር በ2ለ2 አቻ ውጤት የተለያየ ቢሆንም በዛሬው የመልስ ጨዋታ ግን የማዜምቤ ክለብ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀራቸው ባገኙት ፍጹም ቅጣት ምት የተነሳ ከውድድሩ ውጭ ሆነዋል:: ለኮንጎው ቡድን ጆናታን ቦሊንጊ ፍፁም ቅጣትምቷን ወደ ግብነት በመቀየሩ ነው በድምር ውጤት 3 ለ 2 ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፎ ከቻፒዮናው ውጭ ሆኗል::

ዛሬ በተደረገ በሌላ የአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ ጨዋታ የሞዛምቢኩ ፌሮቫሪዮ ማፑቶ እና የዲሞክራቲክ ኮንጎው አስ ቭስታ ክለብ 1ለ1 ተለያይተዋል::

The post ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ ውጭ ሆነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ በፖርትላንድ ኦሪገን ያሸነፈችበትን ቪዲዮ ይመልከቱ | Video

ሳቂታዋ የረጅም ርቀት ሩጫ ንግስት ደራርቱ ቱሉ

$
0
0

Derartu Tulu

ዛሬ የደራርቱ ቱሉ ልደት ነው:: ይህችን ታላቅ ጀግና በቁም እያለች ማክበርና ማመስገን ሌሎችን ማበረታትም ጭምር ነው:: የደራርቱን ልደት በማስመልከት ተወዳጁ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍሰሃ ተገኝ በቶታል 433 ድረገጹ ከዚህ ቀደም ያስነበበንን ጽሁፍ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እንደወረደ አቅርበናል::

መልካም ልደት ለደራርቱ! መልካም ንባብ ለእርስዎ

ኦሎምፒክ ምን እንደሆነ ከማወቄ በፊት የእሷን ስምና ድሏን ነበር የማውቀው። ስሟ በሬዲዮ በተደጋጋሚ ሲጠራ ስለሰማሁት አእምሮዬ ውስጥ ተቀርጾ ተቀምጧል። “የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነች” የሚለው ጩኸት ልቤን አልሰረቀውም፤ ልጅ ነበርኩና የኦሎምፒክን ዋጋና ምንነት ባለማወቄ። “ሮጣ ተፎካካሪዎቿን እንደ ጭራ ከኋላ አስከትላ አሸነፈች” የሚለው ድምጽን ለማስተናገድ ግን አልተቸገርኩም። ምክንያቱም እየተሯሯጠና አቧራ እያቦነነ ለነበረ ልጅ ሩጫ፣ መቅደምና መቀደም ምን እንደሆኑ ለይቶ ለማወቅ አያስቸግረውምና።

ምን አልባት በተደጋጋሚ ፊቷ ላይ የሚታየው ፈገግታ ደራርቱ ቱሉን በተፎካካሪዎቿና ፊት-ለፊት የሚያየውን ነገር ብቻ ማንበብ በለመደ ሰው አይን ውስጥ ጠንካራና ቆፍጣና ተወዳዳሪ ላያስመስላት ይችላል። ተራራማዋ በቆጂ ውስጥ የተወለደችው ደራርቱ ግን ልክ የውድድር ማስጀመሪያው ሽጉጥ እንደተተኮሰ ነብር ትሆንና በአስደናቂ ብልሀት፣ በጽናት እና በጠንካራ ልምምድ ከታጀበው ውብ አሯሯጧ ጋር ተፎካካሪዎቿን እንዳልነበሩ አድርጋ የማሸነፍ ብቃት ያላት ድንቅ አትሌት ነች። ይሄንን ለማረጋገጥ የፈለገ ወደኋላ ብዙ መመለስ አያስፈልገውም። በህዳር ወር መጀመሪያ 2009 ዓ.ም የተካሄደው የኒው ዮርክ ማራቶን ለተወዳዳሪዎችና ሩጫውን ለመከታተል በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ለተገኘው ተመልካች የአየሩ ሁኔታ እጅግ በጣም ቀዝቃዛ በመሆኑ “ምን አለበት ከሞቀው ቤቴ ባልወጣሁ” የሚያሰኝ የነበረ ቢሆንም፤ ደራርቱ ታስብ የነበረው ግን ከድል በኋላ በደስታ ልታገኘው ስለምትችለው ውስጣዊ ሙቀት ነበር።

“ውድድሩ ሲጀመር አየሩ በጣም ቀዝቃዛ ነበር። እንዲያውም የሆነ ቦታ ላይ ለመውደቅም ተቃርቤ ነበር። ምስጋና ተጨማሪ ብርታት ለሰጠኝ እግዚአብሄር ይግባና ያንን አለፍኩ። ውድድሩን ከጨረስኩ በኋላ የተሰማኝ ግን ፍጹም ሌላ አይነት ስሜት ነው፤ በድል አድራጊነት የተገኘ የደስታ ሙቀት” አለች ተፎካካሪዎቿ የነበሩት ራሺያዊቷ ፔትሮቫን እና ፈረንሳዊቷ ዳውኔን  ቀድማ ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቀቀችው ደራርቱ ለረኒንግ ታይምስ መጽሄት በጊዜው በሰጠችው አስተያየት።

derartu

እንዲህ ነች ደራርቱ፤ ፈተናዎቿን በፈገግታ በታጀበው የአሸናፊነት ስሜትና ድል ማሳለፍ የለመደች። ደራርቱን በጊዜው ማንም የኒዮርኩ ማራቶን አሸናፊ ትሆናለች ብሎ አልገመታትም። ምክንያቱም በ2006 ዓ.ም ልጅ ወልዳ ስለነበር ከሁለት አመታት በላይ ከሩጫው ከመራቋ በተጨማሪ፤ ውድድሮች ባደረገችባቸው ጥቂት ጊዜያት ውስጥም ጠንካራ የሚባልና ድሮ የስፖርቱን አፍቃሪ ያስለመደችውን አይነት አቋም ባለማሳየቷ ነው። ያደገችበት ባህል ልጅ ከወለዱ በኋላ ወደስራ በቶሎ መመለስን የማይደግፍ በመሆኑ በቶሎ ወደልምምድ ባለመመለሷ ምክንያት በአንድ ውቅት ክብደቷ በአብዛኛው ስትሮጥ ከነበራት 40ዎቹ አጋማሽ ኪሎ ግራም ላይ 18 ኪሎዎች ጨምራ ነበር። ከውድድር መራቅን፣ በወቅቱ የነበረው የኒው ዮርክን ቅዝቃዜ እና በርቀቱ የአለም የማራቶን ክብረወሰንን የያዘችውና ውድድሩን ታሸንፋለች ተብላ ትልቅ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ብሪታኒያዊቷ ፓውላ ራድክሊፍን የመሰሉ ጠንካራ ተፎካካሪዎቿና አስቸጋሪ ፈተናዎችን ከኋላ አስቀርታ ደራርቱ ቱሉ የኒው ዮርክ ማራቶንን ለማሸነፍ የቻለች የመጀመሪያዋ ሴት ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆነች።

“በርግጥ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበኩም። ነገር ግን ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምሆን አልተጠራጠርኩም። እስከመጨረሻው ለመታገል ቆረጥኩና ከእግዚአብሄር እርዳታ ጋር ለማሸነፍ በቃሁ። ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ያሳለፍኩትን ሳስበው አሁን ያገኘሁት ድል የበለጠ እንድደሰት አድርጎኛል” አለች ደራርቱ ከድሉ በኋላ በፈገግታ በታጀበው አንደበቷ በሰጠችው አስተያየት።

በትምህርት ቤቷ በመካከለኛ ርቀቶች ተወዳድራ በተደጋጋሚ በአሸናፊነት ካጠናቀቀች በኋላ፤ እ.አ.አ በ1988 ዓ.ም አርሲን ወክላ በብሄራዊ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ1500 ሜትር ርቀት የነሀስ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ፤ በአለም አቀፍ የሩጫ መድረኮች ላይ መታየት የጀመረችው በሀገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ነበር። ገና የ16 አመት ታዳጊ ወጣት እያለች እ.አ.አ በ1989 ዓ.ም የኖርዌዋ ስታቬንጋር ከተማ ውስጥ በተካሄደው  17ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ 23ኛ ደረጃን አግኝታ ጨረሰች። መሻሻልን እንጂ ወደታች መውረድን የማታውቀው ደራርቱ ምንም እንኳን የሜዳሊያ ፖዲዬም ላይ የሚያወጣት ውጤት ባታገኝም ከአንድ አመት በኋላ በተካሄደው የአለም አገር አቁራጭ ሻምፒዮና ከአለፈው አሻሽላ ውድድሩን 18ኛ ደረጃን አግኝታ አጠናቀቀች።

የመጀመሪያ አለማቀፋዊ ድልን ያገኘችው ግን በሀገር አቋራጭ ውድድር አልነበረም። በትራክ ወይም መም ውድድር እንጂ። እ.አ.አ በ1990 ዓ.ም በቡልጋሪያዋ ፕሎቭዲቭ ከተማ በተካሄደው በታዳጊ ወጣቶች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የተካፈለችው ደራርቱ አንደኛ ወጥታ የመጀመሪያ የሆናትን አለም አቀፋዊ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። ማሸነፏ ሳይሆን ርቀቱን ለማጥናቀቅ የወሰደባት 32 ደቂቃ ከ56.26 ሰከንድ ነበር በጊዜው በሩጫው አለም መነጋገሪያ የሆነው። ወጣቷ ለውደፊት ትልቅ ተስፋ እንዳላት የገመቱ የዘርፉ ባለሞያዎች ጥልቅ ክትትል እያረጉባት እያለና በተለያዩ ብዙሃን መገናኛዋች ተስፋዋን እያስተጋቡ እንዳለ፤ በ1991 ዓ.ም ቶክዮ ጃፓን ውስጥ በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በግማሽ ፍጻሜው 10 ሺህ ሜትሩን 31 ደቂቃ ከ45.95 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃ በርቀቱ የኢትዮጵያን ክብረወሰን ሰበረችና የአለም የሴቶች ረጅም ርቀት ሩጫ ትኩረት ወደእሷ እንዲዞር አደረገች።

እ.አ.አ 1992 ዓ.ም በደራርቱ የአትሌቲክስ ህይወት ታሪክ ውስጥ ምን አልባት እጅግ በጣም ታላቁ እንደነበረ የሚነገርለት ነው። በዛ አመት በሶስት የ10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ላይ ተካፍላ ሁሉንም ስታሸንፍ፤ ከባርሴሎናው ኦሎምፒክ መጀመር ጥቂት ቀደም ብሎ በተካሄደው የአፍርካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ርቀቱን በጊዜው የአህጉሪቷን ክብረወሰን በሰበረ 31 ደቂቃ ከ22.25 ሰከንድ ጊዜ አጠናቃ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

tulu

በባርሴሎናው ኦሎምፒክ የተፈጠረውን አለም የማይረሳው ነው። “ባርሴሎና ላይ ስካፈል ኦሎምፒክ ምን እንደሆነ ስለማላውቅ ልክ እንደማንኛውም አይነት ውድድር ነበር ያየሁት” ያለችውና በጊዜ 42 ኪሎ ግራም ክብደትና 1.56 ሜትር ቁመት የነበራት ደራርቱ፤ በታላቁ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ አስደናቂ የፍጻሜ ውድድሮች ከሆኑት ተርታ የተመዘገበ እንደሆነ በተነገረለት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ልክ የማብቂያው 25ኛ ዙር ደውል ድምጽ ሲሰማ ውድድሩን ትመራ የነበረችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሌና ሜዬርን ቀድማ አፈትልካ ወጣችና የመጨረሻውን ዙር (400 ሜትር) በ64 ሰከንዶች በመጨረስ ሜዬርን በ30 ሜትሮች ያህል ቀድማ አንደኛ በመውጣት በኦሎምፒክ ታሪክ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ሴት ሆነች። አስደናቂ የነበረው ታዲያ ውድድሩን ያሸነፈችበት አጨራረስ ብቃቷ ብቻ አልነበረም፤ ስፖርታዊ ጨዋነቷም እንጂ። አሸናፊነቷን ያረጋገጠችው ደራርቱ ነጯ ደቡብ አፍሪካዊት ኤሌና ሜዬር ሩጫዋን እስክትጨርስ ቆማ ከጠበቀች በኋላ አቅፋት የእንኳን ደስ አለሽ መልእክቷን ማስተላለፏ ድንቅና በኦሎምፒኩ ከማይረሱት ምስሎች መካከል አንዱ ነበር። ከዚህ በኋላ ሁለቱ አትሌቶች የየሀገሮቻቸውን ሰንደቅ ዓላማ አብረው ጎን ለጎን በመሆን እያውለበለቡ የትራኩን ዙሪያ በመሮጥ ለተመልካቹ ድጋፍ ምስጋና ሲያቀርቡ ያየ በሙሉ “ምን አልባት የአድሲቷ አፍሪካ የወደፊት ታሪክ ብርሀናማ ሊሆን ይችላል” ብሎ እንዲያስብ ስድርጓል።

“ኤሌና በእንግሊዘኛ ስታዋራኝ ትዝ ይለኛል” አለች ደራርቱ ሁኔታውን ወደኋላ መለስ ብላ በማስታወስ። “ምንም እንኳን ምን እየነገረችኝ እንደሆነ ባይገባኝም [ፈገግታ] በምልክት መነጋገር ከጀመርን በኋላ በመግባባታችን ለረጅም ጊዜ ጓደኛሞች እንደሆነን አለን።”

የደራርቱን ስፖርታዊ ጨዋነት በርካታ እሷን የሚያውቋትና የአትሌቲክስ ስፖርት ባለሞያዎች “ፉክክር በበዛበት የስፖርት አለም ለማግኘት የሚከብድ ታላቅ ተምሳሌት” በማለት ይገልጹታል። በ2009 ዓ.ም በተካሄደው የኒው ዮርክ ማራቶን ተወዳዳሪዎቹ የርቀቱን ግማሽ ያህል ከሄዱ በኋላ ደራርቱ ቱሉና ፓውላ ራድክሊፍን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ያሉበት የመሪዎቹ ቡድን ኩዊንስቦሮ ድልድይን እንዳቋረጠ ፓውላ ራድክሊፍ ህመም ይሰማትና ያንን ችላ እያቃሰተች ለመሮጥ ስትሞክር ያየችው ደራርቱ ዘውር ብላ “አይዞሽ በርቺ፤ ልንጨርስ ትንሽ ነው የቀረን” የሚል የብርታት መልእክትን ታስተላልፋለች። ሁለቱ አትሌቶች በሩጫው አለም የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላቸው ቀንደኛ ተፎካካሪዎች መሆናቸውን የሚያውቁ ጋዜጠኞችና የስፖርቱ አፍቃሪ ባዩት ክስተት በጣም ነበር የተገረሙት። ታዲያ ውድድሩ ካለቀ በኋላ ሁኔታውን አስመልክቶ እንድታብራራ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላት ፓውላ “ደራርቱ ማለት ይቺ ነች፤ ከፉክክር ይልቅ መከባበርንና መዋደድን የምታስቀድም ጥሩ ሰው። ሌሎቹ ተፎካካሪ አትሌቶች ሲያልፉኝ እሷ ግን እንዳመመኝ ስላወቀች ጠጋ አለችና በኔ ፍጥነት ቀስ ብላ ከጎኔ እየሮጠች ‘አይዞሽ በርቺ’ አለችኝ” በማለት የደራርቱን ታላቅ ስፖርታዊ ጨዋነት ለአለም አስተጋባች።

በስፖርቱ አለም በርካታ አሸናፊዎች ቢኖሩም አስቸጋሪውና ፈታኙ ግን በድል አድራጊነት ለረጅም ጊዜ መቆየት ነው። ይሄንን ማድረግ የሚችሉ ደግሞ እንደ ደራርቱ ያሉ እጅግ በጣም ጥቂት ስፖርተኞች ናቸው። “ለተደጋጋሚ ጊዜያት መሮጥህ ልምድ እንዲኖርህና ከዛ እንድትማር ያደርግሀል። አገኘዋለሁ ብለህ ያሰብከው ቦታ ላይ ለመድረስ ደግሞ ጠንክረህ መስራት፣ በጽናትና በልበ-ሙሉነት መሮጥ አለብህ። በርግጥ እድሜህ በገፋ ቁጥር ጎልበትህና እግሮችህ ሊክዱህ ይችላሉ። ዋናው ትልቁ ችሎታ አእምሮህ ፈጣን እንደሆነ ማቆየቱ ላይ ነው” የምትለው ደራርቱ፤ የሩጫ ህይወቷ በጣም ረጅምና በድሎች ያሸበረቀ ነው። ይህ ድል እረጅም እድሜ ሊኖረው የቻለው በጠንካራ ስራ ምክንያት ነው። በ1996 ዓ.ም በተካሄደው የአትላንታ ኦሎምፒክ ሜዳሊያ ለማግኘት ያልተሳካላት ደራርቱ ቀጣዩ አላማዋ ከአራት አመታት በኋላ በሚካሄደው የሲድኒ ኦሎምፒክ ላይ ወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ነበር።

የደራርቱ በረጅም ርቀት ሩጫ ንግስትነትና መንፈሰ ጠንካራነት የፈረንጆቹ አዲሱ ሚሌኒዬም መጀመሪያ አመት ላይ በአውስትራሊያዋ ሲድኒ ከተማ በተካሄደው ኦሎምፒክ በደንብ የተረጋገጠበት ነበር። ከረጅም ጊዜ ጉዳት አገግማና የልጅ እናት ከሆነች በኋላ እንደገና ወደ ሩጫ ውድድር ተመልሳ አሸናፊ በመሆኗ “ምናልባት በቀዳሚነት ከማስቀምጣቸው ድሎቼ መሀል አንዱ ነው” ባለችው የሲድኒ ኦሎምፒክ የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር፤ እስከመጨረሻው ዙር ድረስ ከመሪዎቹ ጋር አብራ ከሮጠች በኋላ ልክ የደውሉ ድምጽ ሲሰማ ከሀገሯ ልጅ ጌጤ ዋሚ፣ ከፖርቱጋላዊቷ ፈርናንዶ ሮቤሮ፣ ከብሪታኒያዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ እና ከኬኒያዊቷ ቴግላ ላውሩፔ አፈትልካ የወጣችበት ታክቲክ ለእሷ የተለመደ፤ ለተመልካችና ለተፎካካሪዎቿ ግን እጅግ በጣም ድንቅ ክስተት ነበር። በአንድ ወቅት የውድድሮች ርቀት መጨረሻ ላይ ፍጥነት የመቀየር ችሎታዋን አስመልክታ ስትናገር “ውድድር ማብቂያ ላይ ከፊት ለፊቴ አስርም ሆኑ 20 አትሌቶች ቢኖሩ አልፌያቸው እንደምሄድ እተማመናለሁ” ያለችው ደራርቱ ቱሉ፤ የመጨረሻውን 400 ሜትር በ60.3 ሰከንዶች ዞራ መጨረሷ አስደናቂ የፍጥነት መቀየር ብቃቷን አሳይቷል።

የደራርቱን በሩጫው አለም ለረጅም ጊዜ ድል በድል መሆን በቅርበት ስትከታተል የነበረችውና በ1988ቱ የሶል ኦሎምፒክ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው ሮዛ ሞታ፤ እ.አ.አ በሚያዚያ ወር 2001 ዓ.ም የለንደን ማራቶንን ካሸነፈች አራት ወራት ቆይታ በኋላ በካናዳዋ ኤድመንተን ከተማ በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር አንደኛ ወጥታ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው ደራርቱ ቱሉን አስመልክታ በጊዜው በሰጠችው አስተያየት “የምንጊዜም ታላቋ ሴት የረጅም ርቀት ሯጭ” በማለት መስክራላታለች። “ደራርቱ በሁሉም አይነት የሩጫ መድረክ ታላቅነቷን አሳይታለች። በትራክ፣ በጎዳናና በሀገር አቋራጭ ውድድሮች ከሷ የበለጠ ድልን ያገኘ አትሌት ማንም የለም። ለእኔ የምንጊዜም ታላቅ አትሌት ነች” አለች ሮዛ ሞታ።

ስለቀዳሚዋ የረጅም ሩጫ ንግስት ደራርቱ ቱሉ ታላቅነት ጽፎ መጨረስ አይቻልም። ምክንያቱም እሷ ለብዙዎች ከሯጭነት በላይ ነችና። በሲድኒ ኦሎምፒክ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው ገዛኸኝ አበራ “አርአዬ የምትለው የስፖርት ሰው ማነው?” ተብሎ ሲጠየቅ “ያለምንም ጥርጥር ደራርቱ ቱሉ ነች” የሚል አጭርና ግልጽ ያለ መልስ ነበር የሰጠው።

እኔም በዚህ ላብቃ!

The post ሳቂታዋ የረጅም ርቀት ሩጫ ንግስት ደራርቱ ቱሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: “ከሉዊ ቫንሃል ይልቅ መውቀስ ያለብን ራሳችንን ነው”ዋይኒ ሩኒ

$
0
0

የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ዋይኒ ሩኒ ቡድናቸው በዘንድሮው ሲዝን በማስመዝገብ ላይ ካለው ደካማ ውጤት መወቀስ ያለባቸው ራሳቸው መሆናቸውን ያመነበትን መግለጫን ሰጥቷል፡፡

የውድድር ዘመኑ ወደ 2016 አዲስ ዓመት ከተሸጋገረ ወዲህ በዘጠኝ ግጥሚያዎች ላይ ለማንችስተር ዩናይትድ ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ወደ ጥሩ አቋሙ ለማንሰራራት የቻለው የ30 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ በቡድናቸው ላይ በተፈጠረው የውጤት ቀውስ ከአሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ይልቅ ራሳቸው በሜዳ ላይ ያሉት የቡድናቸው ተጨዋቾች መሆናቸውን በማመን በሰነዘረው አስተያየቱ የቡድናቸውን የእስካሁኑ የአቋም አለመረጋጋት ችግርን ለመቅረፍ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ በሚደረጉት ግጥሚያዎች እያንዳንዱ የቡድናቸው ተሰላፊዎች እስካሁን የተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት እንዲነሳሱ ጥሪውን አስተላልፎላቸዋል፡፡

Luis
‹‹በስኳዳችን በርካታ ተደናቂ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾችን ይዘናል፡፡ ሆኖም ግን በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የቡድናችን ተሰላፊዎች ከያዙት አቋም የወረደ የጨዋታ እንቅስቃሴን ሲያሳዩ ማየት በከፍተኛ ደረጃ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ሆኖብኛል›› በማለት ለዴይሊ ሚረር ጋዜጣ መግለጫውን መስጠት የጀመረው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል በመቀጠልም ‹‹በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ ቡድናችን መጥፎ ውጤቶች ሲፈጠሩበት በግንባር ቀደምትነት ሲወቀሱ የሚታዩ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጥፋተኝነት መፈረጅ ያለብን ወደ ሜዳ በመግባት ግጥሚያዎችን የምናደርገው ራሳችን የቡድናችን ተጨዋቾች ነን፡፡ ምክንያቱም ሉዊ ቫንሃል ይጠቅሙኛል ብለው ያመኑበት የጨዋታ ፕላንን ይዘው ወደ ሜዳ በመግባት የራሳቸውን ትልቅ ኃላፊነትን በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር በእያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በድል ለማጠናቀቅ የምንችልባቸው ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት በሜዳ ላይ ያለነው ተጨዋቾች እንጂ የሉዊ ቫንሃል ኃላፊነት ሊሆን አይገባውም›› የሚል አስተያየቱን አክሏል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ የዘንድሮው ሲዝንን ያጋመሰው የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎውን ወደ መጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች ደረጃ ለማሸጋገር በተሳነው ሁኔታ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን መጥፎ ውጤቶችን ለማካካስ የሚችሉት በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል ለሚያደርጓቸው የሶስት ውድድሮች ማለትም የፕሪሚየር ሊግ፣ የኤፍ.ኤ.ካፕና የዩሮፓ ሊግ ግጥሚያዎች ተራ በተራ ሙሉ ትኩረትን በመስጠት እንደሚሆን በማመን የ30 ዓመቱ የማንቸስተር ዩናይትድና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል በመቀጠል መግለጫውን የሰጠው ‹‹…በእስካሁኑ ሲዝን በተፈጠረብን የአቋም አለመረጋጋት የክለባችን ደጋፊዎችን ላስከፋንበት ጉዳይ ትክክለኛውን ማካካሻን የምናስገኝላቸው በቀሪው ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ዘመቻችንን እስከ 4ኛ ስፍራ ድረስ በመግባት ለማጠናቀቅ በዩሮፓ ሊግ ወይም በኤፍ.ኤ ካፕ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ ጥረትን የምናደርግ ሲሆን ይሆናል፡፡

በእርግጥ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የነበረን ዋነኛ አላማ የዩሮፓ ሊግ የዋንጫ ድልን መቀዳጀት አለመሆኑን አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን በክለባችን ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታዎች አንፃር በፍጥነት የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት በምናደርገው ጥረትን በቸልታ የምንመለከተው ሊሆን አይገባም›› በማለት ነው፡፡
‹‹ከቼልሲና ከሰንደርላንድ ጋር ባደረግናቸው ያለፉት ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎቻችንን በድምሩ አምስት ነጥቦችን ለማባከን በመገደዳችን የውድድር ዘመኑን እስከ 4ኛ ስፍራ በመግባት በምናደርገው ከፍተኛ የሆነ ጥረት ደካማ አቋም ማዘኑን ባለመደበቅ ሩኒ በሰነዘረው አስተያየት ‹‹በምንመኘው መልኩ በበቂ ሁኔታ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን ለመፍጠር ሲሳነን የታየው ግጥሚያ ነው በመከላከሉ ተግባርም ከዚህ ግጥሚያ ይልቅ ከዚህ ግጥሚያ ልዩ ትኩረትን ሰጥተን ስንሰራበት የዘለቅነው ከቆሙ ኳሶች የሚደረጉ ጥቃቶችን የመቋቋም ተግባርን በአግባቡ ለመፈፀም ሲሳነን ታይቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከግጥሚያው አንድ ነጥብ እንኳን ሳናገኝ በመቅረታችን የምንወቀሰው ራሳችንን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም የምንመኘው አይነት ጥሩ አቋምን ለመያዝ ያልቻልንበት ግጥሚያ ነው ከመከላከሉ ተግባርም ከዚህ ግጥሚያ ልዩ ትኩረትን ሰጥተን ስንሰራበት የዘለቅነው ከቆሙ ኳሶች የሚደረጉ ጥቃቶችን የመቋቋም ተግባርን በአግባቡ ለመፈፀም ሲሳነን ታይቷል፡፡

ከዚህ አንፃር ከግጥሚያው አንድ ነጥብ እንኳን ሳናገኝ በመቅረታችን የምንወቅሰው ራሳችንን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም የምንመኘው አይነት ጥሩ አቋምን ለመያዝ ያልቻልንበት ግጥሚያ ነው፡፡ ከቼልሲ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረግናቸው ሁለት ተከታታይ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ ለሶስት ነጥቦችን በመጣላችን ምናልባትም በቀጣዩ ሲዝን ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ለመመለስ የምንችለው የዩሮፓ ሊግ ውድድር የዋንጫ ሽልማትን ለማግኘት ስንችል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን ስ ግን በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል 12 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በመኖራቸው የሚፈጠረውን ነገርን እርግጠኛ ሆነን ለመናገር የማንችል መሆኑን በማመን ነው›› ብሏል፡፡

ደግሞም የዋንጫ ሽልማትን ካገኘን የሶስት ዓመታት ጊዜ በመቆጠሩ ከእንግዲህ የምናማርጠው ውድድር ሊኖረን አይገባም፡፡ የዘንድሮ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎአችንን በዋንጫ ለማጠናቀቅ ከኤፍ.ሲ ሚትላንድ ጋር የሚጠበቅብን የደርሶ መልስ አንስቶ ለእያንዳንዱ በውድድሩ ጨዋታዎች ሙሉ ትኩረትን በመስጠት እስከ ሲዝኑ መጨረሻ ድረስ ለመዝለቅ የዋንጫውን ድል ለመቀዳጀት የተቻለንን ሁሉ ጥረት እንድናደርግ ለቡድናችን ተሰላፊዎች ከዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፍላቸዋለሁ›› በማለት ነው፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ ውድድር ሲሳተፍ የዘንድሮው ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ ከዚህ በፊት በጨመረሻ ጊዜ በ2011-12 ሲዝን በዚህ ውድድር ተሳትፎው ከመጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች ደረጃ ለመሸጋገር አለመቻሉ ይታወሳል፡፡ በዚህ ውድድር ከዚህ በፊት ዘጠኝ ጊዜ የመሳተፍ እድልን አግኝቶም ከሩብ ፍፃሜው የተሻለ ውጤትን ያስመዘገበው አንድ ጊዜ ብቻ ማለትም ከ1964-65 ሲዝን ነበር፡፡

ያኔ በሃንጋሪው ፌሬንቾቫሮቭ በግማሽ ፍፃሜው ደረጃ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ የዘንድሮው ሲዝን ቢሆን ማንቸስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ /የቀድሞው የማህበረሰቡ ዋንጫ/ ውድድርን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋንጫ ባለቤትነት ለማጠናቀቅ የሚጠበቀው ፈተና ቀላል አይሆንለትም፡፡ ምክንያቱም በውድድሩ የመጨረሻው 16 ቡድኖች ደረጃ ቦሪሽያ ዶርትሙንድ፣ ናፖሊ፣ ሴቪያ፣ ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም፣ ፊዮረንቲና፣ ባየር ሌቨርኩዘንና ኤፍ.ሲ ፖርቶን የመሳሰሉት ጠንካራ ክለቦች አብረውት ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ባሻገር የእንግሊዝ ክለቦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዚህ ውድድር ተሳትፏቸው ሊጠቀስ የሚችል ትልቅ ስኬት የሌላቸው መሆኑ ከግንዛቤ ሲገባም ማንቸስተር ዩናይትድ የዘንድሮን ሲዝንን በዩሮፓ ሊግ የሻምፒዮንነት ክብር ለማጠናቀቅ የሚኖረው ተስፋ ዝቅተኛ ሊባል የሚገባው ነው፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣይ ግጥሚያውን የሚያደርገው በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በዝቅተኛ ዲቪዚዮኑ ሽዌስበሪ ሜዳ ነው፡፡ ከሽዌስበሪ ጋር በሚረገው የኤፍ.ኤ.ካፕ 5ኛው ዙር ግጥሚያን በማንቸስተር ዩናይትድ መደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት ይጀምራሉ የሚል ግምት ከተሰጣቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነው ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል ማሮዋን ፊላኒ የክለባችን ሲዝንን እስከ አራተኛ የማጠናቀቅ ተስፋን በማስመልከት ምን አይነት አስተያየት አለህ በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው ‹‹በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በጠንካራ የመሸናነፍ ፉክክር በመዳረግ ላይ በመሆናቸው ይህንን አላማችንን ለማሳካት ከፊታችን ባሉት 12 የሊጉ ጨዋታዎች የሚጠብቀን ፈተና ቀላል አይሆንም፡፡
ከዚህ አንፃር እስከ 4ኛ ስፍራ በመግባት አላማችንን ለማሳካት በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች በበቂ ሁኔታ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን በመፍጠር ብዛት ያላቸው ጎሎችን የማስቆጠር ትልቅ ኃላፊነት እንደሚጠብቀን አምናለሁ፡፡

ይህንን ስል ግን በአሁኑ ወቅት 4ኛ ስፍራን ከያዘው ክለብ ጋር ያለን የነጥብ ልዩነት ያንን ያህል ሰፊ የሚባል ባለመሆኑ እስካሁንም ድረስ የውድድር ዘመኑን ቢያንስ እስከ አራተኛ ስፍራ በግባት የማጠናቀቅ ተስፋ እንዳለን አምናለሁ፡፡ ይህንን አላማችንን በአግባቡ ለመፈፀም እንምንችል ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ የምንሆነው ከፊታችን ያሉት እያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በድል ለማጠናቀቅ ስንችል ብቻ ይሆናል፡፡ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል በሚደረጉት ግጥሚያዎች ከእኛ በላይ ካሉት ክለቦች ውስጥ አርሰናል፣ ቶተንሃምና ሌስተር ሲቲን የምናገኝባቸው በመሆኑም በመሀላችን ያለውን የነጥቦች ልዩነት ለመቅረፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክትልን እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ በሰንደርላንድ 2ለ1 የተሸነፍንበት ጨዋታ ያለመውረድ ትግልን በማድረግ ላይ ያሉትን ክለቦችን መግጠም ምን እንደሚመስል ትምህርትን ሰጥቶናል፡፡ በእኔ አመለካት በሲዝኑ ወሳኝ ወቅት አንድ ትልቁ ፈተና የመውረድ ስጋት ያለባቸው ቡድኖችን መፋለም ነው፡፡ ይህንን ለመቋቋም ግን ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ጉይ ጎል የማስቆጠር ቅድሚያን መያዝ መሆኑን አምናለሁ›› በማለት ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግልህ ስለ ያዝከው አቋም ምን አስተያየት አለህ በሚል ለቀረለበት ጥያቄ ደግሞ ‹‹በተከታታይ ግጥሚያዎች የመጀመሪያው ምርጫዬ በሆነው በመሃለ ማካይ ሚና በመሰለፍ ላይ በመሆኔ በራሴ የመተማመን መንፈሴን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ያማረ አድርጎልኛል ለማለት እችላለሁ፡፡ ተስፋ የማደርገውም በራስ የመተማመን መንፈሴ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በተሻለ ሁኔታ ያማረ ለመሆን በመቻሉ ከፊታችን የመሰለፍ ዕድልን በማገኝባቸው ግጥሚያዎች በእስካሁኑም በተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት እችላለሁ ብዬ የቅርብ ጊዜ አቋሜ ጥሩ እንዲሆን ከረዳኝ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የሌላው ከአብዛኛዎቹ የቡድናችን ተጨዋቾች ጋር ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል አብረን ለመሰለፍ መቻላችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ በመሀላችን ያለውን የጨዋታ እንቅስቃሴን መናበብን ይበልጥ አሳድጎታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማይክል ካሪክ ባሻገር ሞርጋን ሽኔደርሊንና ባስቲያን ሽዌንሲቲገር ተደናቂ ብቃቶችና ሰፊ ልምድን የተላበሱ ተጨዋቾች መሆናቸው ማንኛውም ጋር ጥምረትን ፈጥሮ መጫወት ያንን ያህል አስቸጋሪ አልሆነብኝም፡፡

እርግጠኛ ሆኜ የምናገረውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለማንቸስተር ዩናይትድ በተሰለፍኩባቸው በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች በሜዳ ላይ በለኝ የጨዋታ እንቅስቃሴዬ ሙሉ ደስተኛ የመሆን ባህል እስኪደርሱ መምጣት ችያለሁ፡፡ በተለይም ለማንቸስተር ዩናይትድ የምሰለፍበት ቀጣዩ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዬ ወደ እንግሊዝ ከመጣሁ ወዲህ 200ኛው የውድድሩ ጨዋታዬ ስለሚሆን ከወዲሁ በጉጉት እየተጠባበቅኩት መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ›› የሚል ምላሽን ሰጥቷል፡፡
 
 


Sport: ብዙ ያልተባለለት የሌስተር ሲቲው ጀግና ‹‹የማኬሌሊ ሙያን መመለስ ችሏል›› ጋሬዝ ኩክ

$
0
0

 

በዘንድሮው ሲዝን ሌስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዘመቻው የመሪነቱ ስፍራ ለመቀመጥ እንዲችል በግንባር ቀደምትነት በብዙዎች በመጠቀስ ላይ የሚገኙት የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋቾች እንግሊዛዊው አጥቂ ጃሚ ቨርዲና አልጄሪያዊው ኢንተርናሽናል ራሂድ ማህሬዝ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ተጨዋቾች በእስካሁኑ የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንዲቀመጥ ያስቻሉት ቁልፍ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
lecter cite N'golo Kante

በዛኑ መጠን ግን በቡድኑ የመሃል አማካይ ክፍል ተጨዋቾች የሆኑት ንጎሎ ካንቴና ዳ ድሪንክዋተር በእስካሁኑ ሲዝን ብዙ ያልተዘመረላቸው የሌስተር ሲቲ ጥንካሬ መሰረታዊ ምንጭ መሆናቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጣሊያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒየሪ ቡድን ባደረጋቸው ተከታታይ ጠንካራ ግጥሚያዎች ላይ ባሳዩት የማይዋዥቅ ታላላቅ ፐርፎርማንሳቸው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በተለይም ሌስተር ሲቲ ባለፈው በኢምሬትስ ስቴዲየም ያደረገውን የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያን 2ለ1 በሆነ ውጤት ለመሸነፍ ቢገደድም የ24 ዓመቱ የፈረንሳይ በመሀል አማካይ ክፍል በርካታ የአርሰናል የማጥቃት እንቅስቃሴን የማጨናገፉን በሜዳ ላይ ከነበሩት የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ብዛት ያላቸው ስኬታማ ታክሎን በመግባት ሲታወስ የሚኖር ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡

ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም የአርሰናሉ ዝነኛ ጎል አዳኝ ቲዮሪ ኦንሪ በሰነዘረው አስተያየት ሊስተር ሲቲ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ በተቆጠረበት ጎል 2ለ1 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ ቢገደድም የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች የምለው ንጎሎ ኮንቴን ነው፡፡ ምክንያቱም በሌስተር ሲቲ የተከላካይ መስመር ላይ ሲፈጠር የታየው ጫናን በአግባቡ በመቀነስ እጅግ ምርጥ ብቃት ያለው የሆልዲንግ ሚድል ሚና ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር ችሏል፡፡ በእኔ አመለካከት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቦታው ላይ በምርጥ ብቃቱ አቻ የማይገኝለት ተጨዋች ነው በማለት አድንቆታል፡፡

ክላውዲዮ ራኒየሪ የዘንድሮው ሲዝን ከመጀመሩ በፊት ከፈረንሳዩ ኪን ክለብ 5.6 ሚሊየን ፓውንድ የገዙት ንጎሎ ካንቴን ከዚህ በፊት የቼልሲና የሪያል ማድሪድ የነበረው ክሎድ ማኬሌሌን የጨዋታ ሚናው ለበርካታ ዓመታት በኋላ እንዳስታወሰው ምክንያት የሆነኝ ተጨዋች ነው በሚል የገለፀው ደግሞ የቢቢሲው የፉትቦል ተንታኝ ጋሬዝ ሉክ ነው፡፡ ‹‹ሌስተር ሲቲ በጨዋታው 54ኛው ደቂቃ ላይ ዳኒ ሴምፕሰን በቀይ ካርድ ባያጣው ኖሮ እንደ ንጎሎ ሳንቲ አስገራሚ የመሀል አማካይ ክፍል ተደናቂ ብቃት ግጥሚያውን ቢያነሳ ነጥብ በመጋራት ለማጠናቀቅ በተከገባው ነበር›› ያለው ጋሬሬ ሉክ በመቀጠል ‹‹ሳንቴ ለበርካታ ዓመታት በኋላ የክሎድ ማኬሌሊ የጨዋታ ሚና በማለት የምንገልፀው አጨዋወትን ወደ እንግሊዝ ፉትቦል ለመመለስ የቻለ ተጨዋች ነው፡፡ በእኔ አመለካከትም በእስካሁኑ ሲዝን ብዙ ያልተዘመረለት የሌስተር ሲቲ ትልቁ የአማካይ ክፍል ጀግና ነው›› በማለት የ24 ዓመቱ ‹‹ሌስተር ሲቲ ቁልፍ የመሃል አማካይን ገልፆታል፡፡

ሳንቲ በዘንድሮው ሲዝን በእያንዳንዱ የሌስተር ሲቲ ግጥሚያዎች በመከላከል ላይ ያተኮረ ተደናቂ ተግባር የአማካይ ክፍል ተግባርን መፈፀም መቻሉ የዘመናዊ ፉትቦል የማኬሌሊ የጨዋታ ሚና ለምን እየተረሳ መጣ የሚለውን አጀንዳን ያስነሳ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የኤ.ኤስ.ፒ.ኤን የፉትቦል ተንታኞች ከዚህ በታች ያለውን ሙያዊ ትንተናቸውን አስነብበዋል፡፡ የሪያል ማድሪድ ፕሬሬዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በ2003 ክሎድ ማኬሌሊን ለቼልሲ የሸጡበት ምክንያትን ያብራሩት ‹‹የኳስ ቁጥጥር ለእግሩ በመቆየት ከሶስት ሜትሮች በላይ ለመጓዝ አይችልም፡፡ በማጥቃቱ እንቅስቃሴ ምንም አይነት ተሳትፎ የሌለው ተጨዋች ነው፡፡ ክለባችን ወጣት ተጨዋቾችን በማሳደጉም የማኬሌሊ ማንነት ሙሉ ለሙሉ መረሳቱ የማይቀር ነው›› በማለት ነበር፡፡ ፔሬዝ ይህንን በማለታቸው ግን አንድ መሰረታዊ  የሆነ ነገር ሙሉ ለሙሉ ከአይምሯቸው አስወጥተውታል ለማለት ይቻላል፡፡

kante

የማኬሌሊ የሪያል ማድሪድ ጓደኛ የነበረው የቀድሞው የእንግሊዝ ኢንተርናሽናል ስቲቭ ማክማነመን ግን ፍሎንቲኖ ፔሬዝ ስለፈረንሳዊው አማካይ ትልቅ ግልጋሎት ያልተረዱትን ነገር ቁልጭ አድርጎ አሳይቷቸዋል፡፡ በተለይም ማክማነመን የግል ህይወቱን በያዘው መፅሐፍ ማኬሌሊ ለሪያል ማድሪድ ያለው ከማንም የቡድኑ ተሰላፊ በብዙ መልክ የተሻለ ወሳኝነት ከክለባቸው ውጪ ያሉት ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እውቅናን ሊያገኝ አለመቻሉን በዝርዝር አብራርቶታል፡፡

ማክናመነን በዛ መፅሐፉ ‹‹የሪያል ማድሪድ የመጀመሪያው ምዕራፍ የጋላታክቲኮስ ዘመን ሙሉ ለሙሉ ማክተም የጀመረው ከማኬሌሊ ወደ ቼልሲ ዝውውር ከማድረግ ጋር በተያያዘ ነው›› እስከማለት ደረጃ ደርሷል፡፡ ማክማነመን ካኬሌሊ ለሪያል ማድሪድ የነበረው ወሳኝነት በማሳየት በማብራሪያው በአስቶባዮግራፊው ላይ ያስነበበው››

የሪያል ማድሪድ የጋላክቲኮስ ፍልስፍና የሚገለፀው በበርካታ በማጥቃት ላይ ያተኮረ አይምሮን በተላበሱት ተጨዋቾች መሆኑን አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ለጋላክቲኮስ ፍልስፍና በዋነኝነት የሚጠቀስ መሰረት የሆነው በቡድኑ የመሃል አማካይ የመመላከል ሽፋንን የሚሰጥለት ክሎድ ማኬሊሊ ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በመፈፀም የሪያል ማድሪድ እጅግ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ ዘልቋል፡፡ ሆኖም ግን በርካታ ሰዎች ይልቅ ቁልፍ ሚናውን ዘንግተውታል፡፡ አብረነው የምንሰለፍበት ተጨዋች ብቻ ሪያል ማድሪድ ስለማኬሌሊ ጥርስ የሌለው አንበሳ እንዲሆን እናውቅ ነበር፡፡

በዛን ወቅት ከማኬሌሊ ጋር የሪያል ማድሪድ የተሰለፉበት እያንዳንዱ ተጨዋቾችም ብትጤቃቸው የሚነግሯችሁ ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን የቡድኑ ጓደኞች ቁልፍ ተጨዋቾቻችንን በሃዘን ታጅበን በሄደበት መልካም ነገሮች እንዲገጥሙት በመመኘት ከመሸኘት በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበረውም፡፡

የማኬሌሊ በጁላይ 2003 ሪያል ማድሪድን መልቀቅ የፔሬዝ የጋላክቲኮስ ፍልስፍና መፈረካከስን በይፋ ያስጀመረው ሆኗል፡፡ በአንፃሩ ግን የማኬሌሊ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስ የቼልሲ ወደ ወርቃማ ዘመን የመግባትን የመጀመሪያውን ምዕራፍን አስጀምሮታል›› በማለት ነው፡፡

ፈረንሳዊው የዓለም ፉትቦል የምንጊዜውም ዝነኛ ዚነዲን ዚዳንም ይህንን የማክማነመን አባባልን በማጠናከር በሰነዘረው አስተያየት በ2003 ፕሪ ሲዝን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ማኬሌሊን ለቼልሲ በመሸጥ ዴቪ ቤካምን ከማንቸስተር ዩናይትድ በ25 ሚሊየን ፓውንድ የገዙበት ተግባራቸውን ተኝቶት ነበር፡፡ ዚዙ በወቅቱ በፔሬዝ ሌላ የማጥቃት አዕምሮን የተላበሰ ተጨዋች በማኬሌሊ ምትክ ያስፈረሙበት ተግባራቸው ለቡድናቸው በሜዳ ላይ የሚኖረውን ጠቀሜታን በመጠራጠር አስተያየቱን ሰጥቶ የነበረው ‹‹…ቤንትሌይ ሞዴል ያላት መኪናህን ሞተር ነቅለህ ከወጣኸው በኋላ የመኪናዋ ሽፋንን በወርቅ ማልበስህ ጠቀሜታው ምንድነው በሚል ነበር ፔሬዝ ወዲያውኑ ይህንን የዚዳን አባባልን በማጣጣል በሰነዘሩት አስተያየት ለማኬሌሊ ደመወዝ ስንከፍል የቆየንበት ምክንያት ምን እንደሆነ በትክክል ለመረዳት ተችግሬያለሁ›› ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ዚዳን የጋላክቲኮስ ፍልስፍናቸው መሪ ተዋናይ በመሆኑ በትችት አዘሉ አባባሉ ቂምን ሊይዙበት አልፈለጉም፡፡ ፔሬዝና በስራቸው የነበሩት የሪያል ማድሪድ አመራሮች እንደ ማኬሌሊ ያለ የአማካይ ክፍል ‹‹ዲስትሮዬርስ›› በቡድናቸው ቋሚ አሰላለፍ ማየት አጥብቀው የተጠየፉበት ወቅት እንደነበር በማስታወስ የቶተንሃም ሆትስበርስ ኮቺንግ ስታፍ አባል ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የአጥቂ መስመር ተጨዋች ሌስ ፈረንዲናንድ በቅርቡ በሰነዘረው አስተያየት ፔሬዝ በማኬሌሊ ሚና የነበራቸው ጥላቻን ከመቃወም ይልቅ ፈረንሳዊው ዝነኛ የተጋጣሚ ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴን በማላሸት ላይ ሙሉ ትኩረትን ያደረገው የጨዋታ ሚናን በማቋሸሽ ‹‹በመጀመሪያውኑም ቢሆን ማኬሌሊ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመሳተፍ እድል ሊፈቀርት አይገባም ነበር፡፡ የዓለማችን እጅግ ተወዳጅ የሊግ ውድድራችን መቆሸሽ የጀመረው የጨዋታ ውበትን በማጥፋት ተግባር የተሰማራ ተጨዋች ለቼልሲ ከፈረመ በኋላ ነው፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት የፕሪሚየር ሊግ ካየኋቸው መጥፎ አጋጣሚዎች የማኬሌሊ በቼልሲ የመሃል አማካይ መሰለፍ ነው›› ብሎ ነበር፡፡

ሌስ ፈረንዲናንድ ይህንን ለማለት ያነሳሳው ለፈረንሳዊው አማካይ የግል ጥላቻን በማሳደር ሳይሆን የማኬሌሊ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስን ተከትሎ ከ2003 እስከ 2010 ድረስ ባሉት ዓመታት በመከላከል ላይ ያተኮረ ትኩረትን የሚያደርጉ የመሃል አማካዮች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንደ አሸን መፍላታቸውን በመታዘቡ ነው፡፡ ለሰባትና ስምንት ዓመታት በላይ በፕሪሚየር ሊግ ውድድር በብዛት የታዩትና ከራሳቸው ቡድን ሁለት የመሃል ተከላካዮች ፊት ለፊት የተጋጣሚ ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴን በእንጭጩ በማጨናገፍ ተግባር ከመሰማራት ውጪ የመሀል ሜዳውን መስመርን አቋርጠው የማለፍ ፍላጎት የሌላቸው የሆልዲንግ ሚድፊልደሮች በጠቅላላ ‹‹የማኬሌሊ ሚና›› ባለቤቶች የሚል ተቀፅላን ይዘው ዘልቀዋል፡፡ ይህንን በመታዘብም ሌስ ፈረንዲናንድ ከሁለትና ሶስት ዓመታት በፊት በተደጋጋሚ በስማቸው መግለጫዎች ጊዜው የአማካይ ክፍል ኢስትሮዬርስን የምናጠፋበት ሊሆን ይገባል›› የሚል ጥሪውን ለፕሪሚየር ሊግ መላው ቤተሰብ አስተላልፎ ነበር፡፡

‹‹ማኬሌሊ ሚና›› በዛን ወቅት የስኬታማነት የዓለም ቋንቋ መሆኑን የተረዱት ባለሙያዎች ግን በበቂ ሁኔታ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሬድ ሮም /የኢብራሂሞቪች/ አብዮት በቼልሲ የተቀጣጠለበት ድፍን አንድ ዓመት በኋላ በስታምፎርድ ብሪጅ ስራን ክላውድዮ በስታምፎርድ ብሪጅ ስራ ክላውዲዮ ራኒየሪ የተረከቡት ጆሴ ሞውሪኖ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ስር ከ2004-2007 ባሉት ዓመታት ጆን ቴና ሪካርዶ ካርቫልሆ ‹‹አይነኬ›› የቼልሲ የመሀል ተከላካይ ክፍል መደበኛ ቋሚ ተሰላፊዎቹ ሆነው ዘልቀዋል፡፡

ከቴሪና ከካርቫልሆነ አፍንጫ ስር አጭር ቁመት ያለው ፈረንሳዊው መታየቱ የሞውሪኖ ቼልሲ ቋሚ አሰላለፍ የተለመደ መግለጫ ነበር፡፡ ማኬሌሊ የተጋጣሚ ቡድን እያንዳንዱ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማጨናገፍ ዘመቻ በመሰማራት በቴሪና በካርቫልሆ የመከላከሉ ኃላፊነትን በግማሽ ይቀርፉላቸዋል፡፡ ከተጋጣሚ ቡድን ተሰላፊዎች በቅድሚያ ኳስን ማስጣል ከዛም ለራሱ ቡድን በማጥቃት ላይ ያተኮረ አማካዮች የፈገግታ መንፈስን በገፅታው ላይ ብልጭ በማድረግ አጭር ፓስን ማድረስ የያኔው የቼልሲ 16 ቁጥር አይነተኛው መገለጫ ነበር፡፡ በተለይም ሞውሪኖ 4-4-2 የጨዋታ ፎርሜሽን በሚጠበቀው ተጋጣሚ ቡድኖችን የማጥቃት እንቅስቃሴን ማጨናገፍ ማኬሌሊን በትክክለኛው መፍትሄቸው አድርገውታል፡፡

ምክንያቱም ፈረንሳዊው በተጋጣሚ ቡድን ሁለቱ የፊት አጥቂዎችና በአራቱ አማካዮች መካከል ባለው ቦታ እየገባ አርስ በርስ እንዲለያዩ የሚያደርግበት ኳስ በማጨናገፍ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ይሰማራል፡፡ በቻርልነተን አትሌቲኮ ተሰላፊዎች ዘመኑ ከቼልሲ ጋር በሚደረጉ ግጥሚያዎች ከማኬሌሊ ጋር በርካታ የአማካይ ክፍል ትግሎችን ሲያደርግ የዘለቀው ማት ሀላንድ የፈረንሳዊው አስቸጋሪ ተጋጣሚነትን በማንፀባረቅ በአንድ ወቅት መግለጫውን ሲሰጥ የተደመጠው ‹‹ቼልሲን በምንገጥምባቸው እያንዳንዱ የቡድናችን ትልቅ ራስ ምታት የሚሆነው ማኬሌሊ የጨዋታ እንቅስቃሴ መሆኑን አስታውሳለሁ፡፡

ምክንያቱም በቡድኑ የመከላከል ተግባር ጠልቆ በመግባት ይጫወታል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ከቼልሲ አራት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች አንዱ እስከመምሰል ደረጃ ይደርሳል፡፡ ቼልሲ በመጀመሪያው የሞውሪኖ የስራ ዘመኑ በጭራሽ የማይከፈት የመከላከል ስትራቴጂ የነበረው በማኬሌሊ ዋነኛ ተዋናይነት ነው ለማለት እችላለሁ፡፡ ይህንን በማየትም በእኔ የተጨዋችነት ዘመን የፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች በቡድናቸው የመሀል አማካይ ክፍል ቢያንስ አንድ የማኬሌሊ ሚና ባለቤትን መያዝን የውድ ግዴታ አድርገውት ነበር ለማለት እችላለሁ፡፡ ከማኬሌሊ ወደ እንግሊዝ ፉትቦል መምጣት በፊት የመከላከል ተግባርን በጥልቀት የሚፈጽም አማካይነት አልገጠምኩም፡፡

በእርግጥ የአስፒዎች ታውን ጅምማጊልተንም በቡድኑ የመሀል ተከላካይ ሚና ዘልቆ በመግባት ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ማጊልተን የኳስ ቁጥጥርን ካገኘ በኋላ ድሪብሊንግ የመሀል መስመሩን አቋርጦ በማለፍ የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ጭምር ይሳተፋል፡፡ ማኬሌሊ ግን የመሃል ሜዳ መስር ማቋረጥ ቀርቶ ሊያቀርበው አይመኝም በማለት ነው፡፡ በእርግጥ ራኒየሪ ፈረንሳዊውን ከሪያል ማድሪድ በመግዛት የማኬሌሊ ሚናን በእንግሊዝ ፉትቦል ካስተዋወቁት በኋላ ሌሎችም በሊጉ የሚገኙ አሰልጣኞች በቡድናቸው አማካይ ክፍል የጨዋታ እንቅስቃሴን ማበላሸት አላማው ያደረገ ተጨዋችን ማየትን ተመኝተዋል፡፡

ለምሳሌ ሊቨርፑል ሀቪየር ማስቺራኖ እንዲሁም ቶተንሃም ዴዲዬ ዛኮራን የገዙት ለቡድናቸው የማኬሌሊ ሚናን እንዲፈፅሙላቸው በመመኘት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የማራኪ ፉትቦል አቀንቃኝ ነኝ የሚሉት የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር አሌክስ ሶንግን በማኬሌሊ ሚና ለማሰማራት የወሰኑበት ጥቂት ዓመታት ታይተዋል፡፡ በአንፃሩ ቼልሲ በአንድ ማኬሌሊ ባለመገደብ በወጣትነት የዕድሜ ክልል እያለ በማጥቃት ላይ ያተኮረ የአማካይ ክፍል ሚና የነበረው ጆን አቢ ሚኬልን ወደ አማካይ ክፍል ኳስ አስጣይነት ሚና ቀይሮታል፡፡

አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንም ማንቸስተር ዩናይትድን የማኬሌሊ ሚና ባለቤት ለማድረግ ሲመኙ ታይተዋል፡፡ ነገር  ግን በዚህ ምኞታቸው ፍሬያማ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ማይክል ካሪክን በ2006 ፕሪሲዝን ከቶተንሃም ከገዙ በኋላ ለመረዳት ችለዋል፡፡ ፈርጉሰን እንግሊዛዊው አማካይን የገዙት የማኬሌሊ ሚናን እንዲፈፅምላቸው በማለም ነበር፡፡ ባሰቡትም መልኩ ካሪክን በሆልዲንግ ሚና ላይ ተጠቅመውበታል፡፡

ሆኖም ግን ካሪክ የኳስ ቁጥጥርን ከነጠቀ በኋላ እንደማኬሌሊ አጭር ፓስን ወደ አማካይ ክፍል ነካ በማድረግ የሚገደብ አይነት ተጨዋች ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡፡ ምክንያቱም ካሪክ በውጤታማ ረጅም ፓሶች ለአጥቂ መስመር ተሰላፊዎች የማድረስ ባህል ያለው ተጨዋች ነው፡፡ ፈርጉሰንም በካሪክ ሳይዛነፉና ተለክተው በሚላኩት ረጅም ፓሶች በመማረክ የማኬሌሊ ሚና ንድፍ ሃሳባቸውን ሙሉ ለሙሉ ከአይምሯቸው አስወጥተውታል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶማሊያን አሸነፈ

$
0
0

ethiopia

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሶማሊያ ጋር ለ2017ቱ ከ20 በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለመግባት ያደረገውን የመጀመረ የማጣሪያ ጨዋታ በ2ለ1 አሸነፈ::

ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ይህን ድል መቀዳጀቱን የስፖርት ተንታኞች ገልጸዋል::

የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ከሶማሊያ ጋር ሲያደርግ ወደ መቋድሾ አያመራም:: እዚያ ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ የመልስ ጨዋታው በገለለተኛ ሃገር የሚደረግ ይሆናል:: በዚህም መሰረት ቀጣዩ ጨዋታ ጅቡቲ ላይ ይደረጋል ሲሉ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል::

ብሄራዊ ቡድናችን በዛምቢያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሶማሊያ አቻውን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ሱማሊያ አንድ ጎል ከሜዳዋ ውጭ በማስቆጠሯ ጅቡቲ ላይ አንድ ለዜሮ ካሸነፈች ወደ ቀጣይ ዙር ልታልፍ ትችላለች:: ሆኖም ግን ብሔራዊ ቡድናችን ከሜዳው ውጭ የገባበትን የግብ ዕዳ ለመክፈል ጠንክሮ መጫወትና ጎል ማግባት ይጠበቅበታል::

ኢትዮጵያዊት ሹኮ ገነሞ በቪየና ከተማ ማራቶን የሴቶቹን በድል አጠናቀቀች – VOA

$
0
0

43B6F447-046C-4C76-BD6E-CBABC243A597_cx0_cy4_cw0_w1000_r1_s_r1ኢትዮጵያዊት አትሌት ሹኮ ገነሞ በቪየና አሸንፋለች

በሮም ማራቶን አሸናፊዎቹ የሁለቱን አገሮች አትሌቶች ናቸው አሞስ ኪፕሩቶ በወንዶቹ፣ ራህማ ቱሳ በሴቶቹ ቀድመው ገብተዋል። በቪየና ከተማ ማራቶን የሴቶቹን በድል ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊት ናት ሹኮ ገነሞ ትባላለች።

በሮም ማራቶን አሸናፊዎቹ የሁለቱን አገሮች አትሌቶች ናቸው አሞስ ኪፕሩቶ በወንዶቹ፣ ራህማ ቱሳ በሴቶቹ ቀድመው ገብተዋል። በቪየና ከተማ ማራቶን የሴቶቹን በድል ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊት ናት ሹኮ ገነሞ ትባላለች።ሮበርት ቼሞሲን ከኬንያ የወንዶቹን በአንደኝነት አጠናቋል። የዛሬው የስፖርት ፕሮግራም በአትሌቲክሱ ስፖርት ላይ ያተኮረ ዝርዝር ሰሎሞን ክፍሌ አጠናቅሯል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።[jwplayer mediaid=”53233″]

Sport: በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ መቆየትና መባረር ያለባቸው ተጨዋቾች 

$
0
0

በዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች የቀረበ  

ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያላቸው የአሁኑ ኮንትራት የሚጠናቀቀው በጁን 2017 ቢሆንም በዘንድሮ ሲዝን ለቡድኑ ከሚጠበቅባቸው ያነሰ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በመገደባቸው ግን የኮንትራት ውላቸው ከማለቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ከኦልድትራፎርድ ሥራ የመነሳታቸው ተስፋ እየሰፋ በመምጣት ላይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ የእግርኳስ ተንታኞች በማንሳት ላይ ያሉት ጥያቄም ሉዊ ቫንሃል ተከትለው ከዘንድሮ ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ኦልድትራፎርድን የሚለቁት በክለቡ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾች እነማን ይሆናሉ የሚል ነው፡፡

ቫንሃልን በመተካት የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝነት ስራን በሚረከቡት በጆሴ ሞውሪኖ ወይም በሌላ ባለሙያ ስር እነማንስ የክለቡ አቅድ አካል ሆነው የመዝለቅ እድል ይኖራቸዋል? የሚለውም ሌላ በመነሳት ላይ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች  በማንችስተር ዩናይትድ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾችን ወቅታዊ አቋምን በመገምገም ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ክለብን የሚለቁትና ለተጨማሪ ዓመታት የማንችስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆነው መዝለቅ የሚገባቸው ተጨዋቾችን ማንነትን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡

david Gea

መቆየት የሚገባቸው

ዴቪድ ዳሂአ

ባለፈው ሴፕቴምበር ወር ማንቸስተር ዩናይትድ የቀረበለትን አዲስ ለተጨማሪ አራት ዓመታት የሚዘልቅ ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ፈርሟል፡፡ ከዛ ወዲህ የወደፊት እጣ ፈንታውን በተመለከተ የተፈጠረበት ምንም አይነት ውዝግብ ባለመኖሩ የዳሂአ የማንቸስተር ዩናይትድ በርን ለተጨማሪ ዓመታት አጠራጣሪ አይመስልም፡፡ ክለቡ ለዳሂአ ከስፖንሰርሺፕ ውሎቹ የተወሰነ ፐርሰንት ገቢን ሊፈጥርለት ማቀዱም ስፔናዊው ግብ ጠባቂን ደስተኛ አድርጎት በኦልድትራፎርድ እንደሚቆየው ይጠበቃል፡፡

ማቲዬ ደርሚን

የዘንድሮ ሲዝን ከመጋመሱ በፊት በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የነበረውን ደካማ አቋማችን በማረም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሩ አቋም ለመገኘት ችሏል፡፡ በተለይም ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርቡ በቼልሲና ከሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ያበረከተው ታላቅ ፐርፎርማንስን የጣሊያናዊው ኢንተርናሽናል በሂደት በእንግሊዝ ፉትቦል የጨዋታ ስታይል ጋር በተገቢው መልኩ ለማዋሃድ ለመቻሉ በቂ ማስረጃ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር ደርሚንን ለበርካታ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ ቀኝ ተመላላሽ ሚና የመጀመሪያው ተመራጭ ተጨዋች ሆኖ እንደሚዘልቅ ይጠበቃል፡፡

ሉክ ሻው

የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ ግራ ተመላላሽ የዘንድሮን ሲዝንን በጥሩ አቋም ሆኖ ለመክፈት ቢችልም በሴፕቴምበር ወር ከፒኤስቪ አይንደሆቨን ጋር በተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ዝግጅት ግጥሚያ ያጋጠመው አደገኛ የእግር ስብራት ለበርካታ ወራት ከሜዳ ለመራቅ እንዲገደድ አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከጉዳቱ ለማገገም በማድረግ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥረት ስኬታማ ሆኖለት በሲዝኑ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሜዳ ለመመለስ ይችላል በሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በጥሩ ጤንነት ላይ በሚገኝበት ወቅት ከማንቸስተር ዩናይትድ ባሻገር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር አለኝታ ሆኖ ለበርካታ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ የሰፋ በመሆኑም በክለቡ በጭራሽ ሊለቀቅ የማይችል ተጨዋች እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም፡፡

ካሜሮን በርዝዊክ ጃክሰን

በዘንድሮው ሲዝን ከሉዊ ቫንሃል ጥቂት ተደናቂ ተግባሮች ውስጥ የ18 ዓመቱ ወጣት የግራ ተመላላሽን ከማንቸስተር ዩናይትድ ወጣት ቡድን ወደ ዋናው ለማሳደግ የደረሱበት ቆራጥ ውሳኔያቸው በሮዝዊክ ከወዲሁ ለዋናው ቡድን በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ተደናቂ ብቃቱን በማሳየት ማንቸስተር ዩናይትድ ለዘለቄታው የአስተማማኝ ግራ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶች እጥረት እንደማይኖርበት ለማስመስከር የቻለ ሆኗል፡፡

ፊል ጆንስ

ከዚህ በፊት ማንቸስተር በሪዮ ፊርዲናንድና በኔማኒያ ቪዲች አማካይነት የነበረውን ጠንካራ የመሃል ተከላካይ ክፍል ጥምረትን ሁለቱ እንግሊዛዊያን ክሪስ ስሞሊንግና ፊል ጆንስ በአግባ ለመመለስ ይችላሉ የሚል እምነት በበርካታዎች ዘንድ ተፈጥሮ ዘልቋል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን ይህ እምነት በአግባቡ ተግባራዊ እንዳይሆን በፊል ጆንስ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጉዳት የበኩሉን ተፅዕኖን የፈጠረ ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን ጆንስ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል አጋማሽ የሚገኝ ተጨዋች በመሆኑ የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ ለተጨማሪ ዓመታት የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ክሪስ ስሞሊንግ

ከዚህ በፊት በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር ሳይቀር ብዙ ተለፍቶበት የተረጋጋ አቋምን ለመያዝ ሲቸገር ታይቷል፡፡ በሉዊ ቫንሃል ስር ግን የማንቸስተር ዩናይትድ የተዋጣለት የመሀል ተከላካይ ሚና ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር የቻለበት ተደናቂ ፐርፎርማስን መላበስ ችሏል፡፡ በተለይም የእስካሁኑ ሲዝን የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ምርጡ ተጨዋች ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድ ልዩ ትኩረት ስሞሊንግ ጎን ትክክለኛውን ጥምረትን ለመፍጠር የሚችል ተጨዋችን ለማግኘት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ዳሊን ብሊንድ

የዘንድሮው ሲዝን በአብዛኛው ግጥሚያ ለማንቸስተር ዩናይትድ የተሰለፈበት በተከላካይ መስመር ነው፡፡ ሉዊ ቫንሃ ሆላንዳዊው ኢንተርናሽናል ከአማካይ ክፍል ይልቅ በመሀል ተከላካይ ሚና እንዲጠቀሙበት በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት የሆናቸው በስኳዳቸው የሚገኙት በርካታ የተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን በጉት ሳቢያ ከሜዳ ለመራቅ መገደዳቸው ነው፡፡ ይህን የሚያሳየው የብሊንድ የተለያዩ የጨዋታ ሚናዎች የመሰለፍ ሁለገብ ብቃትን ማንቸስተር ዩናይትደ በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ሊያገኘው አጥብቆ የሚመኘው መሆኑን ነው፡፡

ማይክል ካሪክ

ካለፉት ዓመታት አንፃር የእንግሊዛዊው አማካይ የዘንድሮ ሲዝን አቋም ጥሩ የሚባል ባይሆንም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን የዕድሜው መግፋት ምንም አይነት ተፅዕኖን ሳይፈጥርበት በቦታው ላይ የወትሮውን ጥሩ አቋሙን የሚያስታውሰው ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ነው፡፡ ይህ እውነታ ከግንዛቤ ሲገባም ማንቸስተር ዩናይትድ የተጨማሪ 12 ወራት የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ሊፈቅዱለት ማቀዱ ማስታወቁ አስገራሚ ሊሆን አይችልም፡፡

ሞርጋን ሽኔደርሊን

ፈረንሳዊው አማካይ በቀድሞ ክለቡ ሳውዝአምፕተን የነበረው ታላቅ ፐርፎርማንስን በእስካሁኑ ሲዝን ለመድገም ችሏል ባይባልም በመሀል አማካይ ክፍል ትክክለኛው አማራጭ ተጨዋች የሚያገኝ ከሆነ ግን በቦታው ላይ የማንቸስተር ዩናይትድ አስተማማኝ አለኝታ ሆኖ እንደሚዘልቅ ይታመናል፡፡

ሸኔደርሰሊን ከሲዝኑ መጋመስ ወዲህ የያዘው ጥሩ አቋም መሆን ቀስ በቀስ የማንቸስተር ዩናይትድ የመሀል አማካይን በበላይነት ለመምራት የሚያስችለውን አስተማማኝ ብቃት እንደሚኖረው የሚጠቁም ሆኗል፡፡

አንደር ሄሬራ

በሉዊ ቫንሃል ስር ብዛት ያላቸው ግጥሚያዎች ተከታታይነት ባለው መልኩ የመሰለፍ ዕድል ባይሰጠውም አልፎ አልፎ በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ግን ውጤታማ ፉትቦልን ሲያበረክት መታየቱ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ስፔናዊው አማካይ የኦልድትራፎርድ ስራ በትክክለኛው ባለሙያ የሚያዝ ከሆነ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

አሽሊ ያንግ

በሉዊ ቫንሃል ስር ከዚህ በፊት የነበራቸው ብቃትን አሳድገው ከተገኙት የማንቸስተር ዩናይትድ ስኳድ አባላት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በተለይም ሆላንዳዊው አሰልጣኝ አሽ ያንግ በተፈጥሮ ከያዘው በማጥቃት ላይ ያተኮረ የክንፍ ሚናው ባሻገር ወደኋላ ተመልሶ የመከላከል ተግባርን የሚፈፅምበትን አዲስ የጨዋታ ሚናን አስገኝተውለት ሁለገብ ብቃቱን አሳድገውለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ያንግ ለተጨማሪ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ሜምፌስ ዴፖይ

ባለፈው ሲዝን ፒኤስቪ አይንደንሆቨንን ለሆላንድ ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር እንዲበቃ ያበረከተው ቁልፍ አስተዋፅኦን በእስካሁኑ ሲዝን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለመድገም አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ዴፖይ ውጤታማ ፉትቦሉን በሜዳ ላይ ለማውጣት እንዲችል በሚረዳውን ትክክለኛ አሰልጣኝን ለማግኘት ከቻለ የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ ለመዝለቅ የሚችልባቸውን ሁሉንም አይነት ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡

ክለቡን መልቀቅ ያለባቸው

 ማርኮስ ሮሆ

የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ጥሩ የኳስ ስኬል ችሎታን ስኬታማ ታክሎችን የመግባት ብቃት ያለው ቢሆንም በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ ግን ከትኩረት ማነስ ችግር በመነጨ ስህቶችን ሲፈፅም መታየቱ የተለመደ ባህሉ ነው፡፡ አልፎ አልፎም አስፈላጊው ፋውሎችን በመፈፀም ቡድኑን የሚጎዳበት ባህል ያለው መሆኑ ከግንዛቤ ሲገባም በክለቡ ውስጥ የሚገባው ተጨዋች ነው፡፡

ባስቲያን ሽዌንስቲገር

ሉዊ ቫንሃል ጀርመናዊው ልምድ ያካበተ የመሃል አማካይን ለመግዛት የወሰነበት ተግባራቸው መጥፎ ሃሳብ ተደርጎ ሊቆጠር የሚገባው ቢሆን በእንግሊዝ ፉትቦል መሳተፍ የጀመረው ግን ዕድሜው 31 ከደረሰ በኋላ በመሆኑ ማንቸስተር ዩናይትድ በትክክለኛው ወቅት ላይ አላገኘውም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ሽዌንስቲቨር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ወደ ሜጀር ሊግ ስኮር ውድድር ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማሮዋን ፊላኒ

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽልን ያስፈረሙት ሁለገብ የአማካይ ክፍልና የአጥቂ መስመር ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባታቸው ቢሆንም የያዘው ብቃት ግን የማንቸስተር ዩናይትድ ትልቅ ስታንዳርድን በበቂ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አልተገኘም፡፡ ከዚህ አንፃር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሚጠበቀው እጣ ፈንታ በማንቸስተር ዩናይትድ ለሽያጭ መቅረብ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

አንቶኒዮ ቫሌንስያ

በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር የነበረው ውጤታማ ብቃቱን ቀስ በቀስ በማጣት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ኮርሶችን በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎች ላይ በመደረብ ራሱን የቻለ መጥፎ ሪከርድን ይዞ ዘልቋል፡፡ ከዚህ አንፃር ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚኖረው የፉትቦል ህይወት ወደማክተሙ ደረጃ ተቃሯል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

አድናይ ያንዩዣይ

በመላው አውሮፓ ተደናቂ ብቃትን የተላበሰው በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙት ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑ ቢታመንበትም የሉዊ ቫንሃል እቅድ አካል ለመሆን ተስኖታል፡፡ እስከ ዘንድሮው ሲዝን መጋመስ ድረስ በቦሪሽያ ዶርትሙንድ ያደረገው የውሰት ውል ቆይታውም ተደናቂ ስኬት ሊታጀብለት አልቻለም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ያንዩዣይን በጥሩ ዋጋ ለሌላ ክለብ የመሸጥ ውሳኔ ላይ መድረስ ነው፡፡ ያንዩዣይ በቅርበት የሚያውቁት አስተያየት ሰጪዎች ተጨዋቹ በዘንድሮ ሲዝን መጀመሪያ ላይ ከሉዊ ቫንሃል እቅድ ውጪ መሆኑ ተነግሮት በማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ከተለቀቀ ወዲህ በትክክለኛው የስነ ልቦና ጥንካሬ ደረጃ ላይ ለመገኘት ተስኖታል፡፡

Sport: በቼልሲ አዲሱ አሰልጣኝ ዘመን የትኛዎቹ ተጨዋቾች በክለቡ ይቆያሉ? የትኞቹስ ይለቃሉ?

$
0
0

ከደይሊ ሚረር ጋዜጣ ተተርጉሞ የቀረበ

ቼልሲ በዩሮ 2016 ውድድር መጠናቀቅ በኋላ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ላይ ያለው አንቶኒዮ ኮንቴን ለመቅጠር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ የቼልሲው ባለቤት ሮማን ኢብራሂሞቪች ለመቅጠር የወሰኑት ክለባቸውን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ለመመለስ እንደሚችል በማመን ነው፡፡

የ46 ዓመቱ የቀድሞው የጁቬንቱስ አሰልጣኝ ቼልሲን በመምራት 5ኛው ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት ጁያንሉካ ቪያላ፣ ክላውድዮ ራኒየሪ፣ ካርሎ አንቼሎቲ እና ሮቤርቶ ዲማቲዎ ሌሎቹ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በዋና አሰልጣንነት የመሩ ጣሊያናዊውን ባለሙያ ናቸው፡፡ ኮንቴ የዘንድሮው ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ የቼልሲ ስራን በሚጀምርበት ወቅት በምዕራብ ለንደኑ ክለብ እነማን ይዘልቃሉ ማንስ ክለቡን ይለቃል የሚለው ጉዳይ ከዚህ በታች ባለው መልኩ ተዳስሷል፡፡
Chelsea v Watford - Premier League
ግብ ጠባቂዎች
ከክለቡ ጋር የሚዘልቁ
ቲቧ ኩርቷ
ቤልጅየማዊው ግብ ጠባቂ ከወዲሁ የሪያል ማድሪድ ልዩ ትኩረትን ስቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ካለው እውነታ ለመረዳት የሚቻለውም በክለቡ እንደሚቆይ ነው፡፡
አስሜር ቤጎቪች

የቼልሲ ሌሎቹ ግብ ጠባቂዎች በጉት ከሜዳ በሚርቁበት ወቅት በበቂ ግጥሚያዎች የመሰለፍ ዕድልን በማግኘት ዘልቋል፡፡ ከዚህ አንፃር በኮንቴ ስርም የኩርቷ ተጠባባቂ ሆኖ በስኳዱ የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ ነው፡፡
ተከላካዮች
የሚቆይ
ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች
ሰርቪያዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች ባለፈው ጃንዋሪ ወር የአንድ ተጨማሪ ዓመት የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ተፈቅዶለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ኢቫኖቪች የቼልሲን የሚለቅበት ምንም አይነት ተስፋ አይኖረውም፡፡

ሴዛን አዝፕሌኩዌታ
ቼልሲ ኮንቴን በይፋ መሾሙን ከማረጋገጡ በፊት ኢዝፕሌኩዌታ ለቡድናቸው የወደፊቱ ትክክለኛው አሰልጣኝ ጣልያናዊው እንደሚሆን በይፋ ሲናገር ተደምጧል፡፡ ያንን መግለጫን የሰጠው የጣሊያንና በስፔን ብሔራዊ ቡድኖች በማርች ወር ካደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ ነበር፡፡ ያ መግለጫው ብቻ የኮንቴ እቅድ አካል እንደሚሆን የሚጠቁም ነው፡፡
የሚለቁ
ጆን ቴሪና ባባ ራህማን

የቴሪ በቼልሲ የኮንትራት ማራዘሚያ ሳይፈቅዱለት በመቅረታቸው ከወዲሁ ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ክለቡን በነፃ ዝውውር እንደሚለቅ ያረጋገጠበትን መግለጫን ሰጥቷል፡፡ የ21 ዓመቱ ራህማን በበኩሉ ለቼልሲ የተሰለፈበት የመጀመሪያ ሲዝኑን በማገባደድ ላይ ያለው ቡድኑን በከፍተኛ ደረጃ ለመጥቀም ተስኖት በመሆኑ በኮንቴ ስር ቦታ እንደማይኖረው ለመገመት አላስቸገረም፡፡

አማካዮች
የሚቆዩ
ሴስክ ፋብሪጋስ
በበርካታ ውጣ ውረዶች የታጀበ ሲዝንን ቢያሳልፍም አንቶኒዮ ኮንቴ ግን የቀጣዩ ሲዝን የቡድኑ ቁልፍ አካል ሊያደርጋቸው ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በተለይም ፋብሪጋስ በቅርቡ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ በኮንቴ ከተመራው የጣሊያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ ያሳየው ውጤታማ ፉትቦል በኮንቴ እንደታመነበት ምክንያት የሚሆነው ነው፡፡

ዊሊያን

ብራዚላዊው አማካይ በዘንድሮው ሲዝን ከሌላ ማንኛውም በቼልሲ ስኳድ ከሚገኝ ተጨዋቾች የተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት መቻሉ ከግንዛቤ ሊገባ አንቶኒዮ ኮንቴ በግንባር ቀደምነት የቡድኑ ቁልፍ አካል እንደሚያደርጉት ለመገመት አያስቸግርም፡፡

በርናንድ ትራኦሬ
የ20 ዓመቱ ወጣት በቼልሲና በጊዜያዊው ዋና አሰልጣኝ ጉስ ሂድንክ ስር በስምንት ግጥሚያዎች ላይ የመሰለፍ ዕድልን አግኝቶ ያለውን ተደናቂ ብቃት ማሳየቱ የኮንቴ እቅድ አካል እንዲሆን እንደሚረዳው ይታመናል፡፡ በስምንት ግጥሚያዎች ሁለት ጎሎችንም ለማስቆጠር ችሏል፡፡

ኬኔዲ
ሌላው የ20 ዓመት ወጣት ከቼልሲ የፉትቦል አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ከወዲሁ ለመሸጋገር ችሏል፡፡ የመሰለፍ ዕድልን ባገኘባቸው ጥቂት ግጥሚያዎች ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን ለማበርከት ሲችል በመታየቱም የአንቶኒዮ ኮንቴ ቁልፍ አካል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

እንደሚለቁ
የሚጠበቁ አጥቂዎች
ዲያጎ ኮስታ
ስፔናዊው ኢንተርናሽናል በእስካሁኑ ሲዝን በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር ኃላፊዎችና በፕሪሚየር ሊጉ ዳኞ የተደረገለት አያያዝ ደስተኛ እንዳላደረገው መናገሩ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አንቶኒዮ ኮንቴ ጥረቱ ስኬታማ ካልሆነ በስተቀር የኮስታና የቼልሲ የዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የመለያየት ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ሌይክ ሬሚ
ፈረንሳዊው አጥቂ በጃንዋሪው የዝውውር መስኮት ለቀድሞ ክለቡ ኒውካስል ዩናይትድ በውሰት ውል ለመፈረም ተቃርቦ ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ሃሳቡን በመቀየር ከቼልሲ ጋር መቆየትን ምርጫው አድርጓል፡፡ ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ግን በስታምፎርድ ብሪጅ የመቆየት ምንም አይነት ተስፋ አይኖረውም፡፡

አሌክሳንደር ፓቶ
ብራዚላዊው አጥቂ ኮሬንቲያስን በመልቀቅ ለቼልሲ ከፈረመ ወዲህ ለአዲሱ ክለቡ ለመለሰፍ የሁለት ወራተ ጊዜ ወስዶበታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቼልሲ በተሰፈለበት ግጥሚያ በአስቶንቪላ ላይ ጎልን ለማስቆጠር ቢችልም የአሁኑ የውሰት ውሉ ሲጠናቀቅ ግን ከቼልሲ ጋር መዝለቁ እጅግ አጠራጣሪ ነው፡፡

ራዳሚል ፉልካኦ
በአሁኑ ወቅት ከቼልሲ ጋር ያለው ኮንትራት በሲዝኑ መጨረሻ ላይ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ሌላ የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ማግኘቱ አጠራጣሪ ነው፡፡

Sport: ‹‹በየጊዜው ራሴን ማሻሻል እፈልጋለሁኝ›› –ሜሱት ኦዚል

$
0
0

ozil

ሜሱት ኦዚል ከአርሰናል ጋር ማሳካት የሚፈልጋቸው ህልሞች እንዳሉ ይፋ አድርጓል፤ በቅርብ ጊዜ አርሰናልን መልቀቅ እንደማይፈልግ ያሳወቀው ኢዞል ዋንጫዎችን የማንሳት ህልም እንዳለው አረጋግጧል፡፡

በ2013 ሪያል ማድሪድን ለቅቆ ወደ አርሰናል ሲመጣ የወጣበት 42.5 ሚሊዮን ፓውንድ ትኩረትን የሳበው ኦዚል ዘንድሮ 18 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሎ ምርጥ እይታ ያለው ተጨዋች እንደሆነ አረጋግጧል፤ የ27 ዓመቱ ጀርመናዊ የኮንትራት ስምምነቱ በ2018 የሚጠበቅ መሆኑ ብዙዎች ከክለቡ ጋር እንደሚለያይ ሲያስቡ ቆይተዋል፡፡ ኦዚል ግን ይሄንን እያስተባበለ ነው፡፡

‹‹ይሄ የውድድር ዓመት ከተጠናቀቀ በኋላ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በአርሰናል የሚያቆይ የኮንትራት ስምምነት አለኝ›› ይላል- ኦዚል፤ ጨምሮም ‹‹ከዚህ ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት በአርሰናል ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፡፡ ከክለቡ ጋር መቆየት እፈልጋለሁኝ፤ የቡድን ጓደኞቼ ጥሩ ናቸው- ከተማዋም ተስማምታኛለች፤ ያም ቢሆን በእግርኳስ እርግጠኛ መሆን በጣም ከባድ ነው፤ አሁን ባለው ሁኔታ በአርሰናል ፍፁም ደስተኛ ነኝ፡፡

‹‹የሁልጊዜም አላማዬ ግልፅ ነው- በዓለማችን ለሚገኙ ትልልቅ ክለቦች መጫወት እፈልጋለሁኝ፤ በቻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ እንዲሁም ዋንጫዎችን የማንሳት ፍላጎት አለኝ፤ ይሄንን ህልም እውን ለማድረግ ግን ሰፊ የተጨዋቾች ስብስብ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ወሳኝ ሊባሉ የሚችሉ ተጨዋቾች ዓመቱን ሙሉ ጤነኛ ሆነው አይጫወቱም፣ ጉዳት እንደሚያስተናግዱ ግልፅ ነው፡፡›› ሲል ተናግሯል፡፡

ozi;

በጀርመን ጋዜጦች ላይ አርሰናል ወደፊትም ቢሆን የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ያለው ዕድል ዝቅተኛ እንደሆነ  መግለፁ ኢዚልን አላስደሰተውም፡፡ቢሆንም ተጨዋቹ በጋዜጦች ላይ የተነገረውን መረጃ አስተባብሎ በክረምቱ አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም የፕሪሚየር ሊግ እና ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ አሸናፊ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

‹‹ብዙ ነገሮች በትክክለኛው መንገድ ሊተገበሩ እንደሚገባ የተናገርኩት ለዚህ ነው፤ ቡድኑን ማገዝ እሻለሁኝ፣ አላማችን አርሰናል የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ማስቻል ነው፣ በግሌ ቡድኑ ህልሙን እውን እንዲያደርግ የምችለውን አስተዋፅኦ ማበርከት እፈልጋለሁኝ፣ እዚህ ህልምህን እውን ማድረግ ትችላለህ፡፡ ተጨማሪ ጥቂት ጥሩ አቅም ያላቸውን ተጨዋቾች ማስፈረም ከቻልን ህልማችን እውን ይሆናል›› ብሏል ኦዚል፡፡

ኦዚል ግላዊ ብቃቱን የማሻሻል ፍላጎት እንዳለውም አረጋግጧል፡፡ ዘንድሮ ሰባት ጎሎችን አስቆጥሮ 18 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ሰጥቶ ዓለምን ያስገረመው የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ኮከብ፣ ‹‹አውቃለሁኝ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክለቦች ጥሩ የምሆንባቸው የውድድር ዓመታት ጥቂት የሚባሉ ናቸው፤ በአርሰናል ዘንድሮ ጥሩ ጊዜ እያሳለፍኩኝ እንደሆነ ይሰማኛል፣ ነገር ግን በግላዊ ስኬቴ የመኩራራት ስሜት አይሰማኝም›› የሚል አስተያየትን ሰጥቶ፣ ‹‹በየጊዜው ራሴን ማሻሻል እፈልጋለሁኝ፤ ከዚህ የተሻለ ነገር ማድረግ እና ቡድኑን መጥቀም እንዳለብኝ ይሰማኛል፤ በመጪዎቹ ዓመታት ይሄንን ህልሜን እውን ማድረግ እሻለሁኝ፣ ያም ቢሆን ጥሩ የውድድር ዘመን ማሳለፌ መረሳት የለበትም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን መጪውን ዘመን አሻግሬ መመልከትን እመርጣለሁኝ፣ ዘንድሮ ደግሞ ጥሩ አቋም ሳሳይ ቆይቻለሁኝ›› በማለት ብቃቱ ጥሩ ቢሆንም እንደማይኩራራ አረጋግጧል፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን 3ኛ ወጣ |አትሌት ትዕግስት ቱፋ 2ኛ ወጣች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በተደረገው የለንደን ማራቶን የኬንያ አትሌቶች በወንዶችም ሆነ በሴቶች አሸናፊ ሆኑ:: ኢትዮጵያውያኑ ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች 3ኛ ሲወጣ በሴቶች አትሌት ትዕግስት ቱፋ 2ኛ ወጥታለች::

ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ፈይሴ ታደሰ በውድድሩ ላይ እንዲህ ወድቀው ነበር:: (ፎቶ ከሬውተርስ)

ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ፈይሴ ታደሰ በውድድሩ ላይ እንዲህ ወድቀው ነበር:: (ፎቶ ከሬውተርስ)

የዘንድሮውን የለንደን ማራቶን ያሸነፈው ኬናዊው ኢሉድ ኪፖቾጌ ሲሆን ውድድሩን 02:03:05 ጨርሷል:: 2ኛ የወጣው ሌላኛው ኬንያዊ አትሌትም ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀበት ሰዓት 02:03:51 ሆኗል::

ለሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ድሎችን በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሲያስገኝ የነበረውና አሁን ፊቱን ወደ ማራቶን እያዞረ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ይህን የለንደን ማራቶን በ02:06:36 በመግባት 3ኛ መውጣቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል:: ኤርትራዊው ግርማይ ገብረሥላሴ በ02:07:46 4ኛ ሲወጣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጥላሁን ረጋሳ በ02:09:47 በመግባት 6ኛ ወጥቷል:: እንዲሁም በ 02:10:45 በመግባት አትሌት ሲሳይ ለማ 7ኛ; ኤርትራዊው አትሌት ገብሬ ክብሮም በ 02:11:56 በመግባት 10ኛ ወጥቷል::

ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያዊያኑ አትሌቶች ጋር (ፎቶ ሬውተርስ)

ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያዊያኑ አትሌቶች ጋር (ፎቶ ሬውተርስ)

በሴቶች ማራቶን ኬንያዊቷ አትሌት ጀሚያ ሱምጎንግ በ 02:22:58 በመግባት አንደኛ ስትወጣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ት ዕግስት ቱፋ በ02:23:03 በመግባት 2ኛ ወጥታለች:: 3ኛ የወጣችውም ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት ስትሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሰለፈሽ መርጊያ በ02:23:57 በመግባት 5ኛ; ማሬ ዲባባ በ 02:24:09 በመግባት 6ኛ; ፈይሴ ታደሰ በ02:25:03 በመግባት 7ኛ ወጥተዋል::


Sport: ‹‹ህልሜን እውን አላደረኩም!›› ጆሴ ኤሊስ ሊንጋርድ

$
0
0

 

በማንችስተር ዩናይትድ ዘንድ ክስተት ከሆኑ ተጨዋቾች መሃከል አንዱ ነው፣ ጆሴ ሊንጋርድ፡፡ አሰልጣኝ ሉዊስ ቫን ሃል ዘንድሮ በዋናው ቡድን በቂ የመሰለፍ ዕድል ከሰጧቸው ተጨዋቾች መሃከል የሆነው ሊንጋርድ ለአሰልጣኙ እምነት ምላሽ ሰጥቶ አስደስተዋቸዋል፣ ቫን ሃል እንግሊዛዊውን ወጣት ኮከብ በተለያዩ ቦታዎች አጫውተው እየጠቀሙበት ይገኛሉ፣ የግራ እና ቀኝ መስር አማካይ ሆኖ መጫወት ይችላል፡፡ 23 ዓመቱ እንግሊዛዊ 10 ቁጥር ቦታ ላይ እንዲጫወት ዕድሉ ሲሰጠው አጋጣሚውን የመጠቀም ችግር የለበትም፡፡

Lingard 2

ባለፈው ዓመት በውሰት ለደርቢ ካውንቲ ተሰጥቶ ብቃቱን ወደላቀ ምዕራፍ ያሸጋገረው ሊንጋርድ ከአጥቂ ጀርባ ሆኖ መጫወት እንዳስደሰተው ገልጿል፡፡ ቦታው ላይ በርካታ በርካታ ተጨዋቾች ይገኛሉ፡፡

ሜምፊስ ዴፓይ በግራ መስመር በኩል ቢጫወትም እዚህ ቦታ ላይ የመጫወት ችግር የለበትም፡፡ ሁዋን ማታ ለዚያ ቦታ የተሰራ ይመስላል፣ ጉዳት ላይ የሚገኘው ዌይን ሩኒ ከዕድሜው መግፋት ጋር ተያይዞ እዚህ ቦታ ላይ ሲጫወት ይበልጥ አቅሙን አውጥቶ ይጠቀማል፣ ሄሬራ ደግሞ በተደራቢ አጥቂነት ሲሰለፍ ጎሎችን ማስቆጠር ይችላል፡፡

ዘንድሮ በሁሉም ውድድሮች 31 ጨዋታዎችን ፈፅሞ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ስኬታማ የውድድር ዘመን እያሳለፈ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡፣ ከምንም በላይ በማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ያሳየው አቋም የሁሉንም ትኩረት ስቧል፣ ተጨዋቹን የደርቢ ጨዋታው በዘንድሮ የውድድር ዓመት ምርጥ ብቃትህን ያሳየህበት ነው የሚል ጥያቄ ስታነሱበት ‹‹አዎን፣ አሰልጣኙም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በውድድር ዓመቱ ካሳየሁት ብቃት ምርጡ እንደሆነ ነግሮኛል፣ በግልም ይሄ ስሜት ተሰምቶኛል›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

‹‹እርግጥ ነው የማሸነፊያን ጎል ያስቆጠረው ማርክስ (ራሽፎርድ) ነው፤ ከአካዳሚው የተገኘ ሌላ ተጨዋች በመሆኑ መጪው ዘመን ለማንቸስተር ዩናይትድ ብሩህ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡ በእርሱ ጎል ወሳኙን ጨዋታ በድል መወጣት አስደሳች ስኬትን ይፈጥራል›› የሚል መረጃን የሚሰጠው ሊንጋርድ መጫወት ስለሚችልበት ቦታ ስትጠይቁት ‹‹ሁልጊዜም ቢሆን 10 ቁጥር ቦታ ላይ መጫወት ያስደስተኛል፣ እዚያ ቦታ ላይ ስትጫወት በርካታ ኳሶች ይደርሱሃል፣ የጨዋታውን እንቅስቃሴ መምራት ትችላለህ፡፡ በእርግጥ የግራ ወይም የቀኝ መስመር አማካይ ሆኜ የመጫወት ችግር የለብኝም፡፡ በአጠቃላይ አሰልጣኙ በጠየቀኝ ቦታ ላይ ለመጫወት ዝግጁ ነኝ፡፡ ነበዚህ ወቅት ይሄ ቦታ ነፃ ሚና ያለው ነው፤ እዚህ ቦታ ላይ የሚጫወት ተጨዋች በነፃነት የመጫወት ችግር የለበትም፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ሆኖ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር ይችላል፤ ጎሎች ያስቆጥራል፣ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን መስጠት ይችላል፡፡ ጎሎችን ያስቆጥራል፤ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ያቀብላል፣ ነገር ግን የዚያኑ ያህል በጥለቀት ወደ ኋላ ተመልሶ የመከላከሉን ኃላፊነት በአግባቡ የመወጣት ግዴት አለበት›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

ለእንግሊዝ 21 ዓመት በታች የተጫወተው ሊንጋርድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ለከርሞ በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እቅድ ይዟል፡፡ እነሆ ከስካይ ስፖርት ጋር ያደረገው ቃለምልልስ፡-

ጥያቄ፡በውድድር ዘመኑ ከተደረጉ ጨዋታዎች የደርቢው ጨዋታ ምርጡ ነው ማለት ይቻላል?

ሊንጋርድ፡- ትክክል ነው፣ በመጀመሪያ ደረጃ መሳተፍ ከምፈልግባቸው ጨዋታዎች መሀከል የማንችስተር ደርቢ ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኙ በውድድር ዓመቱ ካደረግኳቸው ጨዋታዎች ይሄ ቀዳሚው እንደሆነ ነግሮኛል፤ በዚያ ጨዋታ ላይ በተደራቢ አጥቂ ቦታ ላይ (10 ቁጥር) መጫወቴ አስደስቶኛል፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ስጫወት የምቾት ስሜት ይሰማኛል፣ እዚያ ቦታ ላይ በርካታ ኳሶችን ታገኛለህ፤ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን የማቀበል ችግር አይገጥምህም፡፡ የፈለግከውን ነገር ለመስራት የሚያስችል ዕድል ይፈጥርልሃል፣ ጎሉን ያስቆጠረው (ማርኮስ) ራሽፎርድ መሆኑ የተለየ ስሜት ፈጥሮብናል፣ ምክንያቱም የተገኘው ክለቡ ከሚገኝበት አካባቢ እና አካዳሚ ውስጥ ነው፡፡

ጥያቄ፡አሰልጣኝ ስዊስ ቫን ሃልም ተደራቢ አጥቂ ቦታ የአንተ ምርጡ እንደሆነ ጠቅሰው ነበር፡፡ እዚህ ቦታ የአንተ ምርጡ እንደሆነ ጠቅመው ነበር፤ እዚያ ቦታ ላይ መጫወት ያስደስትሃል?

ሊንጋርድ፡- በግሌ 10 ቁጥር ቦታ ላይ መጫወት ያስደስተኛል፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ስትጫወት በርካታ ኳሶችን ያገኛለህ፣ የጨዋታውን አቅጣጫ ለመመራት ያስችልሃል፣ እርግጥ ነው በቀኝ መስመር አማካይ ሆኜ መጫወት ያስደስተኛል፡፡ በግራ መስመር በኩልም እንዲሁ፡፡ ሆኖም አሰልጣኙ በየትኛውም ቦታ ላይ እንድጫወት ዕድሉን ከሰጠኝ አጋጣሚውን ለመጠቀም ዝግጁ ነኝ፡፡

ጥያቄ፡10 ቁጥር ሚና የተለወጠ ይመስልሃል? በፊት እዚህ ቦታ ላይ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ማጥቃቱ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ እና በቴክኒክ ረገድ የተዋጣላቸው ነበሩ፤ ሆኖም አሁን ሚናው ተለውጧል ማለት ይቻላል?

ሊንጋርድ፡- በአሁኑ ሰዓት እዚህ ቦታ ላይ መጫወት ነፃነት የሚሰጥ ሆኗል፤ እዚያ ቦታ ላይ ስትጫወት ሜዳውን አካልለህ በመጫወት ምንም ነገር እንዲፈጠር ታደርጋለህ፤ ቡድኑን የሚጠቅም አዳዲስ ነገሮች ትፈጥራለህ፤ ወሳኙ ነገር እንዳለ ሆኖ ወደ ኋላ ተመልሰህ መከላከል ግድ ይልሃል፡፡

ጥያቄ፡ኢትሃድ ላይ ማንቸስተር ሲቲን ባሸነፋችሁበት ጨዋታ ጨዋታው የሚወድቀውን አካላዊ ፈተና በብቃት ተወጥተሃል፣ ይህ ተክለ ሰውነትህ አካላዊ ፈተናዎች ጋር ተፃራሪ ነው?

lingard

ሊንጋርድ፡- በፕሪሚየር ሊጉ ግዙፍ ከሚባሉ ተጨዋቾች መሀካል ቀዳሚውን ቦታ ከሚወስደው ያያ ቱሬ ጋር መፋለም ቀላል አይደለም፡፡ ፈርናንዱንሆንም በዚህ ተርታ የሚካተት ተጨዋች ነው፡፡ ስለዚህ ፈተናው ቀላል አይሆንም፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆነ ሌሎች የቡድናችን ወጣት ተጨዋቾችም ለገጠማቸው ፈተና ራሳቸው ዝግጁ አድርገው በአግባቡ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ አማካዩ ክፍል ላይ የማይክል (ካሪክ) ሚና የላቀ ነበር፡፡ ልምዱን ተጠቅሞ ሊመራን ነበር፡፡ ጨዋታውን ተቆጣጥሮ ያጠናቀቀበት መንገድ በጣም ይገርማል፡፡ ወሳኔ ነገር የምትጫወትበት መንገድ ነው፡፡ በሊጉ ማንቸስተር ሲቲን ጨምሮ በአማካይ ክፍሉ ላይ በርካታ ግዙፍ ተጨዋቾች አሉ፡፡ በደርቢው ጨዋታ ራሴን በአካልም ሆነ አዕምሮ ዝግጁ ማድረግ ነበረብኝ፡፡

ጥያቄ፡ሪዮ ፈርንዲናንድ በቅርቡ ‹‹ጄሴ ሲንጋርድ አስደናቂ ተጫዋች ነው፡፡ በእርሱ ዕድሜ የሚገኙ ተጨዋቾች የሚያደርጉትን ከኳስ ውጭ ድንቅ እንቅስቃሴ ያከናውናል›› ብሎ ነበር፡፡ ይሄንን አስተያየት ሰምተሃል?

ሊንጋርድ፡- አዎን፤ በተለይ በ10 ቁጥር ቦታ ላይ ስትጫወት የዚህ አይነት ብልሃት ሊኖርህ ይገባል፡፡ ያለቀለት ኳስ ለማቀበል በዙሪያ ያሉትን ነገሮች የመቆጣጠር ብቃትህ እና እይታህ ወሳኝነት አለው፡፡

ሆኖም የሪዮ አስተያየት በራሱ የመተማመን ስሜትህን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ከእርሱ ጋር ያለማቋረጥ እንወያያለን፡፡ አሁንም ድረስ የእርሱን ምክር እየተገበርኩኝ እገኛለሁኝ፡፡ በየጊዜው ይከታተለኛል፤ በየጊዜው እንወያያለን፤ እርሱም ቢሆን ይከታተለኛል፡፡

ጥያቄ፡በደርቢው ጨዋታ የቀድሞው የሊቨርፑል ተጨዋች ዳኒ መርሬ የጨዋታው ኮከብ እንደነበርክ ጠቅሷል?

ሊንጋርድ፡- የዚህ አይነት አስተያየቶች ጠንክረህ እንድትሰራ እና ለድል ያለህን የረሃብ ስሜት ከፍ ያደርገዋል፡፡ በቀጣይ ያለ ማቋረጥ እና መዘናጋት ጠንክሬ መስራቱ ይቀጥላል፡፡ ይህ ዓመት የመጀመሪያዬ በመሆኑ ገና ያላሳካኋቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ በቀጣይ ጠንክሬ መስራቴን እቀጥላለሁኝ፡፡

ጥያቄ፡በየጨዋታው ቋሚ ተሰላፊ መሆንህ በራስ የመተማመን ስሜትህን አጎልብቷል ማለት እንችላለህ?

ሊንጋርድ፡- በየጨዋታው ቋሚ ተሰላፊ መሆን በራሱ የመተማመን ስሜት እንደሚያጎለብተው ጥርጥር የለውም፤ ዘንድሮ በራስ የመተማመን ስሜቴን ያሳደገው ይኸው ያለማቋረጥ መጫወቴ ነው፤ ወሳኙ ነገር በሜዳ ውስጥ የምታሳየው ብቃት እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ተጨማሪ ጎሎችን ባስቆጥር ደስተኛ እሆናለሁኝ፡፡ በቀጣይ ይሄ ፍላጎቴ እውን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፤ በቀጣዩ ዓመት ይበልጥ ተጠናክሬ እና ውጤታማ ሆኜ እመለሳለሁኝ፡፡

ጥያቄ፡ከተደራራቢ እና ፈታኝ የጨዋታ ፕሮግራሞች በኋላ የዓለም አቀፍ (ብሔራዊ ቡድን) ጨዋታዎች መከናወናቸው እንደ በጎ የሚታይ ነገር ነው?

ሊንጋርድ፡- እርግጥ ነው ጥቂት እረፍትና ቀለል ያለ የእረፍት ጊዜ ማግኘት ያስደስታል፡፡ ልምምዱ ሲቀንስ የእረፍት ጊዜ ማግኘት ይቻላል፤ ከሪዘርቭ ቡድኑ የመጡ ተጨዋቾችም አብረውን ልምምድ ሲሰሩ ነበር፡፡ ጥቂት ቀናት እረፍት ማግኘታችን ፍም ያስደስታል፡፡ ባለፉት ዓመታት በፋሲካ በዓል ሰሞን ጨዋታዎች ነበሩ፡፡ አሁን ግን የእረፍት ጊዜ አለው፡፡

ጥያቄ፡ማንቸስተር ሲቲን ማሸነፍ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ ለመፈፀም ምን ያል አስተዋፅኦ አለው?

ሊንጋርድ፡- ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሲቲን ማሸነፍ ወሳኝ ነበር፡፡ ይህንንም በሚገባ አሳይተናል፡፡ የደርቢ ጨዋታዎች ሁልጊዜም ትኩረት ያገኛሉ፡፡ የአሸናፊውን ቡድን ሞራል የማነሳሳት አቅም አላቸው፡፡ ደጋፊዎቻችን ጨዋታውን በጉጉት ስሜት ሆነው ይጠብቃሉ፡፡ እኛ ደግሞ እነርሱን ለማስደሰት እንፋለማለን፤ ጨዋታውን በድል ስንወጣ ደግሞ ይበልጥ ሁሉም ነገር ያስደስታል፡፡ ጨዋታውን ብናሸንፍ ኖሮ ነገሮች ይበልጥ ፈታኝ ይሆኑ ነበር፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘን ለመፈፀም ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡ የቡድናችን ተጨዋቾች በየዓመቱ በቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ይህ ህልማችን እውን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁኝ፡፡ ማሳካትም እንችላለን፡፡

ጥያቄ፡የውድድር ዓመትን መለስ ብለህ ስትቃኘው ከጠበቅከው የበለጠ እንደሆነ ይሰማሃል?

ሊንጋርድ፡- አዎን ትክክል ነው፡፡ በኤፍኤ ካፕ ፍፃሜ ዌምብሌይ ላይ ብጫወት ደስ ይለኛል፡፡ ለፍፃሜ ከቀረብን ዋንጫውን ማንሳት እንችላለን፡፡ ከዚህ ውጭ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ መፈፀም ሌላው ዓላማችን ነው፡፡ በግሌ ትክክለኛ ነገሮችን ለመፈፀም እሻለሁኝ፡፡ ይህንን ለማሳካት ደግሞ በሜዳ ውስጥም ሆነ ከሜዳ ውጭ ጠንክሬ እየሰራሁኝ እገኛለሁኝ፡፡ ሉዊስ ቫን ሃል ይህንን በሚገባ አስተውሏል፡፡ እርግጥ ነው በወጣት ተጨዋቾች መጠቀም አደጋ ቢኖውም የተጣለብህ እምነት አስደሳች ነው፡፡ አሁን የምንገኘው በመጀመሪያው ዓመት ላይ ነው፣ በምፈልገው ደረጃ የተሳካ ነገር አለ ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ጠንክሬ መስራቴን እቀጥላለሁኝ፡፡

ጥያቄ፡ከንግግርህ በመነሳት በስኬትህ እንደማትኩራራ ግልፅ ነው፡፡ አሁን የምትፈልገውን ነገር በማሳካት ሂደት ውስጥ ነህ ማለት ይቻላል?

ሊንጋርድ፡- በጭራሽሽ በግሌ በምንም አይነት መልኩ መዘናጋት አልፈልግም፡፡ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በርካታ ጨዋታዎችን በሙሉ መፈፀም እፈልጋለሁኝ፤ በኤፍኤካፕ እስከ ፍፃሜ በመጓዝ በሊጉ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘን መፈፀም አለብን፡፡

የሌንጋርድ መረጃዎች

ስም፡- ጆሴ ኤሊስ ሊንጋርድ

የትውልድ ዘመን፡- ዲሴምበር 15/1992

ዕድሜ፡- 23

የትውልድ ቦታ፡- ዋሪንግተን/እንግሊዝ

ቁመት፡- 1.75 ሜትር

ቦታ፡- የአማካይ አጥቂ

ክለብ፡- ማንቸስተር ዩናይትድ

የማልያ ቁጥር፡- 35

የዩናይትድ የወጣት ቡድን ቆይታ፡- 2000-2011

የዋና ቡድን ቆይታ

2011…..ማንችስተር ዩናይትድ

2012/13….ሌይስተር ሲቲ (ውሰት)

2013/14… በርሚንግሃም ሲቲ (ውሰት)

2014… ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን (ውሰት)

2015… ደርቢ ካውንቲ (ውሰት)

ብሔራዊ ቡድን

2008…. እንግሊዝ ከ17 ዓመት በታች

2013-2015…. እንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተባረሩ

$
0
0

8b0067e1ba18cd789b122c804be56585_XL

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣነታቸው መባረራቸው ተሰማ:: በአንድ ወር የ75 ሺህ ብር ተከፋይ የነበሩት እኚሁ አሰልጣኝ ብሄራዊ ቡድኑን ከሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰለጥኑት ቆይተዋል::

የቀደሞው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የተረከቡትን ብሄራዊ ቡድን ውጤታማ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም በ እርሳቸው ዘመን ብሄራዊ ቡድኑ የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድንን ከማሸነፉ ውጭ ምንም አመርቂ ውጤት አላመጡም እየተባሉ በስፖርት ተንታኞች ዘንድ ሲተቹ ቆይተዋል::

75 000 ብር ወርሃዊ ደመወው; ተሽከርካሪ ከሾፌር ጋር እንዲሁም ባለመስመር የሞባይል ስልክና የጤና ኢንሹራንስ ከተለያዩ ጥቅማትቅሞች ጋር እየተከፈላቸው ብሐራዊ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ የነበሩት አቶ ዮሐንስ በተጨማሪ ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና የበረኞች አሰልጣኝ አሊ ረዲም አብረው መሰናበታቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለከታል::

Video: ኃይሌ ገብረስላሴ ጀነራል ጃጋማ ኬሎን ለዓመት በዓል ቤታቸው ሄዶ ጠየቀ |እናመሰግናለን ኃይሌ

$
0
0


Video: ኃይሌ ገብረስላሴ ጀነራል ጃጋማ ኬሎን ለዓመት በዓል ቤታቸው ሄዶ ጠየቀ | እናመሰግናለን ኃይሌ
Haile

አልማዝ አያና በኳታር ዶሃ 3 ሺህ ሜትር ሩጫ አሸነፈች –ገለቴ ቡርቃም ድል ቀናት

$
0
0

485908858

(ዘ-ሐበሻ) ከደቂዎች በፊት በዳይመንድ ሊግ ውድድር በኳታሯ ዶሃ ከተማ በተደረገው ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በ3ሺ ሜትር የሴቶች ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸነፈች::

አልማዝ ውድድሩን ለማሸነፍ የፈጀባት ጊዜ 8 ደቂቃ ከ23.1 ሰከንድ መሆኑ ታውቋል:: በዚሁ በዳይመንድ ሊግ ውድድር ኬንያዊቴ ሜርሲ ቸሮኖ 2ኛ ስትወጣ ውድድሩን በ8:26.36 ጨርሳለች:: በዚህ ውድድር 3ኛ የወጣችው ገለቴ ቡርቃ ስትሆን ውድድሩን በ8:28.49 ጨርሳለች::

ከ4ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ቦታ የያዙት ኬንያውያኑ አትሌቶች ሲሆኑ እቴንሽ ዲሮ ነዳ 7ኛ ሆናለች:;

እንኳን ደስ አለን::

13112578_10154090036594373_1798588878_o

ፌደሬሽኑ ለብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በወር 80 ሺህ ብር ለመክፈል ተስማማ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የብሔራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ባለፈው ሳምንት ያባረረውና በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን የቀጠረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ለሚዲያዎች “በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈረመ” ሲል በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአሰልጣኙ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ሳይጨምር በወር 80 ሺህ ብር ለመክፈል ተስማምቷል::

ጋዜጣዊ መግለጫው እንደወረደ እነሆ
Geberemedhin

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ከሥራ ማሰናበቱን ተከትሎ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በገብረመድን ኃይሌ መካከል የተፈረመው የሥራ ውል ከግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2009 ዓ.ም ለአምስት ወራት የሚቆይ ነው፡፡

በተጠቀሱት ወራት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በየወሩ ያልተጣራ ብር 80,000.00/ሰማኒያ ሺህ ብር/ ይከፍላል፡፡ የቴሌፎን ፣ የኃላፊነትና የነዳጅ ጥቅማ ጥቅሞችንም ይጠብቃል፡፡

አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌና በፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት አሰልጣኝ ገብረመድን እንደገለፀው ለብሔራዊ ቡድን በመጫወት ያገኘው ትልቅ ክብር ለእዚህ ከባድ ሃገራዊ ኃላፊነት ስምምነቱንና ፈቃደኝነቱን በመግለፅ ብሔራዊ ግዴታውን ለመወጣት ያስገደደው ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሲሼልስ የማጣሪያ ጨዋታ ጀምሮ ያስመዘገበውን ዝቅተኛ ውጤት ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ፈጣን ርምጃ አለመውሰዱ ክፍተት እንደፈጠረ በመቁጠር የተቀበለው ሲሆን በቀጣይነት ውስጣዊ የአሠራር ሥርዓት ማስተካከያ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በሂሳባዊ ስሌት የቡድናችን ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋው ሙሉ በሙሉ ያልተሟጠጠ በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በእግር ኳስ ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠውን ገብረመድን ኃይሌን በጊዜያዊ አሠልጣኝነት እንዲሾም አድርጓል፡፡ አሠልጣኝ ገብረመድን የተረከበውን ከባድ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣና ቡድናችን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የእግር ኳስ ቤተሰቦች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉም ፌዴሬሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

Viewing all 419 articles
Browse latest View live