አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ያለፉትን 4 ቀናት እንዴት አሳለፈ? – ልዩ ቃለምልልስ ያድምጡ
መረጃ ከሪዮ
ከመሳይ መኮንን | ኢሳት
ዛሬ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከብራዚል ባለስልጣናት ጋር ተወያይቷል። ከፍሎሪዳ ግዛትና ከዋሽንግተን ዲስ ወደ ሪዮ ያመሩት ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን አትሌት ፈይሳ ከብራዚል ባልስልጣናት ጋር ተመካክሯል። ብራዚሎች ቋምጠዋል። አትሌቱ እነሱ ጋ እንዲቀር በግልጽ ጠይቀዋል። ”የምትፈልገውን እናቀርባለን። በብራዚል የመኖር ፍቃድ እንሰጥሃለን። ሩጫውንም እዚሁ መቀጠል ትችላለህ” ማለታቸውን የምንጮች መረጃ ያመለክታል። አትሌት ፈይሳ ለብራዚል ባለስልጣናት ምስጋና አቅርቧል። ወደ ሌላ ሀገር የሚሻገርበት ሂደት ነገ ይጀመራል። በሌላ በኩል ታዋቂ አትሌቶች ቦይኮት ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቀው፡ አትሌት ሃይሌ ግብረስላሴና ገብረእግዚያብሄር ገ/ማርያምን ጨምሮ የተወሰኑ አትሌቶች የሚሳተፉበት ጋዜጣዊ መግለጪያ ሀሙስ በአዲስ አበባ ይሰጣል ተብሏል። ቦይኮት ያደረጉ አትሌቶች በስም አልታወቁም። ጋዜጣዊ መግለጪያው ስለ ሪዮ ኦሎምፒክ ተሳትፎ ሲሆን አትሌት ፈይሳን ለማውገዝ የታለመ እንደሆነም ከአዲስ አበባ የመጣው መረጃ ያመለክታል።