ፔፔ ጋርዲዮላ ከወዲሁ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾች በማግኘት ላይ ነው፡፡ በአሁኑ የዝውውር መስኮት 5ኛው የማንቸስተር ሲቲ አዲስ ፈራሚ ሆኖ ኢትሃድ ደረሰው ብራዚላዊው የክንፍ ተጨዋች ጋብርኤል ጆንስ የተገባበት 27 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ የክለቡ የዘንድሮው ፕራሲዝን ዝውውር መስኮት የተጨዋቾች ግዥ ዋጋ ወጪን 100 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያደረሰው ሆኗል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድም የጁቬንቱሱን አማካይ ፖል ፓግባን በሚጠበቀው መልኩ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሂሳብ የክለቡ የዘንድሮው ፕራሲዝን ዝውውር መስኮት የተጨዋቾች ግዥ ዋ ወጪን 100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያደረሰው ሆኗል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድም የጁቬንቱሱን አማካይ ፖል ፓግባን በሚጠበቀው መልኩ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሂሳብ በማውጣት ለማስፈረም ከቻለ የማንቸስተር ሲቲ አርአያነትን የሚከተል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በቅርብ ዓመታት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በአንድ የፕሪ ሲን ዝውውር መስኮት ከ100 ሚሊዮን በላይ ሂሳብ አውጥቶ ለሻምፒዮንነቱ ክብር ለመብቃት የቻለ ክለብ አልታየም፡፡
ለሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ደጋፊዎች ሌላው ትልቅ ፀፀት የሚሆነው የዛሬ ዓመት ሁለቱም ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለአዳዲስ ተጨዋቾች ግዢ እያንዳንዳቸው ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተው የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን በመቀዳጀት ያለፈው ሲዝንን ያጠናቀቀው ሌይስተር ሲቲ መሆኑ ነው፡፡
ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ግን በ4ኛ እና በ5ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጠው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡ ማንቸስተር ሲቲ ልክ የዛሬ ዓመት በቺሊያዊው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ስር ኬቪን ደብሩያንን እና ራሂም ስተርሊንግን የመሳሰሉ ተጨዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ፈራሚዎች እስከ 150 ሚሊየን ፓውንድ የሚደርስ ሂሳብ ማውጣቱ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን ለመቀዳጀት ያለውን አላማ ለማሳካት ሳይረዳው መቅረቱ ይታወቃል፡፡
የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ የነበሩት ሉዊ ቫንሃልም ከ150 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በማውጣት እስከ ስድስት የሚደርሱ ተጨዋቾችን ገዝተው ክለቡን የ2016/17 ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎን በሚያገኝበት ስፍራ ላይ በማስገባት ለማስጨረስ ባለመቻላቸው የኦልድ ትራፎርድ ስራን ለማጣት መገደዳቸው ይታወቃል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ያለፉት ሁለት ሲዝኖችን በፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለማጠናቀቅ የተሳነው በሁለት ተከታታይ የፕሪ ሲዝን የዝውውር መስኮቶች በእያንዳንዳቸው ላይ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዋጋ በማውጣት አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሞ እውነተኛ የሆነ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክርን ሲያደርግ አልታየም፡፡
ማንቸስተር ሲቲም በፕራሲዝን ዝውውር መስኮት ሪከርድ የሰበረ የተጨዋች ግዥን ሲያወጣ የዘንድሮው ለጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ በ2009 እና በ2010 ፕራሲዝኖች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ከፍተኛ የተጨዋች ግዥ ዋጋን አውጥቶ ሁለቱንም ሲዝኖች ያጠናቀቀው ግን የሻምፒዮንነቱ ክብር በሌሎች ክለቦች እጅ ሲገባ ለማየት ተገድዷል፡፡ ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ቼልሲም ከዚህ በፊት በአንድ የፕራሲዝን የዝውውር መስኮት እያንዳንዳቸው ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የተጨዋች ግዥሂሳብን አውጥተው ክለባቸውን ለፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለማብቃት ተስኗቸው ያጠናቀቋቸው ሲዝኖች አሏቸው፡፡
በተለይም ቼልሲ በጁላይ 2003 በራሽያዊው ቢለየነር ሮማን ኢብራሂሞቪች እጅ መግባቱን ተከትሎ የ2003/04 ሲዝንን የጀመረው ለአዳዲስ ተጨዋቾች ግዢ በአጠቃላይ 110 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ በማውጣት መላው ዓለምን በማስገረም ነበር፤ ሆኖም ግን ያንን የውድድር ዘመን ያጠናቀቀው አርሰናል ለሙሉ ሲዝን በአንድም የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ሳይሸነፍ ለሻምፒዮንነት ክብሩ ለመብቃት አስገራሚ ገድልን ሲፈፅም በማየት ነው፡፡
ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም ስፖርትስ ሜይል ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በፕሪሲዝን ዝውውር መስኮት ሪከርድን የሰበረ የተጨዋች ግዢ በጀትን ያወጡት ክለቦች በሲዝኑ ዘመቻቸው ያጋጠማቸው እጣ ፈንታን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዳስሶታል፡፡
ማንቸስተር ሲቲ (በ2015)
አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ በማንቸስተር ሲቲ ስራ ባሳለፉት የመጨረሻው ፕራ ሲዝናቸው ኪቪን ደብሩይን እና ራሂም ሰተርሊንግ ብቻ በድምሩ ከ100 ሚልየን ፓውንድ በማውጣት ገዝተዋቸዋል፡፡ በሁለቱ ተጨዋቾች የማንቸስተር ሲቲ የተጨዋቾች ግዢ ሪከርድን ከአንዴም ሁለቴ ለመስበር ተገድደዋል፡፡ ሆኖም ግን የ2015/16 ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ዘመቻቸውን የጨረሱት በኃላፊነት ዘመናቸው ዝቅተኛውን ስፍራ ማለትም 4ኛ ደረጃን በማግኘት በመሆኑ ከስራቸው ተነስተዋል፡፡
የሲቲ የ2015 ፕራሲዝን ፈራሚዎች
ከቪን ደብሩያን፡- 52 ሚሊየን ፓውንድ
ራም ሰርተርሊንግ፡- 40 ሚሊየን ፓውንድ
ኒኮላ ኦታሚንዲ፡- 32 ሚሊየን ፓውንድ
ፋቢያን ዴልፕ፡- 8 ሚሊየን ፓውንድ
ፓትሪክ ሮበርትስ፡- 48 ሚሊየን ፓውንድ
ዴኔስ ዩናል፡- 2 ሚሊየን ፓውንድ
በአጠቃላዩ ያወጣው፡- 151 ሚሊየን ፓውንድ
በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡- ሌይስተር ሲቲ
ማንቸስተር ዩናይትድ በ2014
ሉዊ ቫንሃል የሆላንድ ብሔራዊ ቡድንን በ2014 የዓለም ዋንጫ በአሰልጣንነት መርተው 3ኛ ደረጃን እንዲያገኝ ከረዱት በኋላ የማንቸስተር ዩናይትድ ስራን የያዙት ክለቡ ከፍተኛ የተጨዋች ግዢ በጀትን መድቦላቸው ነበር፡፡ በ2014 ፕሪ ሲዝንም በአጠቃላይ ስድስት አዳዲስ ተጨዋቾችን በድምሩ 156 ሚሊየን ፓውንድን በማውጣት ገዝተዋቸዋል፡፡ አዲስ ካስፈረሟቸው ተጨዋቾች ውስጥ አርጀንቲናዊው ኢንተርናሽናል አንሄል ዲ ማሪያን በ60 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ በመግዛት በብሪቲሽ ፉትቦል አቻ ያልተገኘለት በታሪክ ከፍተኛ የግዢ ዋጋን ያወጡበት ይገኝበታል፡፡ ሆኖም ግን ክለቡ ከመደበው ከፍተኛ የተጨዋች ግዢ በጀት በአግባቡ ተጠቃሚ ለመሆን ተስኗቸው ማንቸስተር ዩናይትድን በፕሪሚየር ሊግ ዘመቻው በ4ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የተገደበ አጨራረስ እንዲኖው አስገድደውታል፡፡
የዩናይትድ የ2014 የፕራሲዝን ፈራሚዎች
አንሄል ዲ ማሪያ፡- 60 ሚሊየን ፓውንድ
ሉክ ሻው፡- 31.5 ሚሊየን ፓውንድ
አንደር ሄራራ፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ
ማርክስ ሮሆ፡- 16 ሚሊየን ፓውንድ
ዳሊ ብሊንድ፡- 14 ሚሊየን ፓውንድ
ቫራያ ሚሊንኮቪች፡- ባልተገለፀ ዋጋ
ራዳሜል ፋልካኦ፡- 6 ሚሊየን ፓውንድ (በውሰት)
በአጠቃላይ ያወጣው፡– 155 ሚሊየን ፓውንድ
በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡ ቼልሲ
ሊቨርፑል 2014
የቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ሊቨርፑልን በ2013-17 ሲዝን ለፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለመብቃት አቅርበውት በ2ኛ ደረጃ እንዲጨርስ በማስቻላቸው በመነቃቃት የክለቡ ቦርድ ሪከርድን የሰበረ 116 ሚሊየን ፓውንድ የተጨዋች ግዢ በጀትን መድቦላቸዋል፤ ሆኖም ግን በ2014-15 ሲዝን ክለቡን ያስጨረሱት በ5ኛ ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡
የሊቨርፑል የ2014 ፕራሲዝን ፈራሚዎች
አዳም ላላና፡- 23 ሚሊየን ፓውንድ
ማሪዮ ባሎቲሊ፡- 16 ሚሊየን ፓውንድ
ላዛር ማርኮቪች፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ
አልቤርቶ ሞሬና፡- 12 ሚሊየን ፓውንድ
ኢምሬ ቻን፡- 9.8 ሚሊየን ፓውንድ
ሪኪ ላምበርት፡- 4 ሚሊየን ፓውንድ
ዴጃን ሎቨረን፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ
ዳርክ ኦሪጊ፡- 10 ሚሊየን ፓውንድ
በአጠቃላይ ያወጣው፡- 111.8 ሚሊየን
በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡- ቼልሲ