ሊሊ ሞገስ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት ማንችስተር ዩናይትድ በቅርቡ ያስፈረመው ሄንሪክ ምክሂታርያን በእግርኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ለሚከተሉት ታክቲክ አርሜንያዊውን የአማካይ አጥቂ በፈለጉበት ቦታ ለመጫወት የሚያስችል ዕድል አግኝተዋል፡፡ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎችም ባለፉት ሶስት ዓመታት ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፈውን ተጨዋች ለመመልከት ጓጉተዋል፡፡ ጆዜ በአመዛኙ በ4-2-3-1 ፎርሜሽን የሚጫወቱ በመሆናቸው ሄንሪክ በየትኛውም […]
↧