Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? |ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ

$
0
0

ከግሩም ሰይፉ

38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ ቅዳሜ ሲጠናቀቅ ለዋንጫ ጨዋታ ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ሲገናኙ፤ አዘጋጇ ኢትዮጰያ እና ሱዳን ለደረጃ ይጫወታሉ፡፡ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ በሴካፋ የዋንጫ ጨዋታ ሲገናኙ የቅዳሜው ፍልሚያ በታሪክ ለ4ኛ ጊዜ ነው፡፡ ባለፉት ሶስት የዋንጫ ጨዋታዎች ኡጋንዳ አሸንፋለች፡፡ለ37ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና በመሳተፍ ግንባር ቀደም የሆነችው ኡጋንዳ 13 ጊዜ ሻምፒዮን ስትሆን ፤ ለ17ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና የተሳተፈችው ሩዋንዳ 1 ጊዜ ብቻ ዋንጫውን ማግኘት ችላለች፡፡

File Photo

File Photo


በ38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ በዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጰያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ በሩዋንዳ 1ለ0 ተሸነፈ፤ እንደምንም በሁለተኛ ጨዋታ ሶማሊያን 2ለ0 አሸነፈ፤ ከዚያም ከታንዛኒያ ጋር 1ለ1 አቻ ተለያይቶ በምርጥ ሶስተኛ የማለፍ እድል የመጨረሻውን እጣ አግኝቶ ወደ ሩብ ፍፃሜ ገባ፡፡ በሩብ ፍፃሜ በድጋሚ የተገናኘው ከታንዛኒያ ጋር የነበረ ሲሆን በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 አቻ ከተለያዩ በኋላ በመለያ ምቶች 4ለ3 ዋልያዎቹ አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜ ገቡ፡፡ በግማሽ ፍፃሜ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ከተሰጠው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተገናኙ፡፡ የተጫወቱት መቶ ሃያ ደቂቃቃዎች ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት አበቃ፡፡ በመለያ ምቶች ከዋልያዎቹ አምበሉ ጋቶች ፓኖም ሳተ፤ ኡጋንዳዎች ደግሞ ሁሉንም የፍፁም ቅጣት ምቶች አገቡ፡፡ አዘጋጇ አገር ወደቀች፤ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት የተሰጣች ኡጋንዳ ለፍፃሜ አለፈች፡፡ በሌላ ጨዋታ ሩዋንዳ ለዋንጫ ያለፈችው ሱዳንን በመለያ ምቶች በመርታት ነበር፡፡
Yohanes sahele
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑና ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የተፈራረሙት የቅጥር ውል 8 ወራት ሆኖታል፡፡ ከተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጋር በወር 75ሺ ብር እየተከፈላቸው የሚሰሩት ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ሲቀጠሩ በወቅቱ በይፋ ተገልፆ በነበረው የውል ስምምነት መሰረት በ2017 ጋቦን በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ዋሊያዎቹ ወደ ዋናው ውድድር ለማለፍ የሚያስላቸውን ነጥብ በማግኘት የ31ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ተሳታፊነታቸውን ማረጋጋጥ ዋና ዓላማ ነው መባሉ አይዘነጋም፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የዮሃንስ እና የዋልያዎቹ እድል ላይ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት የሚከብድ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አሰልጣኙ ከተሳካላቸው ፌደሬሽኑ ኮንትራታቸውን እንደሚያራዝምም ቃል ገብቷል፡፡ ግን በሌሎቹ የቅጥር ዓላማዎች ዋልያዎቹ በቻን 2016 እና በሴካፋ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ውድድሮችም አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅባቸው ተመልክቶ ነበር፡፡ በእርግጥ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው የቻን ውድድር ዋልያዎቹ ማለፋቸው በዮሃንስ ሳህሌ የተመዘገበው ጉልህ ስኬት ማለት ይቻላል፡፡ መርቂ ውጤት በቻን ላይ ማስመዝገብ አለማስመዝገባቸውን ሲደርስ የምንታዘበው ይሆናል፡፡ ዋልያዎቹ አዘጋጅ ሆነው በተሳተፉበት የሴካፋ ሻምፒዮና ግን የተጠበቀው አመርቂ ውጤት ሳይመዘገብብት ቀርቷል፡፡ ዮሃንስ ሳህሌ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ የዋንጫ ተፎካካሪ የሚያደርጋቸውን አስተያየት፤ አቀም እና ቡድን የመምራት ባህርይ አሳይተዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ከጅምሩ የቡድናቸውን ተሳትፎ ልምድ ለማግኘት፤ አዲስ ብሄራዊ ቡድን ለመገንባት፤ ለወጣቶች እድል ለመስጠት እያሉ ቆይተዋል፡፡ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ሩጫው ሲያበቃም ይሄ ግትርነታቸው ተስተውሏል፡፡

ከኡጋንዳው ሚቾ ጋር በሰጡት መግለጫ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ << በሚገባ ልጆች ያየንበት እድል የሰጠንበት ውድድር ነበር ›› በማለት ተስፋ አስቆራጩ ተሳትፏቸው እንዳጠገባቸው ተኩራርተው መልሰዋል፡፡ አሰልጣኙ በሴካፋ ውድድር ላይ በጥቅሉ ስንታዘባቸው • ቡድን በመገንባት ተጠምጃለሁ ብለው ቡድኑን በማፈራረስ • ልምድ ያላቸውን ተጨዋች ሙሉ ለሙሉ ጠራርጎ በማስወገድ የቡድኑን አቅም በማዳከም • ዋንጫውን ለመብላት የሚያስችል አስተያየት ከመስጠት ከደጋፊ፤ ከሚዲያ አጓጉል አተካራ በመፍጠር • በየጨዋታው ከቤንች ተነስተው ቡድኑን በማንቃት እና በማበረታት ከመስራት በማን አለብኝነት በመኮፈስ … አሳልፈዋል፡፡

The post Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? | ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles