(ኢትዮ-ኪክ) የአለም የቤት ውስጥ ውድድሮች ንግስት ገንዘቤ ዲባባ በእንግሊዝ በበርኒገሀም እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በቀናት ልዮነት ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ አስገኝታለች። ገንዘቤ የ1500 ሜትር ርቀቱን በ4:05.27 በመግባት ከማሸነፏ በተጨማሪም በአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ያገኘቻቸውን የወርቆች ቁጥር 5 አድርሳለች።
↧