(ዘ-ሐበሻ) ቸልሲ አስልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆን ለሁለተኛ ጊዜ አባረረ:: በፕሪምየር ሊጉ 16 ጨዋታ አድርገው 15 ነጥብ ብቻ የያዙት ሆዜ ሞሪንሆ ዛሬ የተባረሩት በቸልሲ የቦርድ ውሳኔ እንደሆነ ከወደ እንግሊዝ የተሰሙ መረጃዎች አመልክተዋል::
ፕሪምየር ሊጉን ካሸነፉ ከ7 ወር በኋላ የተባረሩት የፕሪምየር ሊጉ አድማቂ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆን በተመለከተ ደይሊ ሜይል የተሰኘው ድረገጽ ባሰባሰበው የሕዝብ ድምጽ “ቸልሲ ሞሪንሆን ማባረር ነበረበት ወይ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦ 57%ቱ ሕዝብ እድል ሊሰጠው ይገባ ነበር ማባረሩም መቆየር ነበረበት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::
ዘ-ሐበሻ ከ እንግሊዝ የዜና አውታሮች ባሰባሰበችው መረጃ መሠረት ሞሪንሆ ዛሬ ወደ ቸልሲ ልምምድ ስፍራ ኮብሃም ተጠርተው ከክለቡ ፕሬዚዳንት ብሩስ በክ እና ዳይሬክተሩ ዩጂን ተነቡአም ጋር ስብሰባ ያደረጉ ቢሆንም ለ10 ደቂቃ እንኳ ሳይነጋገሩ መሰናበታቸው ተነግሯቸዋል::
ሞሪንሆ ከዚህ ቀደም የቸልሲ አሰልጣኝ በነበሩበት ወቅት ተባረው ወደ ሪያል ማድሪድ አምርተው የነበረ ቢሆንም እንደገና በአብራሞቭች ተጠርተው ሥራቸው ከተመለሰላቸው በኋላ ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ ተባረዋል::
ሞሪንሆ ሳይበሩ በፊት ዘ-ሐበሻ በስፖርት ገጿ የሚከተለውን ዘገባ አስነብባ ነበር… እዚህ ይጫኑ
The post Sport: ቸልሲ ሞሪንሆን ለ2ኛ ጊዜ አባረረ appeared first on Zehabesha Amharic.