Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: ያከተመው የበላይነት |የእንግሊዝ ክለቦች በአህጉራዊ ውድድር ተዳክመዋል

$
0
0

 

champions

የእንግሊዝ ክለቦች ከ2004/05 የውድድር ዘመን ጀምሮ በአውሮፓ መድረክ የበላይነቱን ወስደው ቆይተዋል፡፡ ይህ የበላይነት እስከ 2011/12 የውድድር ዘመን ድረስ ዘልቋል፣ በዚህ የስምንት ዓት ጊዜ ውስጥ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲ የውድድር ዘመኑ አሸናፊዎች ነበሩ፤ አርሰናል ደግሞ የፍፃሜ ተፋላሚ በመሆን የእንግሊዝ ክለቦች ኩራት ነበር፡፡ ከ2003/04 የውድድር ዘመን ጀምሮ እስከ 2011/12 የውድድር ዘመን ድረስ የእንግሊዝ ክለቦች በምድብ ማጣሪያ ሽንፈቱን ያስተናገዱበት ከፍተኛው ቁጥር አምስት ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ግን ከወዲሁ (ገና አንድ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ እየቀረ) ሰባት ሽንፈቶች ተከስተዋል፡፡ (አራቱ ክለቦች በጋራ ያስመዘገቡት ሽንፈት መጠኑ እጅግ በጣም ከፍ ብሏል፡፡ ውጤቱ በዚህ ቁጥር ወደ ሶስት ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ክለቦች አወራረድ ምን ይመስላል? ተከታዩ ፅሑፍ ምላሽ አለው፡፡

2000/05

የሊቨርፑል ተአምር የታየበት የኢስታንቡሉ የፍፃሜ ጨዋታ የመርሲሳይዱ ክለብ 3ለ0 ከመመራት ተነስቶ ቻ ከተለያየ በኋላ በመጨረሻም በመለያ ምት ያሸፈነበት ነበር፡፡ ‹‹የኢስታንቡሉ ተአምር›› የሚል ስያሜ ያገኘው የፍፃሜ ጨዋታ የእንግሊዝ ክለቦችን አነቃቅቷል፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ቼልሲን ያሸነፈው የአሰልጣኝ የራፋ ቤኒቴዝ ቡድን ሻምፒዮን የሆነበት መንገድ ዛሬም ድረስ የመወያያ ርዕስ ሆኗል፤ በዚያ የውድድር ዘመን አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፈው በውድድሩ በሁለተኛው ዙር ነበር፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡-4

ሩብ ፍፃሜ የደረሱ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 2

2005/06

በስታድ ደ ፍራንስ አርሰናል በባርሴሎና 2ለ1 የተሸነፈበት የፍፃሜ ጨዋታ ፍፁም የሚያስቆጭ ነበር፡፡ የእንግሊዝ ክለቦችን ከሩብ ፍፃሜ ጀምሮ በመወከል ብቸኛ የነበረው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ታሪክ ሊሰራበት የተቃረበበት አጋጣሚ መቼም ቢሆን አይረሳም፡፡ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ጉዟቸው ከሁለተኛው ዙር ሲገታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከምድብ ማጣሪያው ማለፍ አልቻለም፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 03

ሩብ ፍፃሜ የደረሱ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 1

2006/07

ሊቨርፑል በ2004/05 የውድድር ዘመን ለፍፃሜ ከቀረበው ኤሲ ሚላን ጋር በድጋሚ መገናኘቱ ትኩረትን ቢስብም የአቴንሱ የፍፃሜ ጨዋታ በጣልያኑ ክለብ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ ሆኖም ሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸው ለፕሪሚየር ሊጉ እንደ በጎ ዜና ሊወሰድ ይችላል፣ አርሰናል በሁለተኛው ዙር በፒ.ኤስ.ቪ አይንድሆቨን በደርሶ መልስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ለመሆን ተገድዷል፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 4

2007/08

በሞስኮው ሉዝኒስኪ ስታዲየም ሁለት የእንግሊዝ ክለቦች ለፍፃሜ ቀርበው መደበኛው ሰዓት 1ለ1 ከተጠናቀቀ በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድ ቼልሲን በመለያ ምት 6ለ5 አሸንፎ ከ1999 በኋላ የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ኦነግ፣ በሩብ ፍፃሜው አርሰናልን ያሸነፈው ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ለቼልሲ እጅ ሰጥቶ ለፍፃሜ ለመግባት ሳይችል ቀርቷል፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 4

2008/09

ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ሊቨርፑል በተሳተፉበት ውድድር ሊቨርፑል ከምድብ ማጣሪያው ሲወድቅ የተቀሩት ሶት ክለቦች ለግማሽ ፍፃሜ ደረሱ፣ ቼልሲ በባርሴሎና ተሸንፎ ለፍፃሜ ለመግባት የነበረው ህልም ሳይሳካ ቀረ፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን አሸንፎ ለፍፃሜ ቢቀርብም በባርሴሎና ሮም ኦሎምፒክ ላይ 2ለ0 ተረታ፣ ሶስቱ የእንግሊዝ ክለቦች በምድብ ማጣሪያው በጋራ ሽንፈትን ያስተናገዱት በሁለት አጋጣሚዎች ብቻ ነበር፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 3

ሩብ ፍፃሜ የደረሱ የሊጉ ክለቦች፡- 3

2009/10

ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል እና ቼልሲ ምድብ ማጣሪያዎችን ሲያልፉ ሊቨርፑል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ተሳነው፡፡ በሁለተኛው ዙር ቼልሲ የውድድሩ አሸናፊ በሆነው ኢንተር ሚላን ሲሸነፍ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ከሩብ ፍፃሜ ማለፍ ተሳናቸው፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 3

ሩብ ፍፃሜ የደረሱ የሊጉ ክለቦች፡- 2

2010/11

ማንቸስተር ዩናይትድ ለፍፃሜ በቀረበበት የውድድር ዘመን በባርሴሎና ዌምብሌይ ላይ 3ለ1 ተሸንፎ ዋንጫ ለማንሳት የነበረው ህልም ሳይሳካ ቀረ፣ አርሰናል በሁለተኛው ዙር በውድድሩ አሸናፊ ባርሴሎና በተረታበት አጋጣሚ ቶተንሃም እና ቼልሲ ሩብ ፍፃሜ ድረስ መጓዝ ችለው ነበር፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 4

ሩብ ፍፃሜ የደረሱ የሊጉ ክለቦች፡- 3

2011/12

በፕሪሚየር ሊጉ 6ኛ ደረጃን ይዞ የፈፀመው ቼልሲ በቻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ከባለሜዳውን ባየርን ሙኒክ በመደበኛው ጨዋታ 1ለ1 ተለያይቶ በመለያ ምት አሸንፎ ሻምፒዮን የሆነበት መንገድ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ ማንቸስተር  ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ ከምድብ ማጣሪያው በተሰናበቱበት የውድድር ዘመን የአርሰናል ጉዞ በሩብ ፍፃሜው በመገታቱ ቼልሲ ረጅም ርቀት ተጉዞ ያስመዘገበው ስኬት የእንግሊዝ ኩራት እንዲሆን አስችሎታል፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 2

ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 1

2012/13

ቻምፒዮንስ ሊጉ በአዲስ መልክ ከ2003 ጀምሮ ከተዋቀረ በኋላ በሩብ ፍሜው አንድም የእንግሊዝ ክለብ ያልተገኘበት የውድድር ዘመን ነበር፣ ይህ የእንግሊዝ ክለቦች አቅም እየተዳከመ የመምጣት ምልክት አንድ አካል ተደርጎ ይወስዳል፡፡ አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ከሁለተኛው ዙር የተገታው ጉዟቸው ሩብ ፍፃሜ ለመግባት የነበራቸውን ህልም መና ሲያስቀረው ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከምድብ ማጣሪያው እንኳን ማለፍ አልቻሉም ነበር፡፡ ሲቲ በምድብ ማጣሪያው አንድም ጨዋታ አለማሸነፉ በብቃቱ ላይ ጥያቄ አስነስታሏል፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 2

ሩብ ፍፃሜው የተቀባቀሉ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 0

2013/14

በሊዝበን ስታድ ደ ሉዝ ሁለቱ የማድሪድ ክለቦች ለፍፃሜ ቀርበው ሪያል ማድሪድ ለ10ኛ ጊዜ ይህንን ዋንጫ ማንሳት ችሏል፣ ባርሴሎና ደግሞ የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚ ሆኖ በአትሌቲኮ ማድሪድ ያስተናገደው ሽንፈት ግማሽ ፍፃሜ እንዳይገባ አድርጎታል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሰናል እና ቼልሲ ረጅም ርቀት ለመጓዝ የነበራቸው እቅድ የምዕራ ለንደኑን ክለብ ብቻ ግማሽ ፍፃሜ አድርሶ የቀሪዎቹን ሶስት ክለቦች ጉዞ ከሁለተኛው ዙር በላይ እንዳይጓዝ አድርጓል፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 4

ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ የሊጉ ክለቦች ቁጥር፡- 1

2014/15

በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አንድም የእንግሊዝ ክለብ በሩብ ፍፃሜ ያልተስተዋለበት የውድድር ዘመን ነበር፡፡ አርሰናል፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲገቡ ሊቨርፑል ከምድብ ማጣሪያው እንኳን ማለፍ አልቻለም፡፡ በአንፃሩ ከስፔን ክለቦች ሶስቱ ሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር የቀረቡ የሊጉ ክለቦች፡- 3

ሩብ ፍፃሜ የገቡ የሊጉ ክለቦች፡- 0

The post Sport: ያከተመው የበላይነት | የእንግሊዝ ክለቦች በአህጉራዊ ውድድር ተዳክመዋል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles