[በተሻገር ጣሰው]
አንዋር ማዴራ ይባላል በፈርነጆቹ አቆጣጠር ማርች 2003 ላይ ነበር በመዲናችን አዲስ አበባ የተወለደው ::
ገና ታዳጊ ህፃን እያለ በማደጎ ወደ ስፔን ተጎዘ በስፔን ቆይታውም ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር በመኖሩ ከኢትዮጵያ ወስደው የሚያሳድጉት ቤተሰቦቹ ፍላጎቱን ለማሞላት ወደ እግር ኳስ አካዳሚ አስገቡት ::ልክ አስራ አንድ አመቱ ሲሆነው ከአስራ ስድስት አመት በታች ሴልታ ቪጎን ክለብ ተቀላቅሎ መጫወት ጀመረ::
አንዋር አሁን አስራ ሶስት አመቱ ነው:: ከወደ ስፔን የተሰማው ዜና እንደሚያስረዳው በትውልድ ኢትዮጵያዊው የሆነው አንዋር ማዴራ የባርሴሎና ክለብ የበላይ ጠባቂዎችን በአጨዋወት ጥበብ በመማረኩ የተነሳ ሴልታ ቪጎን ክለብ ለቆ ከ16 አመት በታች ለባርሴሎና ክለብ እንዲጫወት ማስፈረማቸውን ነው የተዘገበው::
ተጫዋቹ በያዝነው በፈረንጆቹ አዲስ አመት ጨዋታውን እንደሚጀምርና ከ3 አመት በሆላ ለዋናው ባርሴሎና ክለብ መጫወት እንደሚፈልግ ምኞቱን ተናግሯል::
ለትውልደ ኢትዮጵያዊው አንዋር ማዴራ ያሰበው እንዲሳካለት መልካም ምኞታችን ነው
The post Sport: ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ወጣት ለባርሴሎና ክለብ ፈረመ appeared first on Zehabesha Amharic.