Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር ክለብ በኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳልሀዲን ሰኢድ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ሊጥልበት ነው

$
0
0

salahdin
ኢትዮኪክ ኦፍ እንደዘገበው:-

* ሳላ ኢትዮጵያ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ሳልሀዲን ሰኢድ ከአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር ጋር ለሁለት አመት ለመጫወት የነበረው ውል ለአምስት ወራት ብቻ ዘልቆ ከክለቡ ጋር ባለፈው ሳምንት መለያየቱ ይታወሳል።

በግብፁ አል አህሊ ረጅም ወራቶችን በጉዳት ካሳለፈ በኃላ የአልጄሪያውን MC-አልጀር የተቀላቀለው ሳልሀዲን በ5 ጨዋታዎች በአጠቃላይ 200 ደቂቃዎችን ተቀይሮ በሜዳ ውስጥ ቢቆይም ጎል እና መረብ ሳይሳኩለት ቀርተዋል።

ከአልጀሪያ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የአልጄሪያው ኤም ሲ አልጀር ክለብ ከ USMA ጋር ባደረጉት የአልጀረስ ደርቢ ጨዋታ ላይ ሳልሀዲን ሰኢድ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን አሳይቷል በሚል ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ለማስተላለፍ የክለቡ የዲስፒሊን ኮሚቴው በቀጣዪ ሳምንት ስብሰባ ጠርቷል።

እንደ መረጃው ከሆነ በእለቱ በተደረገው የደርቢ ጨዋታ ላይ ሳልሀዲን ከጉዳቱ አገግሞ ጥሩ አቋም ላይ መገኘቱን ለተቃራኒው ክለብ USMA ለማሳየት መፈለጉን እና ከዚህ ከደርቢ ጨዋታው በፊት ሳልሀዲን ከUSMA ክለብ ጋር ስሙ ተንስቷል የሚለው መረጃ በስፋት በመወራቱ በደርቢ ጨዋታው ላይ በምክትል አሰልጣኙ ትህዛዝ ሳልሀዲንን አሟሙቆ ሊገባ ሲል ዋናው አሰልጣኙ አሳባቸውን ቀይረው ወደ ወንበሩ እንዲመለስ ያስተላለፉትን ትህዛዝ ሳልሀዲንን ክፉኛ ተበሳጭቶ በወቅቱ ላሳያው ያልተገባ ፀባይ የገንዘቡ ቅጣት እንደሚጠብቀው ዘገባው የሚያመለክተው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ሳልሀዲን ሰኢድ በአሁኑ ሰአት ከቤተሰቦቹ ጋር በአገሩ ምድር ኢትዮጵያ ይገኛል።

The post Sport: የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር ክለብ በኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳልሀዲን ሰኢድ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ሊጥልበት ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles