በተደጋጋሚ የሃገራችንን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገችው አትሌት አልማዝ አያና በስዊዘርላንድ የጉልበት ቀዶ ጥገና አደረገች:: የቀዶ ጥገናው የተሳካ የነበረ ሲሆን ዶክተሮቿ ከሦስት ወር በኋላ ወደ ልምምድ እንድትመለስ ምክር እንደሰጡ ተገልጿል:: አልማዝ አያና በአሁኑ ወቅት ስዊዘርላንድ የምትገኝ ሲሆን የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል::
↧