ነቢዩ ሲራክ
ጥር 13 ቀን 2008 ዓም
======================================
* እንኳንም ደስ ያለን !
* ከወንዶች ተስፋየ ከሴቶች ትርፊን የቀደመ አልነበረም !
1000 የሚገመቱ ተሳታፊዎች በሚሳተፉበት ዘንድሮ በዱባይ እየተካሔደ ባለው የዱባይ ማራቶን 2016 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአረንጓዴውን ጎርፍ ድል በበርሃዋ የአረብ ኢምሬት ከተማ በዱባይ ደግመውታል ! አንጸባራቂውን ድል የደገሙት አትሌቶቻችን በወንድና በሴት በተደረገው ውድድር ተከታትለው በመግባት ያገኙት ውጤት በውድድሩ የበላይነትን አቀናጅቷቸዋል ።
በወንዶች አሸናፊ የሆነው ተስፋየ አበራ ዲባባ የገባበት ሰዓት 02:04:24 መሆኑ ታውቋል ። በሁለተኛነት ተስፋየን ተከትሎ የገባው የአምናው አሸናፊ ለሚ ብርሃኑ ኃይሌ 02:04:33 ሰዓት ሲያስመዘግብ በሶስተኛነት ጸጋየ መኮንን አሰፋ 2:04:46; ሰዓት ማስመዝገቡ ታውቋል ።
በሴቶች ውድድር አሸናፊ የሆነችው ትርፊ ጸጋየ ብየነ 02:18:41 ሰዓት ስታስመዘግብ አማኔ ብሪሶ ሻንኩሌ በ 02:20:48 ሰዓት በሁለተኛነት ገብታለች ። መሰለች መልካሙ ኃይለየሱስ በ02: 22:29 ሰዓት በሶስተኛነት ተከትላ መግበቷም ታውቋል !
በወንድም በሴትም በተደረገው ውድድር ከ1 እስከ 5 ተከታትለው የገቡበትን ሙሉው ውጤት እንደሚከተተለው ነው !
በወንዶች Men (All from Ethiopia)
1) Tesfaye Abera Dibaba – 2 hours: 04 minutes: 24 seconds;
2) Lemi Berhanu Hayle 2:04:33;
3) Tsegaye Mekonnen Asefa 2:04:46;
4) Sisay Lemma Kasaye 2:05:16;
5) Mula Wasihun Lakew 2:05:44.
በሴቶች Women (all from Ethiopia):
1) Tirfi Tsegaye Beyene 2:19:41;
2) Amane Beriso Shankule 2:20:48;
3) Meselech Malkamu Haileyesus 2:22:29;
4) Sutume Asefa Kebede 2:24:00;
5) Mulu Seboka Seyfu 2:24:24.
አስገራሚውን ድል በቦታው በመገኘት የታዘቡት በዱባይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአትሌቶች ከፍ ታለ ሞራል ሲሰጡ መዋላቸው የአረብ መገናኛ ብዙሃምንን አትኩሮት በአድናቆት ስበውት ተስተውሏል !
እንኳን ደስ አለን !
The post Sport: ጀግኖች አትሌቶች በዱባይ ማራቶን 2016 ድንቅ ድል ተጎናጸፉ appeared first on Zehabesha Amharic.