(ዘ-ሐበሻ) ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ልዊስ ቫንገሃል ማን.ዩናይትድን ከተረከቡ በኋላ ባደረጉት 78 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት 31 ጊዜ ብቻ ነው:: 29 ጊዜ አቻ ሲወጡ 18 ጊዜ ደግሞ ባልተጠበቁ ቡድኖች ሳይቀር ተሸንፈዋል::
የማን. ዩናይትዱ አሰልጣን ቫንገል በተለይ ከቅዳሜው የሳውዝ ሃምፕተን ጨዋታ ሽንፈት በኋላ ከክለቡ ይሰናበታሉ የሚለውን መረጃ በፍጥነት እያስኬደው ይገኛል:: ተጫዋቾቹ በአሁኑ ወቅት የአሰልጣኙን የአጨዋወት መንገድ መከተል ማቆማቸውን የሚገልጹት መረጃዎች በክለቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜያት የተጫወቱ ተጫዋቾች አውራጣታቸውን ዝቅ በማድረግ ለአሰልጣኙ ያላቸውን ተቃውሞ እያሳዩ ነው::
አንዳንድ ተጫዋቾች አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ ለክለቡ ቺፍ ኤድ ውድ ዋርድ መናገራቸውን የሚገልጹት መረጃዎች ክልቡን ሙሉ በሙሉ ሪያን ጊግስ እንዲይዘው ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ተሰምቷል:: ኤድ ውድ ዋርድም ለማንቸስተር ዩናይትድ ያልተጠበቀ ሽንፈት ተጫዋቾች ለአሰልጣኙ አጨዋወት ዘዴ ደስተኛ ባለመሆናቸው መሆኑን መረዳታቸውን ከክለቡ የሚመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ::
ቫንግሃል ከተሰናበቱ ሪያን ጊግስ ክለቡን ይህ ሲዝን እስከሚጠናቀቅ ሊመራው ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ቢኖሩም ጊግስ ተጠባባቂ አሰልጣኝ ሳይሆን በቋሚነት መያዝ እንደሚፈልግ ተዘግቧል::
The post Sport: ማንቸስተር ዩናይትድ ቫንገሃልን ለማሰናበት ከጫፍ ደርሷል | ተጫዋቾች አውራ ጣቶቻቸውን ዝቅ እያደርጉባቸው ነው appeared first on Zehabesha Amharic.