Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: ዋይኒ ሩኒ –ወደ ቀድሞ ወርቃማ ዘመኑ ይመለስ ይሆን?

$
0
0

 

የማንችስተር ዩናይትድ ጎሎችን ያለማስቆጠር ችግር የዘንድሮው ሲዝን መሰረታዊ ችግሩ ሆኖ እስካሁንም ድረስ ዘልቋል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ቅዳሜ በኦልድ ትራፎርድ የዝቅተኛ ዲቪዚዮኑ ሼፊልድ ዩናይትድን 1ለ0 በረታበት የኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ግጥሚያም በዘንድሮው ሲዝን ለስምንተኛ ጊዜ 0ለ0 በሆነ ውጤት በመለያየት እስከመቃረብ ደረጃ ደርሶ ነበር፡፡

roney body kick

በግጥሚያው የማንችስተር ዩናይድ የመጀመሪያውን ኢላማ ያገኘች ጎል የማስቆጠር ሙከራን ለማየት እስከ 69ኛው ደቂቃ ድረስ ለመታገስ መታየቱንም ምን ያህል በቫንሃል ስር የማንቸስተር ዩናይትድ የማጥቃት ስትራቴጂ መላላቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ማንቸስተር ዩናይትድ በዝቅተኛ ዲቪዚዮኑ ሚድልስብራ ተሸንፎ ከካፒታል ዋን ውድድር ውጪ ለመሆን የተገደደው ሙሉውን 90 ደቂቃዎችን አንድ ጎልን እንኳን ለማስቆጠር ተስኖት ለማሳለፍ ሲገደድ በመታየቱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ያንን ችግራቸውን ለመቅረፍ ሲሉ ቫንሃል በቅዳሜው የኤፍ.ኤ.ካፕ ግጥሚያ የዋናው ቡድናቸው መደበኛ ቋሚ ተሰላፊዎች ይዘው ወደ ሜዳ ቢገቡም ከሼፊልድ ዩናይትድ ጋር የማሸነፊያ ጎልን ለማስቆጠር በባከነ 6 ደቂቃዎች ጭማሪ ውስጥ ዋይኒ ሩኒ በፍፁም ቅጣት ምት ነው፡፡ በ93ኛው ደቂቃ ላይ የዕለቱ አርቢትር ለማንቸስተር ዩናይትድ የፍፁም ቅጣት ምት እድልን የሰጡት ተቀይሮ በገባው ሆላንዳዊው ኢንተርናሽናል ሜምፊስ ዴፓይ ላይ በተሰራ ፋውል ነው፡፡

ከዚህ በተረፈ ግን አጠቃላዩ የማንቸስተር ዩናይትድ የማጥቃት እንቅስቃሴ ቡድኑ ጎሎችን ለማስቆጠር እንዲችል የሚረዳው አይነት አይደለም፡፡ ቫንሃል የቡድናቸው ጎል የማስቆጠር ችግርን ለመቅረፍ በጨዋታው 2ኛው ግማሽ የወሰዱት እርምጃም ከቡድናቸው በመከላከል ላይ ያተኮረ የጨዋታ እንቅስቃሴ ካላቸው ባስቲያን ሼዌንስቲገር እና ማሩዋን ፌላይኒ ይልቅ ሁዋን ማታ እና አንደር ሄሬራን ቀይረው በማስወጣት መሆኑ ከራሳቸው ክለብ ደጋፊዎች የተቃውሞ ድምፅ ተሰምቶባቸዋል፡፡

በዕለቱ ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴ የነበረው ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽነል ማሩዋን ፌላይኒን ቀይረው ያስወጡት ዘግይተው መሆኑም ሌላው የተተቹበት ጉዳይ ሆኗቸዋል፡፡ በአጠቃላይም በግጥሚያው የማንቸስተር ዩናይትድ ብቸኛው የምስራች የቡድኑ አምበል ዋይኒ ሩኒ በሁለት ተከታታይ ግጥሚያዎች የማሸነፊያ ጎልን ለማስቆጠር መቻሉ ብቻ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ምክንያቱም ሩኒ የማንቸስተር ዩናይትድ የመጨረሻው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው ስዋንሲ ሲቲን 2ለ1 የረታበትን የማሸነፊያ ጎልንም ለማስቆጠር ችሏል፡፡ ሉዊ ቫንሃል ቡድናቸው ሼፊልድን 1ለ0 በማሸነፍ የኤፍ.ኤ.ካፕ ዘመቻውን ወደ 4ኛው ዙር ለማሸጋገር ከቻለ በኋላ በሰጡት ፖስት ማች ፕሬስ ኮንፈረንስ ውስጥ ከዚህ በታች ያለው ይገኝበታል፡፡

ስለ ቡድናቸው የጨዋታ እንቅስቃሴ

‹‹በመጀመሪያው ግማሽ በምንመኘው መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ የጨዋታ እንቅስቃሴ ሳይኖረን ቀርቷል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በክንፍ በኩል በተሻለ ሁኔታ የማጥቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ነበረብን፡፡ በ2ኛው ግማሽ በተሻለ ሁኔታ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን ለመፍጠር ችለናል፡፡ ሆኖም ግን የሼፊልድ ዩናይትድ ተሰላፊዎች በጠንካራ ሁኔታ ቅንጅትን ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ በመታየታቸው በምንመኘው መልኩ በበቂ ሁኔታ የመከላከል ስትራቴጂያቸውን ለማስከፈት ሲሳነን ታይቷል››

ስለ ማሸነፊያዋ የፍፁም ቅጣት ምት

‹‹በእኔ አመለካከት ትክክለኛነት ያለው የፍፁም ቅጣት ምት እድልን ለማግኘት ችለናል፡፡ ደግሞም ሜምፊስ ዴፓይ ወደ ተጋጣሚያችን ፔናሊቲ ቦክስ በከፍተኛ ፍጥነት ሆኖ በመግባት ላይ በመሆኑ ጎል የማስቆጠር መልካም አጋጣሚን ሲከላከል ታይቷል፡፡ እሱ ግጥሚያውን ለማሸነፍ እንድንችል የረዳን የቡድናችን ትክክለኛው ጀግና ሆኗል ለማለት እችላለሁ፡፡ ከግጥሚያው በፊት ለቡድናችን ተላፊዎች የነገርኳቸው ነገር ከሁሉም ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ጉይ የኤፍ.ኤ.ካፕ ዘመቻችንን ወደ 4ኛ ዙር ለመሸጋር መቻላችንን ነው በሚል ነው፡፡ ባሰብነውም መልኩ ግጥሚያውን በድል ለማጠናቀቅ በመቻላችን በተመዘገበው ውጤት የማንደሰትበት ምክንያት አይኖርም››

rooney

ቡድናቸው ማሻሻል ስለሚገበው ብቃት

‹‹የጎል ማስቆጠር ዕድሎችን የመፍጠር ብቃቶችን ማሳደግም እስካሁንም ድረስ በልዩ ትኩረት ልንሰራበት የሚገባን ተግባር ነው፡፡ ለዚህ ተግባራዊነት የኳስ ቁጥጥሮችን በፍጥነት ወደ ፊት የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት ከፊታችን ይጠብቀናል፡፡ ይህንን ስል ቢያንስ ከእዚህ ግጥሚያ የሼፊልድ ዩናይትድ ተሰላፊዎች በጠንካራ ሁኔታ የመከላከልን ተግባር ለመፈፀም መወሰናቸው ግን ትልቅ ችግርን እንዲፈጠርብን መንስኤ ይሆናል››

ስለ ዋይኒ ሩኒ የፍፁም ቅጣት ምት

‹‹በግጥሚያው ይዣቸው የገባሁት የመጀመሪያዎቹ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት መቺዎች ሁዋን ማታ እና አንደር ሄሬራ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም ቀይሬ በማስወጣቴ ዋይኒ ሩኒ ፔናሊቲውን የመምታት እድለኛ ሊሆን ችሏል፡፡ ያለፉት ሁለት ግጥሚያዎቻችን ላይ በእያንዳንዱ የማሸነፊያ ጎልን ለማስቆጠር መቻሉም በራስ የመተማመን መንፈሱ እጅግ ያማረ ሁኔታ ላይ መገኘት መቻሉን የሚያሳይ ነው፡፡ ተስፋ የማደርገውም ከፊታችን ባሉት ግጥሚያዎች ላይ ሌሎች በርካታ ጎሎችን ለማስቆጠር ይችልልናል ብዬ ነው፡፡

ስለ ጃንዋሪ ወር እቅዳቸው

‹‹በእኔ አመለካከት የጃንዋሪው የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጨዋቾችን መግዛት ብልህነት ያለው ተግባር ነው፤ ምናልባትም ግን ለቡድናችን የሚጠቅሙ አዳዲስ ተጨዋቾች ዝግጁ ሲሆንልን ፊርማውን ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ ጉጉትን የምናሳድር መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፤ ሆኖም ግን ይህንን ተግባር በመደበኛነት ለመፈፀም ያቀድነው ነገር አለመኖሩን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

The post Sport: ዋይኒ ሩኒ – ወደ ቀድሞ ወርቃማ ዘመኑ ይመለስ ይሆን? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles