Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: 26ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ: አርሰናል የመሪነት ትንቅንቁን ተቀላቀለ ፤ ማን ዩናይትድ ካለፉት 10 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 3ን ብቻ ነው

$
0
0

dani

(ዘ-ሐበሻ) 26ኛው ሳምንት የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትናንት እና ዛሬ ቀጥሎ ውሏል:: በሳምንቱ የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶች ተከስተዋል:: ፕሪምየር ሊጉን በ53 ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ሌስተር ሲቲ በባከነ ሰዓት በአርሰናል በተቆጠረበት ጎል ቢሸነፍም አሁንም ፕሪምየር ሊጉን እየመራ ይገኛል::

በዳኒ ዌልቤክ የባከነ ሰዓት ጎል ያሸነፈው አርሰናል በ2ኛነት ፕሪምየር ሊጉን እየተከተለ የመሪነት ትንቅንቁን ተቀላቅሏል:: ሌስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ አርሰናልን ከ1994 ወዲህ አሸንፎ አያውቅም:: የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ዌንገር ስለዚህ ጨዋታ አስተያየታቸውን ሲሰጡ “ሌስተሮች በመከላከል በኩል ጥሩ ነበሩ:: እስከ እረፍትም 1ለ0 እየተመራ ነበር:: ሌስተሮች በመከላከሉ በኩል ጥሩ ባይሆኑ ኖሮ ብዙ ጎሎችን እናስቆጥር ነበር” ብለዋል::

united

በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ አሰልቺ ጨዋታ እያደረገ ነው እየተባለ በስፖርት ተንታኞች ዘንድ የሚተቸው ማን.ዩናይትድ አሁንም ሽንፈትን አስተናግዷል:: ትናንት በጥቋቁሮቹ ድመቶች 2ለ1 ተሸንፈዋል:: ሰንደርላንድ በፕሪምየር ሊጉ ወራጅ ቀጠና ላይ ያለ ቢሆንም ማን.ዩናይትድን አሸንፈውታል:: ማን.ዩናይትድ ባለፉት 10 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻለው 3 ጊዜ ብቻ ሲሆን; 3 ጊዜ አቻ ወጥቶ 4 ጊዜ ተሸንፏል::

በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል አስቶንቭላን ግማሽ ደርዘን ጎል አስቆጥሮበት 6ለ0 አሸንፎታል::
በርንዝማውዝ በስቶክ 3ለ1 ተሸንፏል:: ቸልሲ ኒውካስትልን 5ለ1.. ዌስትብሮም ኤቨርተንን 1ለ0; ዋትፎርድ ክርስታል ፓላስን 2ለ1 እንዲሁም ሳውዛምፕተን ስዋንሳን 1ለ0 ሲያሸንፉ ኖርዊች እና ዌስትሃም 2ለ2 ተለያይተዋል:: ይህ ዜና እየተጻፈ ባለበት ወቅት ማንቸስተር ሲቲ እና ቶተንሃም እየተጫወቱ ነው:: የሆለቱ አሸናፊ ፕሪምየር ሊጎን በ3ኝነት ይመራል::

The post Sport: 26ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ: አርሰናል የመሪነት ትንቅንቁን ተቀላቀለ ፤ ማን ዩናይትድ ካለፉት 10 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 3ን ብቻ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles