በለንደኑ ማራቶን ሰፊ ግምት የተሰጠው ቀነኒሳ በቀለ በጤና እክል ከውድድሩ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደማይሳተፍ መታወቁ መነጋገሪያ የመሆኑን ያህል ኢትዮጵያ ተስፋ እንደሌላት የተቆጠረውን የለወጠው አዲሱ የማራቶን ጀግና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል። በዘንድሮው የለንደን 40ኛ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ጎርፍ መሆናቸውን ዳግም አስመስከረዋል። ኬንያዊው ብቻ ሁለተኛ ሲወጣ እስከ ስድስተኛ ያለውን ኢትዮጵያውያን አሸንፈዋል። በውጤቱም 1ኛ የወጣው ሹራ ቂጣታ ኢትዮጵያ 2:05.41 ሲያስመዘግብ ሁለተኛው ኬንያዊ ኪፕቹምባ 2:05.42 ሰዓት ገብቶዋል። ከሶስተኛ እድል ስድስተኛ ኢትዮጵያውያን ተቆጣጥረውታል። 3. ሲሳይ ለማ ኢትዮጵያ 2:05.45፣ 4. ሞስነት ገረመው ኢትዮጵያ 2:06.04፣ 5. ሙሌ ዋሲሁን ኢትዮጵያ 2:06.08፣ 6. ታምራት ቶላ ኢትዮጵያ 2:06.41:: የአትሌቲክስ መንደር እንዲህ በርከት ያሉ ጀግኖችን አፍርቶ ተስፋን አለምልሟል።
The post በለንደኑ ማራቶን ያልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ ሹራ ቂጣታ አሸናፊ ሆኗል appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.