በዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች የቀረበ
ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያላቸው የአሁኑ ኮንትራት የሚጠናቀቀው በጁን 2017 ቢሆንም በዘንድሮ ሲዝን ለቡድኑ ከሚጠበቅባቸው ያነሰ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በመገደባቸው ግን የኮንትራት ውላቸው ከማለቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ከኦልድትራፎርድ ሥራ የመነሳታቸው ተስፋ እየሰፋ በመምጣት ላይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ የእግርኳስ ተንታኞች በማንሳት ላይ ያሉት ጥያቄም ሉዊ ቫንሃል ተከትለው ከዘንድሮ ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ኦልድትራፎርድን የሚለቁት በክለቡ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾች እነማን ይሆናሉ የሚል ነው፡፡
ቫንሃልን በመተካት የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝነት ስራን በሚረከቡት በጆሴ ሞውሪኖ ወይም በሌላ ባለሙያ ስር እነማንስ የክለቡ አቅድ አካል ሆነው የመዝለቅ እድል ይኖራቸዋል? የሚለውም ሌላ በመነሳት ላይ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የዴይሊ ሜይል የእግርኳስ ተንታኞች በማንችስተር ዩናይትድ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾችን ወቅታዊ አቋምን በመገምገም ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ክለብን የሚለቁትና ለተጨማሪ ዓመታት የማንችስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆነው መዝለቅ የሚገባቸው ተጨዋቾችን ማንነትን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡
መቆየት የሚገባቸው
- ዴቪድ ዳሂአ
ባለፈው ሴፕቴምበር ወር ማንቸስተር ዩናይትድ የቀረበለትን አዲስ ለተጨማሪ አራት ዓመታት የሚዘልቅ ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ፈርሟል፡፡ ከዛ ወዲህ የወደፊት እጣ ፈንታውን በተመለከተ የተፈጠረበት ምንም አይነት ውዝግብ ባለመኖሩ የዳሂአ የማንቸስተር ዩናይትድ በርን ለተጨማሪ ዓመታት አጠራጣሪ አይመስልም፡፡ ክለቡ ለዳሂአ ከስፖንሰርሺፕ ውሎቹ የተወሰነ ፐርሰንት ገቢን ሊፈጥርለት ማቀዱም ስፔናዊው ግብ ጠባቂን ደስተኛ አድርጎት በኦልድትራፎርድ እንደሚቆየው ይጠበቃል፡፡
2. ማቲዬ ደርሚን
የዘንድሮ ሲዝን ከመጋመሱ በፊት በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የነበረውን ደካማ አቋማችን በማረም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሩ አቋም ለመገኘት ችሏል፡፡ በተለይም ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርቡ በቼልሲና ከሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ያበረከተው ታላቅ ፐርፎርማንስን የጣሊያናዊው ኢንተርናሽናል በሂደት በእንግሊዝ ፉትቦል የጨዋታ ስታይል ጋር በተገቢው መልኩ ለማዋሃድ ለመቻሉ በቂ ማስረጃ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ደርሚንን ለበርካታ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ ቀኝ ተመላላሽ ሚና የመጀመሪያው ተመራጭ ተጨዋች ሆኖ እንደሚዘልቅ ይጠበቃል፡፡
3. ሉክ ሻው
የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ ግራ ተመላላሽ የዘንድሮን ሲዝንን በጥሩ አቋም ሆኖ ለመክፈት ቢችልም በሴፕቴምበር ወር ከፒኤስቪ አይንደሆቨን ጋር በተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ዝግጅት ግጥሚያ ያጋጠመው አደገኛ የእግር ስብራት ለበርካታ ወራት ከሜዳ ለመራቅ እንዲገደድ አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከጉዳቱ ለማገገም በማድረግ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥረት ስኬታማ ሆኖለት በሲዝኑ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሜዳ ለመመለስ ይችላል በሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡
በጥሩ ጤንነት ላይ በሚገኝበት ወቅት ከማንቸስተር ዩናይትድ ባሻገር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር አለኝታ ሆኖ ለበርካታ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ የሰፋ በመሆኑም በክለቡ በጭራሽ ሊለቀቅ የማይችል ተጨዋች እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም፡፡
4. ካሜሮን በርዝዊክ ጃክሰን
በዘንድሮው ሲዝን ከሉዊ ቫንሃል ጥቂት ተደናቂ ተግባሮች ውስጥ የ18 ዓመቱ ወጣት የግራ ተመላላሽን ከማንቸስተር ዩናይትድ ወጣት ቡድን ወደ ዋናው ለማሳደግ የደረሱበት ቆራጥ ውሳኔያቸው በሮዝዊክ ከወዲሁ ለዋናው ቡድን በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ተደናቂ ብቃቱን በማሳየት ማንቸስተር ዩናይትድ ለዘለቄታው የአስተማማኝ ግራ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶች እጥረት እንደማይኖርበት ለማስመስከር የቻለ ሆኗል፡፡
5. ፊል ጆንስ
ከዚህ በፊት ማንቸስተር በሪዮ ፊርዲናንድና በኔማኒያ ቪዲች አማካይነት የነበረውን ጠንካራ የመሃል ተከላካይ ክፍል ጥምረትን ሁለቱ እንግሊዛዊያን ክሪስ ስሞሊንግና ፊል ጆንስ በአግባ ለመመለስ ይችላሉ የሚል እምነት በበርካታዎች ዘንድ ተፈጥሮ ዘልቋል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን ይህ እምነት በአግባቡ ተግባራዊ እንዳይሆን በፊል ጆንስ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጉዳት የበኩሉን ተፅዕኖን የፈጠረ ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን ጆንስ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል አጋማሽ የሚገኝ ተጨዋች በመሆኑ የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ ለተጨማሪ ዓመታት የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
6. ክሪስ ስሞሊንግ
ከዚህ በፊት በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር ሳይቀር ብዙ ተለፍቶበት የተረጋጋ አቋምን ለመያዝ ሲቸገር ታይቷል፡፡ በሉዊ ቫንሃል ስር ግን የማንቸስተር ዩናይትድ የተዋጣለት የመሀል ተከላካይ ሚና ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር የቻለበት ተደናቂ ፐርፎርማስን መላበስ ችሏል፡፡ በተለይም የእስካሁኑ ሲዝን የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ምርጡ ተጨዋች ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድ ልዩ ትኩረት ስሞሊንግ ጎን ትክክለኛውን ጥምረትን ለመፍጠር የሚችል ተጨዋችን ለማግኘት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
7. ዳሊን ብሊንድ
የዘንድሮው ሲዝን በአብዛኛው ግጥሚያ ለማንቸስተር ዩናይትድ የተሰለፈበት በተከላካይ መስመር ነው፡፡ ሉዊ ቫንሃ ሆላንዳዊው ኢንተርናሽናል ከአማካይ ክፍል ይልቅ በመሀል ተከላካይ ሚና እንዲጠቀሙበት በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት የሆናቸው በስኳዳቸው የሚገኙት በርካታ የተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን በጉት ሳቢያ ከሜዳ ለመራቅ መገደዳቸው ነው፡፡ ይህን የሚያሳየው የብሊንድ የተለያዩ የጨዋታ ሚናዎች የመሰለፍ ሁለገብ ብቃትን ማንቸስተር ዩናይትደ በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ሊያገኘው አጥብቆ የሚመኘው መሆኑን ነው፡፡
8. ማይክል ካሪክ
ካለፉት ዓመታት አንፃር የእንግሊዛዊው አማካይ የዘንድሮ ሲዝን አቋም ጥሩ የሚባል ባይሆንም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን የዕድሜው መግፋት ምንም አይነት ተፅዕኖን ሳይፈጥርበት በቦታው ላይ የወትሮውን ጥሩ አቋሙን የሚያስታውሰው ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ነው፡፡ ይህ እውነታ ከግንዛቤ ሲገባም ማንቸስተር ዩናይትድ የተጨማሪ 12 ወራት የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ሊፈቅዱለት ማቀዱ ማስታወቁ አስገራሚ ሊሆን አይችልም፡፡
9. ሞርጋን ሽኔደርሊን
ፈረንሳዊው አማካይ በቀድሞ ክለቡ ሳውዝአምፕተን የነበረው ታላቅ ፐርፎርማንስን በእስካሁኑ ሲዝን ለመድገም ችሏል ባይባልም በመሀል አማካይ ክፍል ትክክለኛው አማራጭ ተጨዋች የሚያገኝ ከሆነ ግን በቦታው ላይ የማንቸስተር ዩናይትድ አስተማማኝ አለኝታ ሆኖ እንደሚዘልቅ ይታመናል፡፡
ሸኔደርሰሊን ከሲዝኑ መጋመስ ወዲህ የያዘው ጥሩ አቋም መሆን ቀስ በቀስ የማንቸስተር ዩናይትድ የመሀል አማካይን በበላይነት ለመምራት የሚያስችለውን አስተማማኝ ብቃት እንደሚኖረው የሚጠቁም ሆኗል፡፡
10. አንደር ሄሬራ
በሉዊ ቫንሃል ስር ብዛት ያላቸው ግጥሚያዎች ተከታታይነት ባለው መልኩ የመሰለፍ ዕድል ባይሰጠውም አልፎ አልፎ በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ግን ውጤታማ ፉትቦልን ሲያበረክት መታየቱ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ስፔናዊው አማካይ የኦልድትራፎርድ ስራ በትክክለኛው ባለሙያ የሚያዝ ከሆነ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት የሚዘልቅበት ተስፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
11. አሽሊ ያንግ
በሉዊ ቫንሃል ስር ከዚህ በፊት የነበራቸው ብቃትን አሳድገው ከተገኙት የማንቸስተር ዩናይትድ ስኳድ አባላት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በተለይም ሆላንዳዊው አሰልጣኝ አሽ ያንግ በተፈጥሮ ከያዘው በማጥቃት ላይ ያተኮረ የክንፍ ሚናው ባሻገር ወደኋላ ተመልሶ የመከላከል ተግባርን የሚፈፅምበትን አዲስ የጨዋታ ሚናን አስገኝተውለት ሁለገብ ብቃቱን አሳድገውለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ያንግ ለተጨማሪ ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ እቅድ አካል ሆኖ የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
12. ሜምፌስ ዴፖይ
ባለፈው ሲዝን ፒኤስቪ አይንደንሆቨንን ለሆላንድ ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር እንዲበቃ ያበረከተው ቁልፍ አስተዋፅኦን በእስካሁኑ ሲዝን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለመድገም አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ዴፖይ ውጤታማ ፉትቦሉን በሜዳ ላይ ለማውጣት እንዲችል በሚረዳውን ትክክለኛ አሰልጣኝን ለማግኘት ከቻለ የማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ ለመዝለቅ የሚችልባቸውን ሁሉንም አይነት ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡
ክለቡን መልቀቅ ያለባቸው
5. ማርኮስ ሮሆ
የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ጥሩ የኳስ ስኬል ችሎታን ስኬታማ ታክሎችን የመግባት ብቃት ያለው ቢሆንም በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ ግን ከትኩረት ማነስ ችግር በመነጨ ስህቶችን ሲፈፅም መታየቱ የተለመደ ባህሉ ነው፡፡ አልፎ አልፎም አስፈላጊው ፋውሎችን በመፈፀም ቡድኑን የሚጎዳበት ባህል ያለው መሆኑ ከግንዛቤ ሲገባም በክለቡ ውስጥ የሚገባው ተጨዋች ነው፡፡
4. ባስቲያን ሽዌንስቲገር
ሉዊ ቫንሃል ጀርመናዊው ልምድ ያካበተ የመሃል አማካይን ለመግዛት የወሰነበት ተግባራቸው መጥፎ ሃሳብ ተደርጎ ሊቆጠር የሚገባው ቢሆን በእንግሊዝ ፉትቦል መሳተፍ የጀመረው ግን ዕድሜው 31 ከደረሰ በኋላ በመሆኑ ማንቸስተር ዩናይትድ በትክክለኛው ወቅት ላይ አላገኘውም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ አንፃር ሽዌንስቲቨር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ወደ ሜጀር ሊግ ስኮር ውድድር ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
3. ማሮዋን ፊላኒ
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽልን ያስፈረሙት ሁለገብ የአማካይ ክፍልና የአጥቂ መስመር ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ ተጨዋች መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባታቸው ቢሆንም የያዘው ብቃት ግን የማንቸስተር ዩናይትድ ትልቅ ስታንዳርድን በበቂ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አልተገኘም፡፡ ከዚህ አንፃር ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሚጠበቀው እጣ ፈንታ በማንቸስተር ዩናይትድ ለሽያጭ መቅረብ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
2. አንቶኒዮ ቫሌንስያ
በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስር የነበረው ውጤታማ ብቃቱን ቀስ በቀስ በማጣት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ኮርሶችን በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎች ላይ በመደረብ ራሱን የቻለ መጥፎ ሪከርድን ይዞ ዘልቋል፡፡ ከዚህ አንፃር ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚኖረው የፉትቦል ህይወት ወደማክተሙ ደረጃ ተቃሯል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
- አድናይ ያንዩዣይ
በመላው አውሮፓ ተደናቂ ብቃትን የተላበሰው በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙት ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑ ቢታመንበትም የሉዊ ቫንሃል እቅድ አካል ለመሆን ተስኖታል፡፡ እስከ ዘንድሮው ሲዝን መጋመስ ድረስ በቦሪሽያ ዶርትሙንድ ያደረገው የውሰት ውል ቆይታውም ተደናቂ ስኬት ሊታጀብለት አልቻለም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንቸስተር ዩናይትድን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ያንዩዣይን በጥሩ ዋጋ ለሌላ ክለብ የመሸጥ ውሳኔ ላይ መድረስ ነው፡፡ ያንዩዣይ በቅርበት የሚያውቁት አስተያየት ሰጪዎች ተጨዋቹ በዘንድሮ ሲዝን መጀመሪያ ላይ ከሉዊ ቫንሃል እቅድ ውጪ መሆኑ ተነግሮት በማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ከተለቀቀ ወዲህ በትክክለኛው የስነ ልቦና ጥንካሬ ደረጃ ላይ ለመገኘት ተስኖታል፡፡
The post Sport: በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ 12 መቆየትና 5 መባረር ያለባቸው ተጨዋቾች appeared first on Zehabesha Amharic.