ስፔናዊው ግራ ተመላላሽ ናቾ ሞንሪል በጃንዋሪው 2013 በአርሰናሉ አርሴን ቬንገር ከማላጋ ክለብ የተገዛው በቡድናቸው የግራ ተመላላሽ ሚና የመጀመሪያው ተመራጭ ለነበረው ኬራን ጊብስ ትክክለኛው ሽፋንን ለመስጠት የሚችልበት ብቃትን ተላብሷል በሚል ታምኖበት ነበር፡፡ በአርሰናል የፈረመበት የመጀመሪያው ዓመትን ያጠናቀቀው ከእንግሊዝ ፉትቦል የጨዋታ ስታይል ጋር በአግባቡ ለመላመድ ጥረትን ለማድረግ ተገድቦ ቢሆንም ቀስ በቀስ አርሰናል የመጀመሪያ ተመራጭ ተጨዋች መሆን ችሏል፡፡
የሞንሪል የአርሰናል መፈረምን ተከትሎም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ደጋፊዎች በድፍን ዘጠኝ ዓመታት የዘለቀው የዋንጫ ሽልማት ጉጉታቸውን ለመቅረፍ ያለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት የኤፍ.ኤ ካፕ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት አርሰናል የዘንድሮው ሲዝንን ከ3ኛ ጊዜ በተከታታይ የኤፍ.ኤ.ካፕ የዋንጫ ድልን በመቀዳጀት በውድድሩ ታሪክ ብቸኛው ክለብ የመሆን ታሪክን ለመስራት ከመጓጓት አልፎ ከ2004 የዘለቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ናፍቆቱን የመቅረፍ አላማን እንዲይዝ በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት የሆነ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ላይ ከሚገኙለት ተጨዋቾችም ውስጥ አንዱ ናቾ ሞንሪል ነው፡፡
ምክንያቱም በዘንድሮው ሲዝን በእያንዳንዱ የአርሰናል ግጥሚያዎች ላይ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት የቡድኑ የግራ መስመር እጅግ ጠንካራ ሆኖ እንዲዘልቅ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ አስተዋፅኦን ለማበርከት ችሏል፡፡ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም አርሴን ቬንገር ሰሞኑን ለሞንሪል ከክለባቸው ጋር ለተጨማሪ ዓመታት የሚዘልቅበትን አዲስ ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ፈቅደውለታል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ፈረንሳዊው አሰልጣኝ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሰነዘሩት አስተያየትም ናቾ ሞንሪልን በስኳዳቸው በሚያገኙት በእያንዳንዱ የቡድናቸው ተጨዋቾች በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀር ተጨዋች ነው በማለት ገልፀውታል፡፡
ሞንሪል በአሁኑ ወቅት በስኳዳችን ከሚገኙትና ከቡድናችን እጅግ ከፍተኛ ወሳኝነት ካላቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑን መጠራጠር በፍፁም አያሻም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ያካበተው ሰፊ ልምድን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ የቡድናችን ተጨዋቾች እንደ ትልቅ አርአያቸው የሚቆጥሩና በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀሩት ተጨዋች መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ›› በማለት በስፔናዊው ግራ ተመላላሽ ዙሪያ መግለጫቸውን መስጠት የጀመሩት አርሴን ቬንገር በመቀጠልም ‹‹በቡድናችን በዘንድሮው ሲዝን በግራ መስመሩ ካለፉት ዓመታት በብዙ መልኩ የተሻለ የተረጋጋ ጥሩ አቋም እንዲኖው ግንባር ቀደሙን አስተዋፅኦን ያበረከተው በመሆኑ የተፈቀደለት አዲስ የኮንትራት ማራዘሚያን ውል በትክክልም በሚመጥነው መሆኑን አምናለሁ›› የሚል አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡
ሞንሪል በእስካሁኑ ሲዝን የያዘው የማይዋዥቅ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ከአርሰናል መደበኛ ቋሚ ተሰላፊዎች ውስጥ የያዛቸው ብቃት አስፈላጊው ከበሬታን ያላገኘለት ተጨዋች ነው በማለት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ አመለካከት ዙሪያ አርሴን ቬንገር አስተያየታቸውን የሰነዘሩት ‹‹እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የሌሎቹ ተቀናቃኞቻችን ክለቦች አባላትም የሞንሪል የተዋጣለት የግራ መስመር ተመላላሽ ሚና ባለቤት መሆንን በአግባ የተረዱበት የውድድር ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ ማንኛውም አስተያየት ሰጪ ቢሆን ሞንሪልን ፍፁም እንከን የማይወጣለት ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ባህሉ ያደረገበት የውድድር ዘመንን በማሳለፍ ላይ መሆኑን ሊመሰክርለት ይችላል፡፡ ከግራ ተመላላሽ ሚና ባሻገር አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት በመሀል ተከላካይ ክፍል በመሰለፍ ለቡድናችን ተጨማሪ ትልቅ ኃላፊነትን የሚፈፅምልን ተጨዋች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእያንዳንዱ ግጥሚያ የሚሰጠውን ኃላፊነትን ለመፈፀም 100 ፐርሰንት ጥረትን የማድረግ ባህሉ ለሌሎች የቡድናችን ተጨዋቾች በትልቅ አርአያነት የሚጠቀስለት ባህሉ ነው፡፡
በአቡኑ ወቅት ቡድናችን በሞንሪልና በኬራን ጊብስ አማካይነት ሁለት ወርልድ ክላስ የግራ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶችን መያዙም እድለኛ እንደሀነ ያህል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሚገኙት አብዛኛዎቹ ክለቦች ከዚህ ቦታ ላይ መሰረታዊና ያለው የመሳሳት ችግር በግልፅ በመታየት ላይ ነው፡፡ ከዚህ መልካም አጋጣሚያችን በአግባቡ ተጠቃሚ በመሆን የዘንድሮው ሲዝንን በምንሳተፍባቸው ውድድሮች ሁሉ መልካም ውጤቶችን በማስመዝገብ ለማጠናቀቅ የማናልምበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል፡፡
ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ግራ ተመላላሽ በበኩሉ አርሰናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንካራ አቋምን በመያዝ በአሁኑ ወቅት የፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥን በመምራት ላይ ካለው ሊስተር ሲቲ የሁለት ነጥቦች ልዩነት በማነስ የሻምፒዮንነት ፉክክሩ ዋነኛ ተዋናይ የሆነው አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ሳይበታተኑ አብረው ብዛት ባላቸው ግጥሚያዎች ላይ የመሰለፍ እድልን ማግኘታቸው መሆኑን ያመነበት መግለጫን ከትናንት በስቲያ ሰጥቷል፡፡
አርሴን ቬንገር ባለፉት ሁለት ተከታታይ የዝውውር መስኮቶች ከአርሰናል አዲስ ያስፈረሟቸው ተጨዋቾች ፒተር ቺክና መሐመድ አልኔኒይ ብቻ መሆናቸውን በማስገንዘብ ሞንሪል መግለጫውን የሰጠው ‹‹በእኔ አመለካከት በስኳዳችን የሚገኙት አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ከሁለትና ከሶስት ዓመታት በላይ በበርካታ ግጥሚያዎች ላይ አብረው የመሰለፍ እድልን ያገኙ መሆናቸው በመሃላቸው እጅግ ተደናቂ ህብረት እንዲፈጠር የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦን አበርክተውልኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመሃላችን ያለው ህብረትም እጅግ ጠንካራ ነው፡፡ በሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሜዳው ውጪም አብዛኛውን ጊዜያችንን አብረን ማሳለፋችን በመሀላችን ያለው የእርስ በርስ መፈቃቀር ከፍተኛነትን የማያንፀባርቅ ነው፡፡
ለአንድ ቡድን የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት እንዲችል ትልቅ አስተዋፅኦን የሚያበረክትለት ጉዳይ ደግሞ በቡድኑ ካምፕ የሚኖረው ህብረት ያማረ መሆን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህንን ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ክራይቴሪያን በተሟላ ሁኔታ ለመያዝ ችለናል የሚል እምነት አለኝ›› በማለት ነው፡፡ የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በእያንዳንዱ የዝውውር መስኮት ከአንድ ወይም ከሁለት የማይበልጡ አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረምን በቅርቡ ዓመታት ውስጥ የተለመደ ባህላቸው ማድረጋቸው የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦን እንዳበረከተላቸው በማመን ሞንሪል በመቀጠል የሰጠው መግለጫ ‹‹…አርሰናል በ11 ተጨዋቾች ክለብ በቻ አይደለም በዋናው ቡድናችን ስኳድ የሚገኙት ሁለት 24 ተጨዋቾች አንዳንድ ህብረትን በመፍጠር ተደናቂ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረትን የሚያደርጉበት ህብረቱና አጠቃላዩ ቅንጅቱ ያማረ ክለብ ነው፡፡ ለዚህ የረዳን ደግሞ በእያንዳንዱ የዝውውር መስኮት ከአንድ የማይበልጥ አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረማችንን የተለመደ ባህላችንን ማድረጋችን መሆኑን አምናለሁ፡፡ ለዚህ ክለብ ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶም በስኳዳችን ያለው ህብረትን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ለመምጣት ምስክርነቱን መስጠት እችላለሁ፡፡ አብዛኛዎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች ከሁለት ዓመታት በላይ አብረን የመጫወት እድልን በማግኘታችንም በመሃላችን ያለው አጠቃላዩ ቅንጅትና የጨዋታ እንቅስቃሴ መናበብ ይበልጥ እያማረ ሊሄድልን ይችላል›› በማለት ነው፡፡
The post Sport: ናቾ ሞንሪያል – የመድፈኞቹ እጅግ ተፈቃሪው ተጨዋች appeared first on Zehabesha Amharic.