Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: ብዙ ያልተባለለት የሌስተር ሲቲው ጀግና ‹‹የማኬሌሊ ሙያን መመለስ ችሏል›› ጋሬዝ ኩክ

$
0
0

 

በዘንድሮው ሲዝን ሌስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዘመቻው የመሪነቱ ስፍራ ለመቀመጥ እንዲችል በግንባር ቀደምትነት በብዙዎች በመጠቀስ ላይ የሚገኙት የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋቾች እንግሊዛዊው አጥቂ ጃሚ ቨርዲና አልጄሪያዊው ኢንተርናሽናል ራሂድ ማህሬዝ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ተጨዋቾች በእስካሁኑ የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንዲቀመጥ ያስቻሉት ቁልፍ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
lecter cite N'golo Kante

በዛኑ መጠን ግን በቡድኑ የመሃል አማካይ ክፍል ተጨዋቾች የሆኑት ንጎሎ ካንቴና ዳ ድሪንክዋተር በእስካሁኑ ሲዝን ብዙ ያልተዘመረላቸው የሌስተር ሲቲ ጥንካሬ መሰረታዊ ምንጭ መሆናቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጣሊያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒየሪ ቡድን ባደረጋቸው ተከታታይ ጠንካራ ግጥሚያዎች ላይ ባሳዩት የማይዋዥቅ ታላላቅ ፐርፎርማንሳቸው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በተለይም ሌስተር ሲቲ ባለፈው በኢምሬትስ ስቴዲየም ያደረገውን የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያን 2ለ1 በሆነ ውጤት ለመሸነፍ ቢገደድም የ24 ዓመቱ የፈረንሳይ በመሀል አማካይ ክፍል በርካታ የአርሰናል የማጥቃት እንቅስቃሴን የማጨናገፉን በሜዳ ላይ ከነበሩት የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ብዛት ያላቸው ስኬታማ ታክሎን በመግባት ሲታወስ የሚኖር ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡

ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም የአርሰናሉ ዝነኛ ጎል አዳኝ ቲዮሪ ኦንሪ በሰነዘረው አስተያየት ሊስተር ሲቲ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ በተቆጠረበት ጎል 2ለ1 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ ቢገደድም የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች የምለው ንጎሎ ኮንቴን ነው፡፡ ምክንያቱም በሌስተር ሲቲ የተከላካይ መስመር ላይ ሲፈጠር የታየው ጫናን በአግባቡ በመቀነስ እጅግ ምርጥ ብቃት ያለው የሆልዲንግ ሚድል ሚና ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር ችሏል፡፡ በእኔ አመለካከት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቦታው ላይ በምርጥ ብቃቱ አቻ የማይገኝለት ተጨዋች ነው በማለት አድንቆታል፡፡

ክላውዲዮ ራኒየሪ የዘንድሮው ሲዝን ከመጀመሩ በፊት ከፈረንሳዩ ኪን ክለብ 5.6 ሚሊየን ፓውንድ የገዙት ንጎሎ ካንቴን ከዚህ በፊት የቼልሲና የሪያል ማድሪድ የነበረው ክሎድ ማኬሌሌን የጨዋታ ሚናው ለበርካታ ዓመታት በኋላ እንዳስታወሰው ምክንያት የሆነኝ ተጨዋች ነው በሚል የገለፀው ደግሞ የቢቢሲው የፉትቦል ተንታኝ ጋሬዝ ሉክ ነው፡፡ ‹‹ሌስተር ሲቲ በጨዋታው 54ኛው ደቂቃ ላይ ዳኒ ሴምፕሰን በቀይ ካርድ ባያጣው ኖሮ እንደ ንጎሎ ሳንቲ አስገራሚ የመሀል አማካይ ክፍል ተደናቂ ብቃት ግጥሚያውን ቢያነሳ ነጥብ በመጋራት ለማጠናቀቅ በተከገባው ነበር›› ያለው ጋሬሬ ሉክ በመቀጠል ‹‹ሳንቴ ለበርካታ ዓመታት በኋላ የክሎድ ማኬሌሊ የጨዋታ ሚና በማለት የምንገልፀው አጨዋወትን ወደ እንግሊዝ ፉትቦል ለመመለስ የቻለ ተጨዋች ነው፡፡ በእኔ አመለካከትም በእስካሁኑ ሲዝን ብዙ ያልተዘመረለት የሌስተር ሲቲ ትልቁ የአማካይ ክፍል ጀግና ነው›› በማለት የ24 ዓመቱ ‹‹ሌስተር ሲቲ ቁልፍ የመሃል አማካይን ገልፆታል፡፡

ሳንቲ በዘንድሮው ሲዝን በእያንዳንዱ የሌስተር ሲቲ ግጥሚያዎች በመከላከል ላይ ያተኮረ ተደናቂ ተግባር የአማካይ ክፍል ተግባርን መፈፀም መቻሉ የዘመናዊ ፉትቦል የማኬሌሊ የጨዋታ ሚና ለምን እየተረሳ መጣ የሚለውን አጀንዳን ያስነሳ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የኤ.ኤስ.ፒ.ኤን የፉትቦል ተንታኞች ከዚህ በታች ያለውን ሙያዊ ትንተናቸውን አስነብበዋል፡፡ የሪያል ማድሪድ ፕሬሬዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በ2003 ክሎድ ማኬሌሊን ለቼልሲ የሸጡበት ምክንያትን ያብራሩት ‹‹የኳስ ቁጥጥር ለእግሩ በመቆየት ከሶስት ሜትሮች በላይ ለመጓዝ አይችልም፡፡ በማጥቃቱ እንቅስቃሴ ምንም አይነት ተሳትፎ የሌለው ተጨዋች ነው፡፡ ክለባችን ወጣት ተጨዋቾችን በማሳደጉም የማኬሌሊ ማንነት ሙሉ ለሙሉ መረሳቱ የማይቀር ነው›› በማለት ነበር፡፡ ፔሬዝ ይህንን በማለታቸው ግን አንድ መሰረታዊ  የሆነ ነገር ሙሉ ለሙሉ ከአይምሯቸው አስወጥተውታል ለማለት ይቻላል፡፡

kante

የማኬሌሊ የሪያል ማድሪድ ጓደኛ የነበረው የቀድሞው የእንግሊዝ ኢንተርናሽናል ስቲቭ ማክማነመን ግን ፍሎንቲኖ ፔሬዝ ስለፈረንሳዊው አማካይ ትልቅ ግልጋሎት ያልተረዱትን ነገር ቁልጭ አድርጎ አሳይቷቸዋል፡፡ በተለይም ማክማነመን የግል ህይወቱን በያዘው መፅሐፍ ማኬሌሊ ለሪያል ማድሪድ ያለው ከማንም የቡድኑ ተሰላፊ በብዙ መልክ የተሻለ ወሳኝነት ከክለባቸው ውጪ ያሉት ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እውቅናን ሊያገኝ አለመቻሉን በዝርዝር አብራርቶታል፡፡

ማክናመነን በዛ መፅሐፉ ‹‹የሪያል ማድሪድ የመጀመሪያው ምዕራፍ የጋላታክቲኮስ ዘመን ሙሉ ለሙሉ ማክተም የጀመረው ከማኬሌሊ ወደ ቼልሲ ዝውውር ከማድረግ ጋር በተያያዘ ነው›› እስከማለት ደረጃ ደርሷል፡፡ ማክማነመን ካኬሌሊ ለሪያል ማድሪድ የነበረው ወሳኝነት በማሳየት በማብራሪያው በአስቶባዮግራፊው ላይ ያስነበበው››

የሪያል ማድሪድ የጋላክቲኮስ ፍልስፍና የሚገለፀው በበርካታ በማጥቃት ላይ ያተኮረ አይምሮን በተላበሱት ተጨዋቾች መሆኑን አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ለጋላክቲኮስ ፍልስፍና በዋነኝነት የሚጠቀስ መሰረት የሆነው በቡድኑ የመሃል አማካይ የመመላከል ሽፋንን የሚሰጥለት ክሎድ ማኬሊሊ ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በመፈፀም የሪያል ማድሪድ እጅግ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ ዘልቋል፡፡ ሆኖም ግን በርካታ ሰዎች ይልቅ ቁልፍ ሚናውን ዘንግተውታል፡፡ አብረነው የምንሰለፍበት ተጨዋች ብቻ ሪያል ማድሪድ ስለማኬሌሊ ጥርስ የሌለው አንበሳ እንዲሆን እናውቅ ነበር፡፡

በዛን ወቅት ከማኬሌሊ ጋር የሪያል ማድሪድ የተሰለፉበት እያንዳንዱ ተጨዋቾችም ብትጤቃቸው የሚነግሯችሁ ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን የቡድኑ ጓደኞች ቁልፍ ተጨዋቾቻችንን በሃዘን ታጅበን በሄደበት መልካም ነገሮች እንዲገጥሙት በመመኘት ከመሸኘት በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበረውም፡፡

የማኬሌሊ በጁላይ 2003 ሪያል ማድሪድን መልቀቅ የፔሬዝ የጋላክቲኮስ ፍልስፍና መፈረካከስን በይፋ ያስጀመረው ሆኗል፡፡ በአንፃሩ ግን የማኬሌሊ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስ የቼልሲ ወደ ወርቃማ ዘመን የመግባትን የመጀመሪያውን ምዕራፍን አስጀምሮታል›› በማለት ነው፡፡

ፈረንሳዊው የዓለም ፉትቦል የምንጊዜውም ዝነኛ ዚነዲን ዚዳንም ይህንን የማክማነመን አባባልን በማጠናከር በሰነዘረው አስተያየት በ2003 ፕሪ ሲዝን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ማኬሌሊን ለቼልሲ በመሸጥ ዴቪ ቤካምን ከማንቸስተር ዩናይትድ በ25 ሚሊየን ፓውንድ የገዙበት ተግባራቸውን ተኝቶት ነበር፡፡ ዚዙ በወቅቱ በፔሬዝ ሌላ የማጥቃት አዕምሮን የተላበሰ ተጨዋች በማኬሌሊ ምትክ ያስፈረሙበት ተግባራቸው ለቡድናቸው በሜዳ ላይ የሚኖረውን ጠቀሜታን በመጠራጠር አስተያየቱን ሰጥቶ የነበረው ‹‹…ቤንትሌይ ሞዴል ያላት መኪናህን ሞተር ነቅለህ ከወጣኸው በኋላ የመኪናዋ ሽፋንን በወርቅ ማልበስህ ጠቀሜታው ምንድነው በሚል ነበር ፔሬዝ ወዲያውኑ ይህንን የዚዳን አባባልን በማጣጣል በሰነዘሩት አስተያየት ለማኬሌሊ ደመወዝ ስንከፍል የቆየንበት ምክንያት ምን እንደሆነ በትክክል ለመረዳት ተችግሬያለሁ›› ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ዚዳን የጋላክቲኮስ ፍልስፍናቸው መሪ ተዋናይ በመሆኑ በትችት አዘሉ አባባሉ ቂምን ሊይዙበት አልፈለጉም፡፡ ፔሬዝና በስራቸው የነበሩት የሪያል ማድሪድ አመራሮች እንደ ማኬሌሊ ያለ የአማካይ ክፍል ‹‹ዲስትሮዬርስ›› በቡድናቸው ቋሚ አሰላለፍ ማየት አጥብቀው የተጠየፉበት ወቅት እንደነበር በማስታወስ የቶተንሃም ሆትስበርስ ኮቺንግ ስታፍ አባል ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የአጥቂ መስመር ተጨዋች ሌስ ፈረንዲናንድ በቅርቡ በሰነዘረው አስተያየት ፔሬዝ በማኬሌሊ ሚና የነበራቸው ጥላቻን ከመቃወም ይልቅ ፈረንሳዊው ዝነኛ የተጋጣሚ ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴን በማላሸት ላይ ሙሉ ትኩረትን ያደረገው የጨዋታ ሚናን በማቋሸሽ ‹‹በመጀመሪያውኑም ቢሆን ማኬሌሊ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመሳተፍ እድል ሊፈቀርት አይገባም ነበር፡፡ የዓለማችን እጅግ ተወዳጅ የሊግ ውድድራችን መቆሸሽ የጀመረው የጨዋታ ውበትን በማጥፋት ተግባር የተሰማራ ተጨዋች ለቼልሲ ከፈረመ በኋላ ነው፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት የፕሪሚየር ሊግ ካየኋቸው መጥፎ አጋጣሚዎች የማኬሌሊ በቼልሲ የመሃል አማካይ መሰለፍ ነው›› ብሎ ነበር፡፡

ሌስ ፈረንዲናንድ ይህንን ለማለት ያነሳሳው ለፈረንሳዊው አማካይ የግል ጥላቻን በማሳደር ሳይሆን የማኬሌሊ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስን ተከትሎ ከ2003 እስከ 2010 ድረስ ባሉት ዓመታት በመከላከል ላይ ያተኮረ ትኩረትን የሚያደርጉ የመሃል አማካዮች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንደ አሸን መፍላታቸውን በመታዘቡ ነው፡፡ ለሰባትና ስምንት ዓመታት በላይ በፕሪሚየር ሊግ ውድድር በብዛት የታዩትና ከራሳቸው ቡድን ሁለት የመሃል ተከላካዮች ፊት ለፊት የተጋጣሚ ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴን በእንጭጩ በማጨናገፍ ተግባር ከመሰማራት ውጪ የመሀል ሜዳውን መስመርን አቋርጠው የማለፍ ፍላጎት የሌላቸው የሆልዲንግ ሚድፊልደሮች በጠቅላላ ‹‹የማኬሌሊ ሚና›› ባለቤቶች የሚል ተቀፅላን ይዘው ዘልቀዋል፡፡ ይህንን በመታዘብም ሌስ ፈረንዲናንድ ከሁለትና ሶስት ዓመታት በፊት በተደጋጋሚ በስማቸው መግለጫዎች ጊዜው የአማካይ ክፍል ኢስትሮዬርስን የምናጠፋበት ሊሆን ይገባል›› የሚል ጥሪውን ለፕሪሚየር ሊግ መላው ቤተሰብ አስተላልፎ ነበር፡፡

‹‹ማኬሌሊ ሚና›› በዛን ወቅት የስኬታማነት የዓለም ቋንቋ መሆኑን የተረዱት ባለሙያዎች ግን በበቂ ሁኔታ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሬድ ሮም /የኢብራሂሞቪች/ አብዮት በቼልሲ የተቀጣጠለበት ድፍን አንድ ዓመት በኋላ በስታምፎርድ ብሪጅ ስራን ክላውድዮ በስታምፎርድ ብሪጅ ስራ ክላውዲዮ ራኒየሪ የተረከቡት ጆሴ ሞውሪኖ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ስር ከ2004-2007 ባሉት ዓመታት ጆን ቴና ሪካርዶ ካርቫልሆ ‹‹አይነኬ›› የቼልሲ የመሀል ተከላካይ ክፍል መደበኛ ቋሚ ተሰላፊዎቹ ሆነው ዘልቀዋል፡፡

ከቴሪና ከካርቫልሆነ አፍንጫ ስር አጭር ቁመት ያለው ፈረንሳዊው መታየቱ የሞውሪኖ ቼልሲ ቋሚ አሰላለፍ የተለመደ መግለጫ ነበር፡፡ ማኬሌሊ የተጋጣሚ ቡድን እያንዳንዱ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማጨናገፍ ዘመቻ በመሰማራት በቴሪና በካርቫልሆ የመከላከሉ ኃላፊነትን በግማሽ ይቀርፉላቸዋል፡፡ ከተጋጣሚ ቡድን ተሰላፊዎች በቅድሚያ ኳስን ማስጣል ከዛም ለራሱ ቡድን በማጥቃት ላይ ያተኮረ አማካዮች የፈገግታ መንፈስን በገፅታው ላይ ብልጭ በማድረግ አጭር ፓስን ማድረስ የያኔው የቼልሲ 16 ቁጥር አይነተኛው መገለጫ ነበር፡፡ በተለይም ሞውሪኖ 4-4-2 የጨዋታ ፎርሜሽን በሚጠበቀው ተጋጣሚ ቡድኖችን የማጥቃት እንቅስቃሴን ማጨናገፍ ማኬሌሊን በትክክለኛው መፍትሄቸው አድርገውታል፡፡

ምክንያቱም ፈረንሳዊው በተጋጣሚ ቡድን ሁለቱ የፊት አጥቂዎችና በአራቱ አማካዮች መካከል ባለው ቦታ እየገባ አርስ በርስ እንዲለያዩ የሚያደርግበት ኳስ በማጨናገፍ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ይሰማራል፡፡ በቻርልነተን አትሌቲኮ ተሰላፊዎች ዘመኑ ከቼልሲ ጋር በሚደረጉ ግጥሚያዎች ከማኬሌሊ ጋር በርካታ የአማካይ ክፍል ትግሎችን ሲያደርግ የዘለቀው ማት ሀላንድ የፈረንሳዊው አስቸጋሪ ተጋጣሚነትን በማንፀባረቅ በአንድ ወቅት መግለጫውን ሲሰጥ የተደመጠው ‹‹ቼልሲን በምንገጥምባቸው እያንዳንዱ የቡድናችን ትልቅ ራስ ምታት የሚሆነው ማኬሌሊ የጨዋታ እንቅስቃሴ መሆኑን አስታውሳለሁ፡፡

ምክንያቱም በቡድኑ የመከላከል ተግባር ጠልቆ በመግባት ይጫወታል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ከቼልሲ አራት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች አንዱ እስከመምሰል ደረጃ ይደርሳል፡፡ ቼልሲ በመጀመሪያው የሞውሪኖ የስራ ዘመኑ በጭራሽ የማይከፈት የመከላከል ስትራቴጂ የነበረው በማኬሌሊ ዋነኛ ተዋናይነት ነው ለማለት እችላለሁ፡፡ ይህንን በማየትም በእኔ የተጨዋችነት ዘመን የፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች በቡድናቸው የመሀል አማካይ ክፍል ቢያንስ አንድ የማኬሌሊ ሚና ባለቤትን መያዝን የውድ ግዴታ አድርገውት ነበር ለማለት እችላለሁ፡፡ ከማኬሌሊ ወደ እንግሊዝ ፉትቦል መምጣት በፊት የመከላከል ተግባርን በጥልቀት የሚፈጽም አማካይነት አልገጠምኩም፡፡

በእርግጥ የአስፒዎች ታውን ጅምማጊልተንም በቡድኑ የመሀል ተከላካይ ሚና ዘልቆ በመግባት ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ማጊልተን የኳስ ቁጥጥርን ካገኘ በኋላ ድሪብሊንግ የመሀል መስመሩን አቋርጦ በማለፍ የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ጭምር ይሳተፋል፡፡ ማኬሌሊ ግን የመሃል ሜዳ መስር ማቋረጥ ቀርቶ ሊያቀርበው አይመኝም በማለት ነው፡፡ በእርግጥ ራኒየሪ ፈረንሳዊውን ከሪያል ማድሪድ በመግዛት የማኬሌሊ ሚናን በእንግሊዝ ፉትቦል ካስተዋወቁት በኋላ ሌሎችም በሊጉ የሚገኙ አሰልጣኞች በቡድናቸው አማካይ ክፍል የጨዋታ እንቅስቃሴን ማበላሸት አላማው ያደረገ ተጨዋችን ማየትን ተመኝተዋል፡፡

ለምሳሌ ሊቨርፑል ሀቪየር ማስቺራኖ እንዲሁም ቶተንሃም ዴዲዬ ዛኮራን የገዙት ለቡድናቸው የማኬሌሊ ሚናን እንዲፈፅሙላቸው በመመኘት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የማራኪ ፉትቦል አቀንቃኝ ነኝ የሚሉት የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር አሌክስ ሶንግን በማኬሌሊ ሚና ለማሰማራት የወሰኑበት ጥቂት ዓመታት ታይተዋል፡፡ በአንፃሩ ቼልሲ በአንድ ማኬሌሊ ባለመገደብ በወጣትነት የዕድሜ ክልል እያለ በማጥቃት ላይ ያተኮረ የአማካይ ክፍል ሚና የነበረው ጆን አቢ ሚኬልን ወደ አማካይ ክፍል ኳስ አስጣይነት ሚና ቀይሮታል፡፡

አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንም ማንቸስተር ዩናይትድን የማኬሌሊ ሚና ባለቤት ለማድረግ ሲመኙ ታይተዋል፡፡ ነገር  ግን በዚህ ምኞታቸው ፍሬያማ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ማይክል ካሪክን በ2006 ፕሪሲዝን ከቶተንሃም ከገዙ በኋላ ለመረዳት ችለዋል፡፡ ፈርጉሰን እንግሊዛዊው አማካይን የገዙት የማኬሌሊ ሚናን እንዲፈፅምላቸው በማለም ነበር፡፡ ባሰቡትም መልኩ ካሪክን በሆልዲንግ ሚና ላይ ተጠቅመውበታል፡፡

ሆኖም ግን ካሪክ የኳስ ቁጥጥርን ከነጠቀ በኋላ እንደማኬሌሊ አጭር ፓስን ወደ አማካይ ክፍል ነካ በማድረግ የሚገደብ አይነት ተጨዋች ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡፡ ምክንያቱም ካሪክ በውጤታማ ረጅም ፓሶች ለአጥቂ መስመር ተሰላፊዎች የማድረስ ባህል ያለው ተጨዋች ነው፡፡ ፈርጉሰንም በካሪክ ሳይዛነፉና ተለክተው በሚላኩት ረጅም ፓሶች በመማረክ የማኬሌሊ ሚና ንድፍ ሃሳባቸውን ሙሉ ለሙሉ ከአይምሯቸው አስወጥተውታል፡፡

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles