ከደይሊ ሚረር ጋዜጣ ተተርጉሞ የቀረበ
ቼልሲ በዩሮ 2016 ውድድር መጠናቀቅ በኋላ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ላይ ያለው አንቶኒዮ ኮንቴን ለመቅጠር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ የቼልሲው ባለቤት ሮማን ኢብራሂሞቪች ለመቅጠር የወሰኑት ክለባቸውን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ለመመለስ እንደሚችል በማመን ነው፡፡
የ46 ዓመቱ የቀድሞው የጁቬንቱስ አሰልጣኝ ቼልሲን በመምራት 5ኛው ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት ጁያንሉካ ቪያላ፣ ክላውድዮ ራኒየሪ፣ ካርሎ አንቼሎቲ እና ሮቤርቶ ዲማቲዎ ሌሎቹ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በዋና አሰልጣንነት የመሩ ጣሊያናዊውን ባለሙያ ናቸው፡፡ ኮንቴ የዘንድሮው ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ የቼልሲ ስራን በሚጀምርበት ወቅት በምዕራብ ለንደኑ ክለብ እነማን ይዘልቃሉ ማንስ ክለቡን ይለቃል የሚለው ጉዳይ ከዚህ በታች ባለው መልኩ ተዳስሷል፡፡
ግብ ጠባቂዎች
ከክለቡ ጋር የሚዘልቁ
ቲቧ ኩርቷ
ቤልጅየማዊው ግብ ጠባቂ ከወዲሁ የሪያል ማድሪድ ልዩ ትኩረትን ስቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ካለው እውነታ ለመረዳት የሚቻለውም በክለቡ እንደሚቆይ ነው፡፡
አስሜር ቤጎቪች
የቼልሲ ሌሎቹ ግብ ጠባቂዎች በጉት ከሜዳ በሚርቁበት ወቅት በበቂ ግጥሚያዎች የመሰለፍ ዕድልን በማግኘት ዘልቋል፡፡ ከዚህ አንፃር በኮንቴ ስርም የኩርቷ ተጠባባቂ ሆኖ በስኳዱ የመዝለቁ ተስፋ የሰፋ ነው፡፡
ተከላካዮች
የሚቆይ
ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች
ሰርቪያዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች ባለፈው ጃንዋሪ ወር የአንድ ተጨማሪ ዓመት የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ተፈቅዶለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ኢቫኖቪች የቼልሲን የሚለቅበት ምንም አይነት ተስፋ አይኖረውም፡፡
ሴዛን አዝፕሌኩዌታ
ቼልሲ ኮንቴን በይፋ መሾሙን ከማረጋገጡ በፊት ኢዝፕሌኩዌታ ለቡድናቸው የወደፊቱ ትክክለኛው አሰልጣኝ ጣልያናዊው እንደሚሆን በይፋ ሲናገር ተደምጧል፡፡ ያንን መግለጫን የሰጠው የጣሊያንና በስፔን ብሔራዊ ቡድኖች በማርች ወር ካደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ ነበር፡፡ ያ መግለጫው ብቻ የኮንቴ እቅድ አካል እንደሚሆን የሚጠቁም ነው፡፡
የሚለቁ
ጆን ቴሪና ባባ ራህማን
የቴሪ በቼልሲ የኮንትራት ማራዘሚያ ሳይፈቅዱለት በመቅረታቸው ከወዲሁ ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ክለቡን በነፃ ዝውውር እንደሚለቅ ያረጋገጠበትን መግለጫን ሰጥቷል፡፡ የ21 ዓመቱ ራህማን በበኩሉ ለቼልሲ የተሰለፈበት የመጀመሪያ ሲዝኑን በማገባደድ ላይ ያለው ቡድኑን በከፍተኛ ደረጃ ለመጥቀም ተስኖት በመሆኑ በኮንቴ ስር ቦታ እንደማይኖረው ለመገመት አላስቸገረም፡፡
አማካዮች
የሚቆዩ
ሴስክ ፋብሪጋስ
በበርካታ ውጣ ውረዶች የታጀበ ሲዝንን ቢያሳልፍም አንቶኒዮ ኮንቴ ግን የቀጣዩ ሲዝን የቡድኑ ቁልፍ አካል ሊያደርጋቸው ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በተለይም ፋብሪጋስ በቅርቡ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ በኮንቴ ከተመራው የጣሊያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ ያሳየው ውጤታማ ፉትቦል በኮንቴ እንደታመነበት ምክንያት የሚሆነው ነው፡፡
ዊሊያን
ብራዚላዊው አማካይ በዘንድሮው ሲዝን ከሌላ ማንኛውም በቼልሲ ስኳድ ከሚገኝ ተጨዋቾች የተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት መቻሉ ከግንዛቤ ሊገባ አንቶኒዮ ኮንቴ በግንባር ቀደምነት የቡድኑ ቁልፍ አካል እንደሚያደርጉት ለመገመት አያስቸግርም፡፡
በርናንድ ትራኦሬ
የ20 ዓመቱ ወጣት በቼልሲና በጊዜያዊው ዋና አሰልጣኝ ጉስ ሂድንክ ስር በስምንት ግጥሚያዎች ላይ የመሰለፍ ዕድልን አግኝቶ ያለውን ተደናቂ ብቃት ማሳየቱ የኮንቴ እቅድ አካል እንዲሆን እንደሚረዳው ይታመናል፡፡ በስምንት ግጥሚያዎች ሁለት ጎሎችንም ለማስቆጠር ችሏል፡፡
ኬኔዲ
ሌላው የ20 ዓመት ወጣት ከቼልሲ የፉትቦል አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ከወዲሁ ለመሸጋገር ችሏል፡፡ የመሰለፍ ዕድልን ባገኘባቸው ጥቂት ግጥሚያዎች ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን ለማበርከት ሲችል በመታየቱም የአንቶኒዮ ኮንቴ ቁልፍ አካል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
እንደሚለቁ
የሚጠበቁ አጥቂዎች
ዲያጎ ኮስታ
ስፔናዊው ኢንተርናሽናል በእስካሁኑ ሲዝን በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር ኃላፊዎችና በፕሪሚየር ሊጉ ዳኞ የተደረገለት አያያዝ ደስተኛ እንዳላደረገው መናገሩ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አንቶኒዮ ኮንቴ ጥረቱ ስኬታማ ካልሆነ በስተቀር የኮስታና የቼልሲ የዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የመለያየት ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
ሌይክ ሬሚ
ፈረንሳዊው አጥቂ በጃንዋሪው የዝውውር መስኮት ለቀድሞ ክለቡ ኒውካስል ዩናይትድ በውሰት ውል ለመፈረም ተቃርቦ ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ሃሳቡን በመቀየር ከቼልሲ ጋር መቆየትን ምርጫው አድርጓል፡፡ ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ ግን በስታምፎርድ ብሪጅ የመቆየት ምንም አይነት ተስፋ አይኖረውም፡፡
አሌክሳንደር ፓቶ
ብራዚላዊው አጥቂ ኮሬንቲያስን በመልቀቅ ለቼልሲ ከፈረመ ወዲህ ለአዲሱ ክለቡ ለመለሰፍ የሁለት ወራተ ጊዜ ወስዶበታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቼልሲ በተሰፈለበት ግጥሚያ በአስቶንቪላ ላይ ጎልን ለማስቆጠር ቢችልም የአሁኑ የውሰት ውሉ ሲጠናቀቅ ግን ከቼልሲ ጋር መዝለቁ እጅግ አጠራጣሪ ነው፡፡
ራዳሚል ፉልካኦ
በአሁኑ ወቅት ከቼልሲ ጋር ያለው ኮንትራት በሲዝኑ መጨረሻ ላይ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ሌላ የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ማግኘቱ አጠራጣሪ ነው፡፡