ፖል ፖግባ በቂ የመሰለፍ ዕድል ባለማግኘቱ ከአሰልጣኝ ስር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኦልድ ትራፎርድ ሲለቀቅ ወደ ጁቬንቱስ አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ ይሆናል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡ እርግጥ ነው ሌሎች በማንቸስተር ዩናይትድ ከአካዳሚው የተገኙ ተጨዋቾች በዋናው ቡድን በታሰበው ደረጃ ባለመሰለፋቸው ክለቡን ቢለቅቁም የፈረንሳዊውን ያህል በሌላ ክለብ ስኬታማ ሆኖ የውይይት ርዕስ የፈጠረ የለም፡፡
ሰር አሌክስ በፕሪሚየር ሊጉ የመሰለፍ ዕድል የነፈጉት ፖግባ በአሰልጣኙ ደስተኛ አልሆነም፤ አሰልጣኙ ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር ባደረጉት ውይይት ወኪሉ ሳምንታዊ 20 ሺ ፓውንድ እንዲከታተለው መጠየቁ አላስደሰታቸውም፡፡
በማንቸስተር ዩናይትድ በወጣት ዕድሜ መጥቶ ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ ባርሴሎና አምርቶ ስኬታማ የሆነው ጄራርድ ፒኬ ነው፤ ግዙፉ ተከላካይ በሪዮ ፈርዲናንድ ኔማንያ ቪዲችን ጥምረት መስበር ተስኖት ክለቡን ለመልቀቅ ተገድዷል፡፡ ሪድ በጣም በቅርቡ ‹‹ፒኬ በእንግሊዝ ቢቆይ በፕሪሚየር ሊጉ ስኬታማ ስለሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም ማለቱ ወደ ባርሴሎና ማምራቱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ያስብላል፡፡
ምንም ይሁን ምን ግን ፖግባ አሁን ባለው ደረጃ በእንግሊዝ እግርኳስ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚቸገር አይሆንም፡፡ የ23 ዓመቱ አማካይ በዚህ ዕድሜው እንኳን የላቀ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ‹‹የዓለማችን ምርጡ ተጨዋች ስለሆኑ ባላውቅም በአሁኑ ሰዓት ምር አማካይ ሆኗል›› ብሏል ፈርንዲናንድ በ2014 በሰጠው አስተያየት፡፡
ለፖግባ መልቀቅ በምክንያትነት ከሚቀርቡ ግብአቶች መሃከል የተጫዋቹ ባህሪይ፣ ከፍ ያለ ግምት እንዲሁም የወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጉዳይ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፣ ፈርጉሰን የህይወት ታሪካቸውን በሚተርከው መፅሐፋቸው ላይ ራዮላን ቢወቅሱም ወኪሉ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
‹‹በወቅቱ ለደምበኛዬ ጥቅም መከራከር ነበረብኝ፤ በፍጥነት የማገኘውን ጥቅም ባስስ ቅድሚያ የምሰጠው ፖግባ በማንቸስተር እንዲቆይ ማድረግ ነበር፡፡ ፖግባ በማንቸስተር እንዲቆይ ማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም የፖግባን ፍላጎት ማስቀደም ነበረብኝ፡፡ የእርሱ ፍላጎት ደግሞ ወደ ቱሪን ማምራት ነበር፡፡ ፈርጉሰን የሚወድደው እርሱን የሚያከብሩትን ነው፤ ከእርሱ መፅሐፍ መረዳት የቻልኩት የፖግባን እውነተኛ ማንነት አልተረዳም›› ብሏል፡፡
ምናልባት ፈርጊ የተጫዋቾቹን ዕድገት ለመጠበቅ ተጨዋቹ ከጫና ነፃ መሆን እንዳለበት ተገንዝበው ሊሆን ይችላል፡፡ ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ የወጣት ተጨዋቾችን አቅም የመረዳት ችግር የለባቸውም፡፡
ሌሎች በፖግባ እና ፈርጉሰን መሀከል የተፈጠረውን አለመረጋጋት በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጡት በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፈረንሳዊው በግል እያሳየ የሚገኘው ዕድገት እንዲታወቅበት እና ምን ያህል ጠቃሚ ተጨዋቾች እንደሆነ ማወቅ ይፈልግ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በፈርጊ ምን ያህል እምነት እንደተጣለበት ማወቅ ይፈልግ ነበር፡፡ ይሄ በሆነበት ወቅት ሰር አሌክስ ጫማውን የሰቀለውን ፖል ስኮልስ ከቤት ጠርተው ቡድኑን እንዲቀላቀል በማድረጋቸው ወጣቱ አማካይ ተስፋ በመቁረጥ ኦልድ ትራፎርድን ለመልቀቅ ወሰነ፡፡
ወደ ጁቬንቱስ ካመራ በኋላ ያለውን አቅም ሙሉ ለሙሉ አውጥቶ ለመጠቀም አልተቸገረም፡፡ በቴክኒኩ ከእኛ ሳይሆን በአካል ብቃቱ እና አካላዊ ዕድገቱን ጠብቆ የተጓዘው ፓግባ ከወቅቱ ታላላቅ አማካዮች ተርታ ለመካተት አልተቸገረም፡፡
በዚህ ወቅት 100 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመተው አማካይ በባርሴሎና፣ ሪያል ማድሪድ እና ፓራሰን ዠርመ እየተፈለገ ነው፤ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ ይሄንን ተጨዋች ቢያገኙ አይጠሉም፡፡ ጁቬንቱስ ይሄንን ተጨዋች መሸጥ ባይፈልግም ኬቨን ዴ ብሩይነን ካገኘ ለማንቸስተር ሲቲ ሊሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
‹‹በሁለቱ መሀከል ከፍተኛ ልዩነት አለ›› ይላሉ፡፡ አሰልጣን ማኑዌል ፔሌግሪኒ፤ ‹‹የማንቸስተር ዩናይትድን ሲለቅ በክለቡ የማይፈለግ ነፃ ተጨዋች ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት የጁቬንቱስ ቁልፍ ተጨዋች ነው፡፡ ያም ከአሁኑ ጋር በጭራሽ አይገናኝም፡፡
ፓግባ እና ዴ ብሩይነ ይመሳሰላሉ፡፡ ሁለቱም በእናት ክለባቸው ተገፍተው በአሁኑ ሰዓት ከምርጥ አማካዮች ተርታ ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ፤ ሆኖም ግን አንድ ነገር እርግጥ ነው፡፡ ፈርጉሰን ፓግባን አቆይተው ቢሆን ኖሮ 28 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቶበት ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የወጣውን ማሮን ፌላይኒን በኦልድ ትራፎርድ አንመለከተውም ነበር፡፡
ፓግባ በ2015/16
ተጫወተ፡- 35
ጎል፡- 8
ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ፡- 36%
የፈጠረው የጎል ዕድል፡- 46
ያቀበለው ኳስ በመቶኛ፡- 83%
የአንድ ለአንድ የበላይነት፡- 51%