ኢትዮጵያ ቡና ከሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ ፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እንዳስታወቀው ዛሬ ጥቅምት 23/2008 ዓ.ም በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥትዋል ፡፡ ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ለኢትዮጵያ ቡና በ10 ወር 2 ሚሊዮን ብር ስፖንሰርሺፕ የፈረመ ሲሆን አጠቃላይ ውሉ ለ5 አመት ይዘልቃል ፡፡በስምምነቱ መሰረት የሐበሻ ሲሚንቶ ሎጎ በኢትዮጵያ ቡና መለያ በቀኝ በኩል የሚያርፍ ይሆናል ይህም በአምበሉ መሱድ መሀመድ አማካኝነት ተዋውቋል ፡፡ በቀጣይ ሚያዝያ ወር በሚደረግ ውይይት ስፖንሰርሺፑን ለማሳደግ እና ውሉን ለማሻሻል እንደሚነጋገሩ በቦታው ተገልፅዋል ፡፡ የድርጅቱ የስራ ሃላፊዎች እና የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ከግንቦት ወር በኋላ ስራ ከሚጀምረው ሐበሻ ሲሚንቶ ጋር በትብብር በመስራት ለውጤታማነት እንደሚተጉ ገልፀዋል ፡፡
The post Sport: ሐበሻ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን በ10 ወር 2 ሚሊዮን ብር እየከፈለው ስፖንሰር ለማድረግ ተሰማማ appeared first on Zehabesha Amharic.