Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

ኢትዮጵያ ምርጥ 2ኛ ሆና ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ያላትን ዕድል ለማስፋት ከሌሴቶ ጋር ትፋለማለች

$
0
0

ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በሚቀጥለው ዓመት 2017 በጋቦን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችላትን ዕድል ለማግኘት ኢትዮጵያ የመጨረሻ ዕድሏን ነገ ትሞክራለች:: የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ባለፈው ሐሙስ ሲሸልስን በደጋፊዋና በሜዳዋ 2ለ0 ካሸነፈ በኋላ ወደ 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋገጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ምርጥ 2ኛ ሆና የማለፍ እድሏን ለማስፋት ነገ ሌሴቶን ትገጥማለች::

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመሩት ዋሊያዎቹ ነገ በማሱሮ ከተማ ለሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ላለፉት 10 ቀናት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደቆዩ ተነግሯል:: ወደ ሌሴቶ የተጓዙት የብሔራዊ ቡድናችን አባላትም በግብ ጠባቂነት ጀማል ጣሰው እና አቤል ማሞ አብረው፤ በተከላካይ ስፍራ አንተነህ ተስፋዬ፣አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየህ፣ ደስታ ዮሐንስ፣አህመድ ረሺድ እና አብዱልከሪም መሐመድ ፤ በአማካይ መስመር ኤልያስ ማሞ ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ኤፍሬም አሻሞ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ታደለ መንገሻ፣ ሽመክት ጉግሳ እና አስራት መገርሳ እንዲሁም በአጥቂ ስፍራ ታፈሰ ተስፋዬ፣ ዳዊት ፍቃዱ እና ጌታነህ ከበደ መሆናቸው ታውቋል::

walia

ዋሊያዎቹ የሌሴቶን ብሄራዊ ቡድን ባህር ዳር ላይ 2ለ1 ያሸነፉ ሲሆን በነገው ጨዋታ ካሸነፉ በምርጥ 2ኛነት የማለፍ እድላቸውን ያሰፉታል::

እንደታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ግሩም ሰይፉ ዘገባ ኢትዮጵያ ከነገው ጨዋታ በፊት በ5 ነጥብ እና በ5 የግብ ክፍያ ሁለተኛ ደረጃን እንደያዘች ነው፡፡ በ5ኛ ዙር ማጣርያ ግጥሚያ በአልጄርያ የተሸነፈችው ሲሸልስ በ4 ነጥብ እና በ5 የግብ እዳ 3ኛው ደረጃ ላይ ስትቀር ሌሶቶ ከነገ ጨዋታ በፊት በ3 ነጥብና በ4 የግብ እዳ 4ኛ ደረጃ ላይ ነች፡፡
ከ5ኛው ዙር የማጣርያ ጨዋታዎች በፊት በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣርያው ከተደለደሉት 14 ምድቦች በምርጥ ሁለተኛነት ለማለፍ በሚቻልባቸው 2 እድሎች ኢትዮጵያ በ11ኛ ደረጃ መጨረሻ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ በምርጥ ሁለተኛነት የማለፍ እድል የደረጃ ሰንጠረዥ ከምድብ 3 ቤኒን በ8 ነጥብ መሪነቱን እንደያዘች ነው፡፡ በምርጥ ሁለተኛነት ለማለፍ ባለው እድል ለመጠቀም ግን ከኢኳቶርያል ጊኒ ጋር ከምታደርገው ጨዋታ በፊት በፊፋ የተጣለባት እግድ መነሳት አለበት፡፡ እገዳው ካልተነሳላት ለሌሎች ቡድኖች ሰፊ እድል ይፈጠራል፡፡ ከምድብ 1 ቱኒዚያ፤ ከምድብ 13 ሞውሪታኒያ፤ ከምድብ 4 ኡጋንዳ እንዲሁም ከምድብ 2 መካከለኛው አፍሪካ በ7 ነጥብ እስከ 5 ባለው ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡ ከምድብ 6 ኬፕ ቨርዴ፤ ከምድብ 7 ኮንጎ እንዲሁም ከምድብ 5 ብሩንዲ በ6 ነጥብ ሲከተሉ፤ ከምድብ 12 ስዋዚላንድ እና ከምድብ 10 ኢትዮጵያ በ5 ነጥብ እየተፎካከሩ ናቸው፡፡

 

የዛሬ ጨዋታዎች፡

15፡30 – ጅቡቲ ከ ቱኒዚያ (ስታደ ናሽናል ኤል ሃጂ ሃሰን ጉሌድ አፕቲዶን)

17፡00 – ሞሪታንያ ከ ካሜሮን (ኦፊስ ዱ ኮምፕሌክስ ኦሎምፒክ ደ ናውኩቾ)

19፡00 – ሊቢያ ከ ሞሮኮ (ስታደ ኦሎምፒክ ደ ራደስ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles