(ዘ-ሐበሻ) አሰልጣኙን አሰናብቶ ገብረመድህን ኃይሌን በቅርቡ በተጠባባቂ አሰልጣኝነት የሾመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምርጥ 2ኛነት ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ያለውን እድል እያሰፋ ነው:: ዛሬ የሌሶቶ ብሔራዊ ቡድንን ሃገሩ ላይ ሄዶ 2ለ1 ያሸነፈው ብሔራዊ ቡድናችን ሁለቱንም የማሸነፊያ ጎሎች ያገባው ጌታነህ ከበደ ነው::
ኢትዮጵያ ምርጥ 2ኛነት ለማለፍ ለሁለት ብሔራዊ ባለው እድል ከምድብ 4 ኡጋንዳ 10 ነጥብ በመያዝ ትመራለች፡፡ ከምድብ 1 ኬፕቨርዴ እንዲሁም ከምድብ 6 ላይቤርያ 9 ነጥብ ይዘው ይከተላሉ:: ኢትዮጵያ ከምድብ 10 እንዲሁም ቤኒን ከምድብ 13 በ8 ነጥብ ላይ ሲሆኑ ዋሊያዎቹ በቀጣይ አዲስ አበባ ላይ ከሲሸልስ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ካሸነፉ ተስፋቸውን ያሰፋሉ::
ጌታነህ ከበደ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለሃገራችን 5 ጎሎችን አግብቷል:: በአጠቃላይ 33 ጨዋታዎችን አድርጎ 16 ጎሎችን አግብቷል::