(ዘ-ሐበሻ) ማን.ዩናይትድ በስፔን ላሊጋ ለቭላሪያል እየተጫወተ የሚገኘውን ኤሪክ ባኢሊን ለማስፈረም እየተነጋገረ መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘገበ::
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ኮትዲቭዋራዊውን ተከላካይ ማን.ዩናይትድ በ እጁ ለማስገባት 30 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርቧል::
አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ የ22 ዓመቱን ተከላካይ በማስፈረም የተከላካይ ክፍላቸውን ማጠናቀር ይፈልጋሉ:: በተለይ ማን.ዩናይትድ እንደ ሮሆ ያሉትን ክለቡን አይመጥኑም የሚባሉትን የተከላካይ ክፍሉን ተጫዋቾች በማሰናበት እንደ ኤሪክ ያሉትን ወጣትና ብቃት ያላቸውን ተከላካዮች ማስፈረም ይፈልጋሉ::