Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

ሰበር ዜና: አክሱም ስታዲየም ፌደራል ፖሊሶች ተፈነከቱ –ሕዝቡ በድንጋይ ተከታከተ (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

aksum Tig aksum Tigrai 1 axum tigrai axum

(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ አክሱም ስታዲየም ውስጥ በተደረገ የ እግር ኳስ ጨዋታ ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት ፖሊሶችና በርካታ የስፖርት ደጋፊዎች ተፈነከቱ::

በአክሱም ስታዲየም የአክሱም ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ እየደረገ ባለበት ወቅት ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት የተነሳ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ስታዲየሙ ሄልሜት ባጠለቁ ልዩ ኃይሎች መከበቡ ታውቋል::

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የሚጫወቱት ሁለቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች ያነሱት ሁከት ላይ ተጫዋቾች ሳይቀሩ መፈንከታቸውና ደጋፊዎች በድንጋይ ሲከታከቱ እንደቆዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቡና ደጋፊዎች ባነሱት ብጥብጥ ስታዲየሙ ላይ እና በሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ አንድ ሰው መሞቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles