አጭር መረጃ: ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከጋና አቻው ጋር በኬፕኮስት ስታዲየም የመልስ ጨዋታ ነበራቸው:: ሆኖም ግን በኬፕኮስት በጣለው ዶፍ ዝናብ የተነሳ ጨዋታው ለነገ ተዘዋውሯል::
በጋና ኬፕኮስት ስታዲየም የጣለውን ዶፍ ዝናብ ተከትሎ ሜዳው እጅጉን መጨቅየቱን እና ለነገ እንዲተላለፍ የተወሰነው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ ፉትቦል ኮንፌዴሬሽን ተወካዮች ሜዳውን ከመረመሩ በኋላ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::
ወጣት በብሔራዊ ቡድናችን ኢትዮጵያ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ ጋናን 2ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል::
መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን