ሶማሊ-እንግሊዛዊዉን ሙሐመድ ፋራህ በማሽነፉ የሚታወቀዉ ኢብራሒም ጄይላኒ አሸነፈ። በረመዳን ባለፈዉ ሀሙስ ስቶክሆልም ስዉዲን ዉስጥ በተደረገዉ የ5000 ሜትር የሩጫ ዉድድር ላይ ኢብራሒም ጅይላኒ አንደኛ ወጥቷል። ኢትዮጵያን ወክለዉ ከሚወዳደሩት ሯጮች መካከል የተለያ ማሊያ የለበሰዉ ኢብራሒም የአንደኝነት ቦታዉን ይዞ ይመራ የነበረዉን ዮሚፍ ቀጄልቻን በመቀድም ነዉ አንደኛ ለመዉጣት የቻለዉ። በዉጤቱም ዮሚፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ ሲሆን ሙክታር እድሪስ ሶስተኛ ወጥቷል።
ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ያለዉን ቦታ በመያዝ ኢትዮጵያዉያን እንዳሸነፉበት በታወቀዉ የዳይመንድ ሊግ ዉድድር ኢብራሒም ጀይላኒ፣ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ሙክታር እድሪስ፣ይገረም ደምመላሽ፣የኔነዉ አላምረዉ፣ሰለሞን ብርሃኑ ከአንድ እስከ ስድስት ያለዉን ቦታ ሲይዙ ጌታነህ ታምሬ ሰባተኛ ወጥቷል።
ኢብራሒምና ሙክታር ከድል በኋላ ስጁድ የወረዱ ሲሆን ሲተቃቀፉም ታይቷል።ቢቢኤን አትሌቶቻችንን እንኳን ቀናቹ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።