Quantcast
Channel: ስፖርት | ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) - Latest Ethiopian News Provider
Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Sport: ኤደን ሃዛርድ ‹‹ያጣሁትን በራስ የመተማመን መንፈሴን መልሼ አግኝቼዋለሁ››

$
0
0

ጋዲሳ ገመቹ | ለዘ-ሐበሻ

ዓምና በእንግሊዝ እግርኳስ ያሉትን ሁሉንም አይነት የኮከብ ተጨዋችነት ስያሜዎችን ያገኘው ኤደን ሃዛርድ ዘንድሮ  በድንገት አቋሙ ወርዶ መገኘቱ በርካታዎችን ያስገረመ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለቤልጅየማዊው ፕሌይ ሜከር የዘንድሮው የአቋም መውረድ ችግር በቂ ማስረጃ ከሚሆኑት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በዘንድሮ የውድድር ዘመን የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን ለማስቆጠር እስከ አፕሪል ወር ድረስ ለመታገስ መገደዱ ነው፡፡

Eden Hazard

ሆኖም ግን ከዛ ወዲህ ባሉት ሳምንታት ውስጥ ዳግም ወደ ጥሩ አቋም ማንሰራራት መቻሉንና አጥቶት የነበረው ያማረ በራስ የመተማመን መንፈሱ ወደ ቦታው እንደተመለሱት በማረጋገጥ ሰሞኑን መግለጫውን ሰጥቷል፡፡ ሃዛርድ በዚህ ወር በፈረንሳይ አዘጋጅነት በሚደረገው የዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎን የሚያደርገው የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት ይመራል፡፡ ይህንን ክብር እንዲያገኝ የረዳው የማንችስተር ሲቲው የመሀል ተከላካይ ቪንሶ ኮምፓኒ በጉዳት ሳቢያ የዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎ የሚያመልጠው በመሆኑ ነው፡፡ ሃዛርድ ለቼልሲ በ2012 ከመፈረሙ በፊት ለፈረንሳዩ ሊል ክለብ ለሰባት ዓመታት ያህል ተጫውቷል፡፡

ይህ የዩሮ 2016 ውድድር አዘጋጅ በሆነችው ፈረንሳይ መጫወት እንደ ሀገሩ የሚቆጥረው ምክንያት እንደሚሆን በማመን የቼልሲው ፕሌይ ሜከር መግለጫውን የሰጠው ‹‹የዘንድሮውን ሲዝን ያሳለፍኩት በአብዛኛው ግጥሚያዎች ላይ የምመነኘውን አይነት ታላቅ ፐርፎርማንስን ማበርከት ተስኖኝ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን ከአፕሪል ወር ወዲህ ባሉት ወራት ውስጥ እስከዛ ደረጃ ድረስ ለበርካታ ወራት አጥቼው የነበረው በራስ የመተማመን መንፈስን ዳግም መልሼ ማግኘት መቻሌን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ለቼልሲ ለመጨረሻ ጊዜ በሜዳ ላይ ሁሉንም አይነት ጥረት ያደረኩበት ግጥሚያ ፒ ኤስ ጂን የተፋለምንበት የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ነው፡፡ በዛ ግጥሚያ በመጨረሻዎቹ አጠቃላዩ ውስጥ ያጋጠመኝ ጉት አጠቃላዩ ሲዝኔ እንዲበላሽ ትልቅ ተፅዕኖን ፈጥሮብኛል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የሲዝኑ የመጨረሻዎቹ ግጥሚያዎች ግን ዳግም በአስተማማኝ ጥሩ ማች ፊትነሴን ለማድረግ መቻሌ በአሁኑ ወቅት በጥሩ አቋምና ጉልበት ይዤ ለዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎ በተጠናከረ ሁኔታ ዝግጅቴን እንድሰራ የረዳኝ ሆኗል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከዚህ አንፃር ከፊታችን ባለው የዩሮ 2016 ውድድር የቤልጅየም ፉትቦል አፍቃሪዎችን ዳግም ለማስደሰት የምችልበት ያማረ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማርከት እችላለሁ የሚል እምነት አለኝ›› በማለት ነው፡፡

ሃዛርድ በፈረንሳይ አዘጋጅነት በሚካሄደው የዩሮ 2016 ውድድር ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ያለመው የዘንድሮን ሲዝንን ያሳለፈበትን ደካማ አቋሙን ለመርሳት በመመኘት ብቻ ሳይሆን የዛሬ ሁለት ዓመት በብራዚል አዘጋጅነት በተካሄደው የ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ሳይችል የቀረበትን ደካማ አቋምን በማረም የአገሩ ፉትቦል አፍቃሪዎችን ለመካስ በመመኘት ጭምር ነው፡፡

ቤልጅየም በ2014 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው በሩብ ፍፃሜው ደረጃ ላይ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሲሆን የነበረውን አቋምን መለስ ብሎ በማስታወስ የቼልሲው ኮከብ አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹የዛሬ ሁለት ዓመት በዓለም ዋንጫው ውድድር ሁሉም ሰው ከእኔ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማየት ጠብቆ ነበር፡፡ በእኔ እምነትም የሚጠበቅብኝን ውጤታማ ፉትቦልን ለማበርከት ተስኖኝ ከብራዚል ጉዞዬ ለመመለስ ተገድጃለሁ፡፡ ይህንን ስል ግን የቡድናችን ተሰላፊዎች ከዛ ውድድር የተሻለ ስኬትን ለማስመዝገብ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ማድረግ መቻላቸውን በማመን ነው፡፡

እኔ በግሌ ግን በዛ ውድድር የምመኘው አይነት ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን ሳላሳይ የቀረቡበትን ፀፀቱን በዩሮ 2016 ተሳትፎዬ ሙሉ ለሙሉ ለመርሳት ከፍተኛ ጉጉትን ማሳደሬን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡ ከወዲሁም ለአገራችን ፉትቦል  አፍቃሪዎች የፉትቦል አፍቃሪያን ቃል የምገባላቸው በዩሮ 2016 ውድድር ከእኔ የሚጠብቁትን ሁሉንም አይነት ታላቅ ፐርፎርማንስን በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ላይ በማበርከት በያዝኩት ብቃት እንዲኮሩብኝ አደርጋቸዋለሁ በሚል ነው፡፡ በእርግጥ የውድድሩ ተሳትፏችንን የምንጀምረው የቡድናችን አምበል ቬንሶ ካምፓኒን በጉዳት ለማጣት በተገደድንበት ሁኔታ ነው፡፡ እሱ የቡድናችን ቁልፍ ተጨዋቾችና መሪ በመሆኑ የዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎ እንዳመለጠው መስማት ሁላችንንም አሳዝኖናል፡፡ ሆኖም ግን የካምፓኒ የመሀል ተከላካይ ሚና ግልጋሎትን ለመመለስ የሚችሉልን ብቃታቸው አስተማማኝ የሆኑ የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች በመኖራቸው የእሱ አለመኖርን በውድድሩ ተሳትፎው ለሚኖረን ውጤት በምንም አይነት መልኩ በምክንያትነት የምንጠቅሰው መሆን እምደማይገባ ለማረጋገጥ እውዳለሁ›› በማለት ነው፡፡

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎ ከሚያደርጉት 24 አገሮች በወሩ በፊፋ ደረጃ ተቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቀጥሎ በፊፋ የወሩ ራንኪንግ በ2ኛ ስፍራ ላይ መቀመጡን ከግንዛቤ በማስገባት በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ቤልጅየም በዩሮ 2016 ውድድር ትልቅ ስኬት ይኖታል ቢሉም ሃዛርድ ግን የአገራቸው ብሔራዊ ቡድን የውድድሩ የዋንጫ ድል ለማግኘት ይችላል ከማለት መቆጠብን በመምረጥ በማጠቃለያው ላይ በሰነዘረው አስተያየት ‹‹የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአገሩ ስለሚካሄድ ለዋንጫ ድሉ ትልቅ ተስፋ አለው፡፡ ከፈረንሳይ ቀጥሎም ስፔንና ጀርመን ጠንካራ አቋምን የያዙ ቡድኖ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር የእኛ ቡድን ምናልባትም ከእነዚህ ሶስት አገሮች ቀጥሎ የዋንጫውን ድል የመቀዳጀት ግምት ሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ›› ብሏል፡፡

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 419

Trending Articles