
ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡
Updated | (ዘ-ሐበሻ) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተካሄደ ባለው ኦሎምፒክ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የተወዳደረችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሶፊያ አሰፋ ለፍጻሜ ማለፏን አረጋገጠች::
ሶፊያ በተወዳደረችበት ምድብ የማጣሪያውን ውድድር 9:18:75 በመገባት ሁለተኛ ወጥታ ነው ለማለፍ የቻለችው:: በሶስት ምድብ በተደረገው በዚሁ የሴቶች መሰናክል በሌሎች ምድቦች እቴነሽ ዲሮና ሕይወት አያሌው ተሳትፈው የነበረ ቢሆንም ሳይቀናቸው ቀርቷል:: ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡
ሶፊያ የተወዳደረችበትን ምድብ በአንደኝነት ያጠናቀቀችው በትውልድ ኬንያዊት የሆነችውና አሁን ለባህሬን የትምሮጠው ሩት ጃቤት ናችት::