
ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡
(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በሪዮ በተደረገው የ3000 ሜትር መሰናክል በውድድሩ ላይ ጫማዋ ወልልቆ በአንድ እግር ጫማ ውድድሩን ለመጨረስ የተገደደችው ኢትዮጵዊቷ አትሌት እቴነሽ ዲሮ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይግባኝ በመጠየቋ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወሰነላት::
የ25 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት እቴነሽ ጫማዋ ወልቆ ይህም ቢጎትታትም በ7ኛነት በ9:34.70 ሰዓት በመገባት ውድድሩን አጠናቃለች:: ይህ ሰዓት ለፍጻሜው ውድድር የማያሳልፋት ቢሆንም በይግባኟ መሰረት ግን እንድታልፍ ተፈቅዷል:: በዚህም መሰረት በ3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ኢትዮጵያ በሶፊያ አሰፋና በ እልፍነሽ ዲሮ ትወከላለች::
እቴነሽ በአሁኑ ሰዓት በትዊተር መነጋገሪያ ሆናለች:: ስለርሷ እየተሰጡ ያሉ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን ይመልከቱ::