ቤልጂየማዊው ኢንተርናሽናል አድናን ያንዩዣይ የዘንድሮ ሲዝን የጀመረው ለማንቸስተር ዩናይትድ ጎል በማስቆጠር የታጀበ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት ቢሆንም በሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ግን ከፒ ኤስ ቪ አይንደንሆቨን የገዙት ሜምፌስ ዴፓይን ውጤታማ ፉትቦልን ለማጉላት በመጓጓት ያንዩዣይን በውሰት ውል ወደ ቦሪሽያ ዶርትሙንዱ የመልቀቅ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ያንን ውሳኔያቸውን በማስመልከት ቫንሃል በተደጋጋሚ በሰጡት መግለጫዎች ከጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር በመሳተፍ በቂ ልምድን አግኝቶ እንደሚመለስልኝ በመጓጓት ነው ቢሉም በተግባር ከታየው ለመረዳት ያስቻለው ግን የያንዣይ በውሰት ውል ማምረት ሶቱን አካሎች ማለትም ቦሪሽያ ዶትሙንድ ማንቸስተር ዩናይትድና ራሱ ተጫዋቹን ያልጠቀመ ሆኗል፡፡
ምክንያቱም ያንዩዣይ ለቦሪሽያ ዶርትሙድ የተሰለፈው በአራት ግጥሚያዎች ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ብቻ የቡንደስሊጋ ግጥሚያው ነው ሌሎቹ ሶስት ጨዋታዎችን ያደረገው በዩሮፓ ሊግ ውድድር ነው፡፡ የዶርትሙንዱ አሰልጣኝ ለያንዣይ በበቂ ግጥሚያዎች የመሰለፍ እድልን ያልሰጡበት ምክንያት የሚገልኑት ግጥሚያዎችን ለማድረግ የስነ ልቦና ጥንካሬ አልታየበትም በማለት ነው፡፡
ይህ አባባላቸው በ20 ዓመቱ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል በቫንሃል ችሎታው ሙሉ እምነትን ባለማሳደሩ መጠነኛ የሆነ የመረበሽ መንፈስ እንደተፈጠረበት ነው ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ግን ዶርትሙንድ የያንዩዣይን ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የውሰት ውልን ለማቋረጥ በመስማማት ሉዊ ቫንሃል ወደሚወደው ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ መልሰውታል፡፡ ይህንን ተከትሎም የያንዩዣይ ወደ ኦልድትራፎርድ መመለስ ከጉዳቱ ይልቅ ጠቀሜታው የሰፋ እንደሚሆን በማመን አስተያየታቸውን የሚሰጡ ባለሙያዎች ተበራክተዋል፡፡ በተለይም የዛሬ ሁለት ዓመት ከማንቸስተር ዩናይትድ ፉትቦል አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ለመሸጋገር የቻለው ቤልጅየማዊው ወጣት ወደ ኦልድትራፎርድ መመለሱ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል ለሉዊ ቫንሃል ቡድን የሚኖረውን ጠቀሜታዎችን የዴይሊ ሚረር የፉትቦል ተንታኞች ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡
1. ጎል የማስቆጠር ተሰጥኦው
ማንቸስተር ዩናይትድ የዘንድሮን ሲዝንን ያጋመሰው ከዚህ በፊት በነበረው በተለይ ሁኔታ በበቂ ጎሎችን የማስቆጠር ረሃብ ተፈጥሮበት ነው፡፡ ለዚህ አንዱ ችግሩ የቡድኑ የአጥቂና አማካይ ክፍል ተጨዋቾች የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን የማድረግ ድርጊትን እያጡ ሲመጡ መታየታቸው ነው፡፡ ይህ ዥ ችግራቸው ማንቸስተር ዩናይትድ በእስካሁኑ ሲዝን ባደረጋቸው 20 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች 24 ጎሎቹ ብቻ እንዲኖሩት መንስኤ ሆኖታል፡፡ ያንዩዣይ ግን በሚፈጠሩለት ጎል የማስቆጠር እድሎችን ካለምንም ማመንታት ለመጠቀም ከርቀት ሳይቀር ጠንካራ ሹትን በመምታት ከፍተኛ ድፍረትን የተላበሰ ተጨዋች ነው፡፡
2. የሚያስገኘው ከፍተኛ ፍጥነት
በሉዊ ቫንሃል ስር በማንቸስተር ዩናይትድ የማጥቃት እንቅስቃሴ በመታየት ላይ ያለው ችግሮች ውስጥ ከፍተኛ ፍጥነቱ በጣት አንዱ ነው፡፡ ይህንን ችግሩን ለመቅፈረፍ ሲሉም ቫንሃል በዘንድሮው ሲዝን ዝውውር መስኮት ፔድሮ ባርሴሎና ለመግዛት ተቃርበው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ፔድሮ በመጨረሻው ሰዓት ወደ ቼልሲ ማምራትን ምርጫው በማድረጉ ጥረታቸው ሳይሰምርላቸው ቀርቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ሌላው ከፍተኛ ፍጥነትን የተላበሰ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያለው ያንዩዠይን የውሰት ውሉን አቋርጦ እንዲመለስ ባደረጉበት ውሳኔያቸው ፔድሮን ሲያስፈርሙበት የቀሩበት ስህተታቸውን መጠነኛ የሆነ እርምትን የሚያስገኙለት እንደሚሆን ይታመናል፡፡
3. በተጋጣሚ ላይ የሚፈጠረው ጫና
ያንዩዣይ በተፈጥሮው በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎች ላይ የኳስ ቁጥጥርን ይዞ በመሮጥ ከፍተኛ ጫና እንዲፈጠርባቸው የማድረግ ተሰጥኦው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ተሰጥኦው የክለቡ ደጋፊዎች በመነቃቃት ለቡድናቸው ለሙሉሃይሉ የማጥቃት ተነሳሽነት እንዲኖው የማያቋርጥ ድጋፍን እንዲሰጡት የሚያስገድዳቸው ይሆናል፡፡
ምክንያቱም ያንዩዣይ በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ ድሪብሊንጎችን በሚያደርግበት ወቅት በኦልድትራፎርድ ተደናቂ ድባብ እንዲፈጠር ምክንያት ሲሆን መታየቱ የተለመደ ነው፡፡
4. ለማን.ዩናይትድ ስኬት ያለው ተቆረቋሪነት
ሉዊ ቫንሃል ከተተቹበት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ማንቸስተር ዩናይትድ በፉትቦል አካዳሚ ያፈራቸው ዳኒ ዌልቤክና ቶም ክሌቨርሌይን የመሳሰሉት የራሱ የሆኑ ተጨዋቾችን ወደ ሌሎች ከክለቦች እንዳይመሩ ያደረጉበት ተግባራቸው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ያንዩዣይን የመሰሉበት ተግባራቸው ከዚህ ወቀሳ ራሳቸውን ማዳን እንዲጀምሩ የሚረዳቸው እንደሚሆን ይታመናል፡፡
ደግሞም ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል በማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀር ለክለቡ ስኬታማነት ከፍተኛ የሆነ የተቆርቋሪነት መንፈስን በመላበስ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎችን ከፍተኛ በሆነ በማሸነፍ ወኔ የማድረግ ባህል ያለው በመሆኑ ነው፡፡ የቤልጅየማዊው ከፍተኛ የማሸነፍ ወኔ በዙሪያው ላሉት የቡድኑ ጓደኞች በድል የመነሳሳትን መንፈስን የሚፈጥርላቸው እንደሚሆን ይታመናል፡፡
5. ለማታ የሚሰጠው ጠቀሜታ
ሉዊ ቫንሃል በስፔናዊው ኢንተርናሽናል ሁዋን ማታ ተደናቂ ኳሊቲዎችን በግራ ክንፍ በኩል እንዲሰለፍ በማስገደድ እያባከኑት ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱም ለማታ ይበልጥ ተስማሚ የሚሆንለት ጨዋታ ሚና ከፊት አጥቂ ጀርባ ባለው ቦታ ወደመሃል ገብቶ የሚጫወትበት ነፃነትን የሚያገኝበት ነው፡፡ በአንፃሩ ያንዩዩይ የበለጠ ውጤታማ ግልጋሎትን የሚሰጠው በግራ ክንፍ በኩል ግጥሚያዎችን በመጀመር ወደ መሃል ሰንጥቆ በመግባት በጠንካራ ቀኝ እግሩ የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን የሚያደርግበት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የያንዩዣይ መመለስ የማንቸስተር ዩናይትድ ግራ ክንፍን በመረከብ ወደ ማታ በሚመርጠው የጨዋታ ሚና በመሰለፍ ዕድልን ፈጠሮለት ነፃ እንዲወጣ የሚረዳው እንደሚሆን ይታመናል፡፡
The post Sport: የአድናን ያንዩዣይ መመለስ | ለማንቸስተር ዩናይትድ የሚያስገኙለት 5 ቁልፍ ጠቀሜታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.