ዛሬ እሁድ ዩናይትድ አርሰናልን በፕሪሚየር ሊጉ ገጥሞ 3ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ብዙዎች በጨዋታው ላይ 2 ግቦችን በማስቆጠርና አንድ ደግሞ አመቻችቶ የነበረው ረሽፎርድ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ነበር።
ታዲያ የጨዋታው ኮከብ ይህ ታዳጊ ተጫዋች ማን ነው?
ስም:ማርክስ ራሽፎርድ
የልደት ቀን:ጥቅምት 31፣ 1997 (እ.ኤ.አ)
የትውልድ ስፍራ: ማንቸስተር
የጨዋታ ስፍራው : አጥቂ
ዩናይትድ ተቀላቀለ: ኃምሌ 1፣ 2014
ረሽፎርድ ግሩም በሆነ ሁኔታና ሚዛናዊኑን ጠብቆ መጫወት የሚችል እንዲሁም ኳስን በኃይል አክርሮ መምታት የሚችል ታዳጊ ተጫዋች ነው። ይህ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ታዳጊ በደረጃው አስደናቂ ለውጥ ያደረገ ሲሆን በ2015 የማንችስተር ዩናይትድን የመጀመሪያ ቡድን መቀላቀልም ችሏል።
በ2013/14 የውድድር ዘመን ከሌስተር ሲቲ ጋር በተደረገው የኤፍኤ ወጣቶች ዋንጫ ላይ በድንገት መሰለፍ በመቻሉ የመጀመሪያውን ትልቅ ጨዋታ አድርጓል። በወቅቱ በቦታው ላይ ተሰልፎ ባይጫወትም መጥፎ አቋም ሳያሳይ ወጥቷል።
በ10 ጨዋታዎች ላይ 4 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ መቻሉና በሚየደርጋቸው የግብ ሙከራ ጥረቶች በታዲጊዎች ማሰልጠኛ ውስጥ የክለቡ መልማዮችን ቀልብ መያዝም ችሏል። ከታቀደለት ጊዜ በፊትም ቀድሞ እንደሄደ እንዲሰማቸው አድርጓል።
ከዩናይትድ ጋር በ2014 በሚልክ ካፕ ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላም ዲሜትሪ ሚሼል በጉዳት ምክኒያት መሰለፍ ባልቻለባቸው ጨዋታዎች ላይ የዩናይትድ ታዳጊ ቡድን ዋና አጥቂ ሆነ። በእነዚህ ጊዜያትም የመሃል ለመሃል የፊት ተጫዋችነት ሚናን በሚገባ ልምድ ቀስሟል። በ25 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 13 ግቦችን ከመረብ በማዋሃድ የኮክብነት ተስፋ ያለው ተጫዋች መሆኑንም አሳይቷል። በወጣቶች የኤፍኤው ዋንጫ ላይ በቶተንሃም ላይ ያስቆጠረው ድንቅ ቅጣት ምት ተጫዋቹ በቆሙ ኳሶች ላይ ያለውን ብቃት ማሳየት የቻለም ነበር።
ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ቡድን ውስጥ በመደበኛነት ግብ ማስቆጠሩን ቀጥሎበትም በዋርን ጆይሱ ከ21 ዓመት በታች የዩናይትድ ቡድን ውስጥ የመጫወት ዕድል አግኝቷል።
ይህን ቡድንም በአውሮፓ ህብረት የእግር ኳስ ማህበር የወጣቶች ሊግ መድረክ ላይ ከኒኪ በት የአምበልነት የክርን ማዕረጉን ተቀብሎ ቡድኑን በአምበልነትና በፊት ተጫዋችነት መርቷል። ታታሪው አጥቂ ከ21 ዓመት በታች ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መሰለፍ የቻለው ቡድኑ ሌስተርን 6ለ1 በረታበት ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ ነበር። እንዲሁም በኤፍኤው የወጣቶች ዋንጫ ውድድር ላይ ጉልህ የሆነ ቁልፍ ሚናም ነበረው።
The post Sport: አርሰናል ላይ ዛሬ ሁለቱን ጎል ያገባው ማርከስ ራሽፎርድ ማን ነው? appeared first on Zehabesha Amharic.