(ዘ-ሐበሻ) የካታሎናዊው ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋን አንሳ:: ባርሴሎና በመጨረሻዎቹ ጥቂት ጨዋታዎች ነጥቦችን በመጣሉ ተከታዮቹ ሲጠጋጉት የቆዩ ሲሆን በዚህም ሻምፒዮን ይሆናል ወይ? የሚለው አጠያያቂ ሆኖ ነበር::
ሆኖም ግን ባርሳ ዛሬ በተደረገው የላሊጋው የመጨረሻ ጨዋታው ግራናዳን 3 -0 አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል:: ጎሎቹን ያስቆጠረው ደግሞ የፒቺቺ አሸናፊ ሆኖ ያጠናቀቀው ስዋሬዝ ነው። ስዋሬዝ ከመስመር ተጨዋቾቹ አልባ እና አልቬዝ የተሻገለት ኳስ አጨራረሱን በማሳመር አስቆጥሯል:: ለ3ኛው ጎል አመቻችቶ ኳሱን ያቀበለው ደግሞ ብራዚላዊው ኔማር ነበር::
ባርሴሎና የስፔንን ላሊጋ 24 ጊዜ ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ 32 ጊዜ አሸንፏል:: ባርሴሎና ባለፈው ዓመትም የላሊጋው ሻምፒዮን ነበር::