ድል የተጠማው የብሔራዊ ቡድናችን ደጋፊ (ፎቶ ከፋይል)
ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት
(ዘ-ሐበሻ) ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የጋና አቻው የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጋጠሙ ታወቀ:: የጋና ብሄራዊ ቡድን ኢትዮጵያን ለመግጠም አዲስ አበባ መግባቱም ተሰምቷል::
የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጨዋታ ቀደም ብል ከናሚቢያ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ በፍጹም የበላይነት 4ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል::
የኢትዮጵያ ወጣቶች ቡድን ብዙ ዝግጅት ሲያደርግ እንደቆየ ከፌዴሬሽኑ የተሰጠው መግለጫ ሲያስረዳ ከኢትዮጵያና ጋና ብሄርዊ ቡድኖች አሸናፊ የሚሆነው ከቱኒዚያ እና ሴኔጋል አሸናፊ ጋር እንደሚጫወት የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል::
የኢትዮጵያ ወጣቶች ቡድን የሶማሊያ አቻውን አሸንፎ ከጋና ጋር የደረሰው ሲሆን ሶማሊያን በማሸነፉም በፌደሬሽኑ ለቡድኑ አባላይ ለያንዳንዳቸው አስር ሺ ብር መሸለሙ ይታወሳል::